Skip to main content

Posts

Showing posts from 2012

የአዲስ አበባ ከተማ እና ምርጫዋ

አዲስ አበባ 125ኛ ዓመቷን እያከበረች ነው፡፡ በከተማይቱ ልደት ሰሞን እናትና አባቷ (በመናገሻ ከተማነት የቆረቆሯት አጤ ምኒልክ እና ስሟን ያወጡለት እቴጌ ጣይቱ) ስማቸው ሲነሳ አልሰማሁም፡፡ ይልቁንም ላለፉት 21 ዓመታት በፌዴራል መንግሥቱ ርዕሰ መሪነታቸው በእጅ አዙር የዘወሯት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ስም በተደጋጋሚ ሲነሳ እና በየመንገዱ ዳር በቆሙ ‹ቢልቦርዶች› ላይ ከከተማይቱ የመሠረተ ልማት አውታሮች ፎቶ ፊት ለፊት በጉልህ በተቀመጡ ምስሎቻቸው ታጅቦ ታይቷል፡፡ የክብረ በዓሉን ክንውን እንዲያዘጋጅ የኢሕአዴግ ሰዎች የሚመሯቸው ዋልታ እና ፋና ጥምር-ድቅል የሆነው ዋፋ የማስታወቂያ ድርጅት ሙሉ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡ ምናልባትም የዚሁ የፓርቲ ጥገኝነት ጉዳይ ይሆናል መለስን በግምባር ቀደምነት የከተማይቱን ቆርቋሪ አስዘንግቶ ያስጠቀሳቸው፡፡ ለነገሩ ይህን ጽሑፍ ለማሰናዳት ያነሳሳኝ የክብረ በዓሉን ዐብይ-ሰብ (figure) ለመሰየም አይደለም፡፡ ስለከተማይቱ እያነሳሁ ይህንን ያፈጠጠ ስህተት ሳልነቅስ ማለፍ ስላልሆነልኝ ነው፡፡ የጽሑፌ ርዕሰ ጉዳይ ሚያዝያ ወር ላይ የሚካሄደው ምርጫ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ከሀገር አቀፍ ምርጫ በሁለት ዓመት እንዲዘገይ የሆነው፣ በምርጫ 97 ከአንድ ወንበር በስተቀር ሁሉንም የከተማዋን ምክር ቤት መቀመጫዎች አሸንፎ የነበረው ቅንጅት ምክር ቤቱ ለመግባት ባለመፍቀዱ   ማሟያ ምርጫ እስኪካሄድ በተፈጠረው መዘግየት ሳቢያ ነው፡፡ ሀገሪቱ ከአንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በላይ ባላየችባቸው ሁለት ዐሥርት ዓመታት ውስጥ፣ አዲስ አበባ አምስት ከንቲባዎችን ለማየት ታድላለች፡፡ አንዴ ግዜያዊ የባለአደራ ከንቲባ ስታስተናግድ ቀደም ብሎ ደግሞ ‹‹ተበለሻሸች›› ተብሎ - የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በሚፈ...

የኛ ኃይል

ከ ዞን ዘጠኝ የተወሰደ በበፍቃዱ ኃይሉ እና ሶልያና ሽመልስ “ፒያሳ፤ መሐሙድጋ ጠብቂኝ” በመሐመድ ሰልማን የተጻፈ እና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ ኢ-ልቦለዳዊ መጣጥፎች ስብስብ ነው፡፡ የዛሬ ዓመት ገደማ ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ በተባለ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት   አማካይነትመጽሐፉን የመገምገሚያ ዝግጅት አምስት ኪሎ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚዬም ቀርቦ ነበር፡፡ በውይይቱ መሐል የመጽሐፉ ዝነኝነት ምንጮች ምን ምን ናቸው የሚል ውይይት የነበረ ሲሆን ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ‹‹ደራሲው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ጸሐፊ የነበረ›› መሆኑን እና ‹‹ጽሑፎቹም በ አዲስ ነገር ጋዜጣ እና ድረገጽ ላይ ወጥተው የነበሩ›› መሆናቸውን ጠቀሰ፡፡ ውይይቱ የአዲስ ነገር ጋዜጣ መታሰቢያ ይመስል፣ የትዝታ ጫወታው ተጧጧፈ እናም ከውይይቱ ተሳታፊዎች አንዱ የሚከተለውን ሲናገር ረዥም ጭብጨባ አዳራሹን አደመቀው ወጣቱ አስተያየት ሰጪ በንግግሩ መሃል የተጠቀመው እና ጢም ብሎ የሞላውን አዳራሽ በጭብጨባ ያናጋው ንግግር የሚከተለው ነበር፡፡ ‹‹ይህ ትውልድ በአዲስ ነገር ጋዜጣ የሚደራደር ትውልድ አይደለም፡፡›› ጉዳዩን አስገራሚ የሚደርገው ወጣቱ ይህንን የተናገረው አዲስ ነገር ጋዜጣ መታተም ካቆመች ከሁለት ዓመታት በኋላ መሆኑ ሲሆን፣ አጋጣሚው የጋዜጣዋ መንፈስ በበርካቶች ልብ ውስጥ በትኩስነት መኖሩን የሚናገር ነበር፡፡ ዛሬ፣ ጥቅምት 5/2005 የዓለም የጡመራ የተግባር ቀን ( Blog Action Day 2012 ) “የኛ ኃይል” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ የጡመራ የተግባር ቀን በየዓመቱ የሚከበር፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ጦማሪዎች በሙሉ በአንድ ሐሳብ ዙሪያ የሚጽፉበት ቀን ነው፡፡ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ2007 ሲሆን በተመሳሳይ   ዓመት ‹‹አ...

የኃይለማርያም ፲ ተግዳሮቶች

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኅልፈት ከተሰማ 50 ቀናት ሆኑት፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ቃለ መሓላ ከፈፀሙ ደግሞ 18 ቀናት፡፡ እነዚህ ከሁለት ሳምንታት እምብዛም ያልበለጡ ቀናት የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምን አያያዝ ለመገምገም በቂ አይደሉም ነገር ግን ‹‹ያባት ዕዳ ለልጅ›› በሚለው ብሒል መሠረት የመለስን ፈለግ በመከተል እና ባለመከተል መካከል፣ ሊያመጧቸው በሚችሏቸው ለውጦች እና ሕዝብ/አገር ከሚጠብቅባቸው ነገሮች አንፃር የሚጠብቃቸውን ተግዳሮት ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በተለይ ከቪኦኤ የእንግሊዝኛው አገልግሎት ጋር ባደረጉት የ40 ደቂቃ ቃለምልልስ፥ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተለየ አቋም እንደሌላቸው መታዘብ ይቻላል፡፡ ፓርቲውም ቢሆን የአቶ መለስን ውርስ ለማስቀጠል እንደሚተጋ በተደጋጋሚ ተናግሯል፡፡ በተቃራኒው መለስ የሚባልላቸውን ያህል ውጤታማ እና ፍፁም አልነበሩም፡፡ ለዚህም ምስክሩ ሳይዘጉ የተዉአቸው የሚከተሉት አጀንዳዎች ናቸው፡፡ የአቶ ኃይለማርያም ተግዳሮቶች ሁነው ይቀጥላሉ፡፡

የ2004 ሒሳብ ሲዘጋ

እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ በዚህ ዓመትም ሰዎች ከፌስቡክ ውጪ እንዴት እንደሚኖሩ ለማወቅ ጉግል ውስጥ ፈልጌም፣ አስፈልጌም መልስ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ስለዚህ በፌስቡክ ውስጥ መኖሬን ቀጥያለሁ፡፡ በርግጥ ፌስቡክ ምንም አልጎደለበትም፤ እንኳን የሆነው የታሰበው ሳይቀር ይወራበታል፡፡ ለአብነትም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርን ሞት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፌስቡክ ምድር ላይ ካለው ‹እቤት-እመስሪያቤት› ምልልስ የተሻለ ፋይዳ ያለው ሥራ ለመስራት የተመቸ ዕድልም ይፈጥራል፡፡ የዳቦ ጉዳይ (bread winning) ሁላችንንም በየሙያችን ቢያሰማራንም፣ የምንናፍቀው እና የሚናፍቀን ሌላ ነገር የለም ማለት መቼም አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ የምንዋደደውን ያክል የምንወደውና የሚወደንን ዓይነት መንግስት ያገኘንበት ጊዜ እምብዛም ነው፡፡ ይህንን መናፈቅ እና መማከር ደንብ ሆኖ፣ በሌላም፣ ዓመቱን ሙሉ በጻፍናቸው ነገሮች ያስደሰትነው ሰው እንዳለ ሁሉ ያስቀየምነው የለም ማለት ዘበት ነውና፣ ያው የግል ጥቅም ይዞን አለመሆኑ ታውቆ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ይቅር መባባልን የመሰለ ነገር የለም፡፡ በዚህ ዓመት በፌስቡክ ገጼ ላይ ያሰፈርኳቸውን እና ከወዳጆቼ ጋር ቅኔ የተዛረፍኩባቸውን ግጥሞች በአንድ መድብል ‹‹ የፌስቡክ ትሩፋት ›› በሚል ጠርዠዋለሁ፡፡ ማንም ቢፈልግ እዚያው ባለበት ማንበብ፣ ወይም ዳውንሎድ ማድረግ ይችላል፡፡ አምና ሁለት ሺህ ሦሰትን በአርባ ሁለት በሚል በ2003 የጻፍኳቸውን ጦማሮች አንድላይ ቢጠረዙ መልካም ነው በሚል ማስቀመጤ ይታወሳል፡፡ አሁንም ዘንድሮ የሞነጫጨርኳቸውን እዚህ አስቀምጫለሁ፡፡ በስህተቴ ያረማችሁኝን እና የነቀፋችሁኝን፣ በብርታቴ ላይ አበርታች የሆነ አስተያየታችሁን ለሰጣችሁኝ፣ በዝምታ ስታነቡኝ ከርማችሁ መንገድ ላይ ...

በቁማቸው ከገደሉት በሞታቸው የገደሉት

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞት በብዙዎች ጉንጭ ለሁለት ወር ሲጉላላ ቆይቶ በኢትዮጵያ መንግስት ከተረጋገጠ ይኸው ሁለት ሳምንት ሊሆነው ጥቂት ቀናት ቀሩት፡፡ መንግስት ብሔራዊ የሐዘን ቀናት እስከዕለተ ቀብራቸው በማወጁ ባንዲራም ዝቅ ብሎ እየተውለበለበ ነው፣ መገናኛ ብዙሐንም ሙሉ ትኩረታቸውን በዚያው በሐዘኑ ጉዳይ ላይ እንዳደረጉ ናቸው፡፡ (በነገራችን ላይ የጡረተኛ ሚኒስትሮችን ጥቅማጥቅም የሚዘረዝረው የ2001 አዋጅ ላይ [አንቀጽ 11/1/ለ] ብሔራዊ የሐዘን ቀን አንድ ቀን እንደሆነ ይደነገጋል፡፡) ኢትዮጵያውያን ወትሮም ቢሆን ሐዘን የማክረር ባሕላችን የተጋነነ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሠልስት ሳይቀር እየተሰረዘ የሦስቱ ቀን ሐዘን ወደሁለት ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡ በነገራችን ላይ የሐዘን ቀናት ወደሦስት ቀናት ዝቅ እንዲሉ የተደረገው በአፄ ምኒልክ አዋጅ የዛሬ መቶ ዓመት ገደማ ነበር፡፡ እንግዲህ በሰሞኑ፣ ሁለት ሳምንታት የዘለቀ የሐዘን ግዜ መቶ ዓመት ያህል ወደኋላ ተመልሰናል ማለት ይቻላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር የሞተበት አገር ሕዝብ ማዘኑ አስገራሚ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን በውዴታም ይሁን በግዴታ ይህንን ያህል ቀናት ማዘኑ ወይም እንዲያዝን ማድረጉ ብዙ ጥያቄዎችን ያጭራል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የምናውራውም ከዚህ ፈር ከለቀቀ የሐዘን ግዜ በስተጀርባ ስላሉ ጉዳዮች ነው፡፡ አንድ፤ ችግር ይኖር ይሆን? አገሪቱ አሁን እየተመራች ያለችው በተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ነው ቢባልም፣ ያንን የሚያስመሰክር ነገር አላየንም፡፡ የመንግስት ልሳን የሆኑት እነ አዲስ ዘመን ሳይቀሩ ‹‹ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር›› እያሉ ነው የሚጠሯቸው፡፡ ከዚያም በላይ አሳሳቢው ግን በቶሎ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ማዕረግ በፓርላማ ምርጫ እ...

ነውርን ማን ፈጠረው?

ሰሞኑን በሞት ስልጣናቸውን ስለለቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር   ያለኝን ትዝታ ‹ የመለስ ሁለት መልክ › በሚል ጽፌው ነበር፡፡ ጽሑፉ ውስጥ የመለስ አስተዳደር በተለይ የተመቻቸው የብሔር አባላት እንዳሉ በስም በመጥቀሴ ‹‹ዘረኛ ነህ›› የሚል ብዙ አስተያየት ተሰንዝሮብኛል፡፡ እነሆ ይህ አስተያየትም ይህን ጽሑፍ ወልዷል፡፡ ነውርን ማን ፈጠረው? በመጀመሪያም፡- ነፃነት እና ልቅነት ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት ለድርድር የማይቀመጡለት አጀንዳ ነው፡፡ ሆኖም ሁሉም ሰው ሐሳቤን በነፃነት የመግለፅ መብቴ በሕግ ተደንግጓል ወይም ተፈጥሮ ያጎናፀፈኝ ነው በማለት እንዳሻው አይናገርም፡፡ በተለይም ሐሳቡ የሚቀርብበት ሚዲየም ሰፊ ሲሆንና ብዙ ተደራሲዎች ሲኖሩት ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ ይህ ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት በርካታ ምክንያቶች አሉ፤ ከነዚህም ውስጥ የሕዝብን አቅጣጫ ላለማሳት፣ መረንነትን ወይም ልቅነትን ላለማስፋፋት እና አሁን ስለሆነው ሳይሆን ነገ እንዲሆን ስለምንፈልገው በመሳሳት (ሳ ላልቶ ይነበብ) ነው፡፡ ሁሉንም በሒደት ወደታች አብራራቸዋለሁ፡፡ ‹የሕዝብን አቅጣጫ ላለማሳት› ያልኩት ሐሳባችንን የምንገልጽበት አገባብ (context) ተደራሲያኑ ጋር ሲደርስ ሌላ አንድምታ እንዳይኖረው የሚለውን ነው፡፡ ምናልባትም ያለፈው ጽሑፍ ውስጥ ‹ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት አዲስ አበባ ውስጥ ከተሰሩ ሕንፃዎች መካከል አብዛኛዎቹ የትግራይ ልጆች ንብረት ናቸው› ማለቴ በአንባቢው ዘንድ የትግራይ ልጆች ሁሉ በኢሕአዴግ ስርዓት ተጠቅሟል የሚል ትርጉም ከሰጠ አቅጣጫ አስቷል ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እኔ በፃፍኩበት መንፈስ የትግራይ ተወላጆች ከኢትዮጵያ ሕዝብ አንፃር ካላቸው ድርሻ (proportion) ጋር ሲወዳደር በስልጣን እና በከተማ ሃብት ይዞታ ላይ ያላቸው...

የመለስ ሁለት መልክ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሞት ‹‹ድንገተኝነት›› ብዙ ድራማዎችን አስከትሏል፡፡ መጀመሪያ ላይ ብዙዎች ተደሰቱ፣ ማታ ላይ ኢቴቪ ያነጋገራቸው ‹‹አንዳንድ ሰዎች›› የሰውየውን ታላቅ መሪነት ሲዘክሩ ያድናቂዎቻቸው ቁጥር ጨመረ፣ በጣም ማታ ላይ ወ/ሮ አዜብ ‹‹ተቀጣሁ፤ ምን አጥፍቼ ነው?›› በማለት ሙሾ ሲያወርዱ ‹‹የመለስ ታላቅነት›› የተገለፀላቸው ሰዎች ቁጥር በእጥፍ አደገ፡፡ ልብ በሉ በሞታቸው የመጀመሪያ ዕለት ብቻ ሁለት የተለያየ ገጽታ ለመያዝ የበቁት መለስ ዜናዊ ብቻ ናቸው፡፡ ነገርዬው ግን አብሯቸው የኖረ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ-አምባገነን መለስ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የሚመስል ነገር መስርተዋል፡፡ ‹‹ዴሞክራሲ›› የሚለው ቃል በሚዲያ ተደጋግሞ እንዲነገርም ይፈልጋሉ፤ ያለ እንዲመስል፡፡ በምርጫ ማሸነፍ ያለበት የእርሳቸው ፓርቲ ብቻ እንደሆነ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የገዢው ፓርቲ ደጋፊ እንዲሆኑ፣ ጋዜጦችና ጋዜጠኞ ስኬታቸውን ብቻ እንዲያወሩ ይፈልጋሉ፡፡ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሲሄድም የሚወስዱትን እርምጃ በ21 ዓመታት አመራራቸው አሳይተውናል፡፡ መለስ ሳያነቡት እንደማያመልጣቸው የነገሩን The Economist ከሞታቸው በኋላ በጻፈው ጽሑፍ ‹‹ መለስ አምባገነንነት ተቀባይነት እንዲያገኝ ሰርተዋል ›› በማለት አስታውሷቸዋል፡፡ ኢትዮ-ኤርትራዊነት መለስ ኦነግ፣ ኦብነግንና ምንም ሪፖርት የተደረገ ጥፋት ሰርቶ የማያውቀውን ግንቦት ሰባትን በአሸባሪነት ሲፈርጁ ለስንት እልቂት ሰበብ የሆነውን ‹‹ሻዕቢያ››ን አሸባሪ ያላሉት በእርሳቸው መስፈርት ስላልሆነ ከመሰላችሁ አትሸወዱ፡፡ ቤተሰባቸው ስለሆነ ነው፡፡ መለስ ለኤርትራ እና ለኢሳይያስ ጥልቅ ፍቅር ነበራቸው፡፡ የ‹‹ትሮይ ፈረስ›› የሚለውን መጽሐፍ ካነበባችሁ ‹‹ኅወሓት››ን ማን ጠፍጥፎ ...