Skip to main content

ከ21 ዓመት በኋላ (ዴሞክራሲ ሲሰላ)


ኢሕአዴግ ከ21 ዓመታት በኋላ በዴሞክራሲ ጎዳና ወደኋለ መመለሱን ለማረጋገጥ ጥናት አያስፈልገውም፡፡ ታሪክን ባጭሩ ‹‹መገረብ›› በቂ ነው፡፡ ሆኖም ከሰሞኑ የተሰራች ትንሽዬ ቅኝትም የምንገርበውን የታሪኩን ወቅታዊ ደረጃ ውጤት ታረዳናለች፡፡

ኢሕአዴግ በትጥቅ ትግል አምባገነኑን ደርግ ከገረሠሠ በኋላ የሽግግር መንግስት አቋቋመ፡፡ የሽግግር መንግስቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ በነፃ ሐሳብ የመግለፅ መብትን እና ወዘተ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚደነግገውን ሕገ መንግስት ቀረፀ፡፡

በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሳተፉበት ምርጫም (ከነእንከኑ) ተካሄደ፣ ተደገመ፡፡ በርካታ የግል ጋዜጦች ተከፈቱ፣ ብዙ ሰዎችም ትንፋሽ ታፍኖ ከሚኖርበት የደርግ የኑሮ ዘዬ በከፊል በመላቀቅ ለመብታቸው ጥብቅና መቆም እና ሐሳባቸውን መግለፅ ጀመሩ፡፡ በዚህ መሃል ሦስተኛው ብሔራዊ ምርጫ (97) መጣ፡፡ ያ ወቅት የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ከፍተኛ ጫፍ (maximum peak) ላይ የደረሰበት ወቅት ነበር፡፡

ምርጫ 97 መጨረሻው ብጥብጥ ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ እያቆጠቆጠ የነበረው ሕዝባዊ ነፃነት እና ዴሞክራሲ ወደአፎቱ ተመለሰ፡፡ ኢሕአዴግም በኢትዮጵያ ታሪክ በምርጫ ስልጣን በመልቀቅ አዲስ ምዕራፍ የመክፈት ዕድሉን በገዛ ፈቃዱ ገደለው፡፡ በርካታ አዋጆች የዴሞክራሲያችንን አቅም፣ የሕዝቡን ነፃነት እና እምነት አሽመደመዱት፡፡

ዛሬ መንግስት ዴሞክራሲን እያሳደገ እንደሆነ ቢናገርም፡፡ እስካሁን ድረስ በሕገመንግስቱ የተቀመጡት መብቶች ባይፋቁም ተግባራዊነታቸው ግን ወደ 1983 ተመልሶ ‹በ› ጉብጠት (n-curve) ሰርቷል፡፡
ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እና መንግስታዊ ቅቡልነትን በአዋጆች ቁጥር፣ በገዢ ፓርቲ አባሎች እና ደጋፊ ነን ባዮች ብዛት እና በምርጫ ውጤት (99.6%) ለመገምገም መሞከር ወደተሳሳተ መደምደሚያ ያደርሰናል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በይነመረብ (Internet) ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በመጠየቅ ስለዴሞክራሲያችን ወቅታዊ፣ ሕዝባዊ የቅቡልነት ደረጃ (legitimacy level) ለመቃኘት አቅጄ ተነሳሁ፡፡ ቅኝቱን ለማካሄድ ያቀረብኩትን መጠይቅ የሚሞሉ ሰዎች ቁጥር መጠይቁን ለማስተዋወቅ የጻፍኩትን ጦማር ካነበቡት ሰዎች ቁጥር እጅግ ያነሰ ነበር፡፡ ይህ አንዱ የዴሞክራሲያችን መክሸፍ (የፍርሃታችን መገለጫ) መሆኑን የተረዳሁት ግን ጥቂት በግል የማውቃቸው ሰዎች ያልሞሉበትን ምክንያት ከነገሩኝ በኋላ ነው፡፡ የመንግስት የደህንነት ሰዎች የመለሱትን መልስ በሆነ መንገድ ያውቁብናል የሚል ስጋት አላቸው፡፡

የሆነ ሆኖ በሞሉት ሰዎች መልስ ላይ ተመስርቼ የደረስኩበት መደምደሚያ የሚከተለውን ይመስላል፤ (ሙሉ ቅጂውን እዚህ ማግኘት ይቻላል፡፡)
በመጠይቁ ውስጥ የተካተቱት መሰረታዊ ጥያቄዎች በሙሉ ከ86 በመቶ በላይ አሉታዊ ምላሾች አሉዋቸው፡፡ አብዛኞቹ የቅኝቱ ተሳታፊዎች ዴሞክራሲ አለ ብለው አያምኑም፣ በመንግስት ምርጫ ይተካል ብለው አያምኑም፣ ሐሳብን የመግለፅ ነፃነት በርግጥም ተረጋግጧል ብለው አያምኑም፣ የሕግ የበላይነት አለ ብለው አያምኑም፣ ዜጎች ሰብአዊ መብታቸው ያለ ዘር እና ፖለቲካዊ አድሎ ይጠበቅላቸዋል ብለው አያምኑም፣ ብዙሐኑ የሚመራበት አናሳው መብቱ የሚከበርበት ስርዓት አለ ብለው አያምኑም፡፡

ሲቪል ማሕበረሰቡ ፖለቲካዊ ተስፋ የማያደርግበት ምክንያት፣ በብዙዎች እምነት የደህንነት ፍራቻ ነው፡፡ መንግስት በምርጫ ይተካል ብለው እንደሚያምኑ የተናገሩት ጥቂቶች እንኳን እንደምክንያት የሚያስቀምጡት የተቃዋሚዎችን ድክመት እና የፖለቲካ ምህዳሩን መጥበብ እንጂ የገዢውን ፓርቲ ተፈላጊነት ወይም ጥንካሬ አይደለም፡፡

በጥቅሉ ጥያቄዎቹ በሙሉ የሚያተኩሩት ስለዴሞክራሲያዊ መርሖቹ በሃገራችን አተገባበር ላይ የመላሾቹን እምነት ማግኘት ላይ ነው፡፡ በውጤቱም መደምደም የሚቻለው አብዛኛዎቹ መላሾች በኢሕዴግ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ላይ ምንም ዓይነት እምነት እንደሌላቸው ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በርግጥም ተተግብሯል እንዲባል ሕዝባዊ ቅቡልነት ያስፈልገዋል፤ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግን ይህ ዓይነቱ ሕዝባዊ ቅቡልነት የሌለው መሆኑን ከዚህ አጭር ቅኝት አጠቃሎ መረዳት ይቻላል፡፡
ኢሕአዴግ ከ21 ዓመታት በኋላ ለስልጣኑ ያለው ቀናኢነት የተጋነነ ደረጃ ላይ ደርሶ የገረሠሠውን አምባገነን ለመተካት እንደበቃ ምስክር መጥራት የማያሻን ይህንን ስናይ ነው፡፡

ቢሆንም የሕዝቦች ትዕግስት ተንጠፍጥፎ ሲያልቅ በጉልበት መብቱን ከመጠየቁ በፊት ቢሰሙም ባይሰሙም የኢሕአዴግ አመራሮችን መምከር ተገቢ ነው፡፡ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ ነፃነት አፋኝ አዋጆች ይከለሱ፣ የይስሙላው ፓርላማ ፈርሶ የሽግግር ፓርላማ ይቋቋም፣ ምርጫ ቦርድ ፈርሶ በገለልተኛ ወገን እንደገና ይዋቀር፣ አዲስ ምርጫ ይካሄድ እና ሕዝባዊ ቅቡልነት ያለው መንግስት ይመስረት፡፡ ይህንን ሁሉ ለማድረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ብቻ በቂ በመሆኑ ባለማድረጋቸው ሃገሪቷ ላይ ለሚደርሰው ኪሳራም ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

The "Corridor Development" is a Façade of the Prosperity Party

Befekadu Hailu I have seen a news report claiming that 40% of central Addis Ababa will be demolished for the corridor development; I am not able to confirm the validity of the news but it sounds real to me given the size of massive operations in the demolition of old neighborhoods and construction of bike lanes, green areas, and glittering street lights. I like to see some beauty added to my city but cannot help mourning the slow death of it too. Addis Ababa was already in a huge crisis of housing and the demolition of houses is exacerbating it. Apparently, Prime Minister Abiy Ahmed is eager to showcase his vision of prosperity by demonstrating how fast his administration can do magic by beautifying the front sides of the streets with lights, new pavements, and painted fences ("to fake it until he makes it" in my friend's words). Therefore, he and his party do not care about the miserable human stories behind the scenes and they will harass you if you tell it (Azeb Woku...

መጽሐፍ የሚወጣው፣ የተዋነይ ዘ ጎንጅ 5 መሥመር ቅኔ

ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል። “የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።” (ተዋነይ ዘ ጎንጅ። ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ) ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን ...

የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ

በፍቃዱ ዘ . ኃይሉ “የአዲስ አበባ ብሔርተኝነት” ቢኖር ኖሮ መሪው ልጅ ሚካኤል ይሆን ነበር። አሁን አሁን እሱ ስለ አዲስ አበባ የዘፈናቸውን ዘፈኖች ቁጥር ራሱ በትክክል መቁጠር ይቸግረኛል። ለአዲስ አበባ ከተዘፈኑ ዘፈኖቹ ውጪም በየዘፈኑ ውስጥ የሚጨማምራቸው መልዕክቶች በራሳቸው መወድሰ አዲስ አበባ ናቸው። ለምሳሌ፣ በቅርቡ በለቀቀው ‘አዲስ አራዳ’ በተሰኘው አልበሙ ውስጥ ‘የድሬ ልጅ’ የሚል ዘፈን አለው። ዘፈኑ የተዘጋጀው ያው የአዲስ አበባ እህት ተደርጋ የምትቆጠረውን ድሬ ዳዋን ለማወደስ ነበር። ልጅ ሚካኤል ግን የአዲስ አበባ ፍቅሩ ያመልጠውና የሚከተለውን ያቀነቅናል፦ “መጣልሽ በሏት፣ ድሬ ድረስ፣  ከአዱ ገነት፣ ከሸገር፣ ከአዲስ ደረሰ፣... የሸገር ልጅ አራዳ ነው፣ ሰው አክባሪ፣ ሰው ወዳዱ፣ ቀላጅና ተረበኛ፣ ፍቅር ይዞ የሚተኛ፣ ‘አለው’ የለ፣ ‘የለው’ የለ፣ ከሁሉ ጋ፣ ግባ ጀባ...፤” ፤ ልጅ ሚካኤል በዚህ አልበሙ ብቻ አዲስ አበባን የሚያውድሰባቸው ሌሎችም ዘፈኖች አሉ፤ ‘ አዲስ አራዳ ’ የሚለው የአልበሙ መጠሪያ እና ‘ሸገር’ የሚሉት ዘፈኖቹ ዋነኞቹ ናቸው። ታዲያ እንዲህ በአዲስ አበባ ፍቅር የሚቃጠለው ልጅ ሚካኤል "ሊነግረን የሚፈልገው ምንድን ነው?" የሚለው ጥያቄ ደጋግሞ ይመጣብኛል። ይህ የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ ምንነትን ለመረዳት የሚጥር ፖለቲካዊ መጣጥፍ ነው። ‘አዲሱ አራዳ’ ማነው? በዚህ ዘፈኑ በብዙዎቻችን ዕድሜ የትዝታ ማኅደር ውስጥ የሚገኙ ነገር ግን በአዲስ አበባ ልማት ሥም የፈረሱ እና እየተረሱ ያሉ ሰፈሮችን ሥም ያነሳሳል። ዘፈኑ በግጥሙም በዜማውም፣ የሐዘን እንጉርጉሮ ያለበት ነው። ምሳሌ እንውሰድ፦ “ጨርሰሽ ስትወጪ ከቡፌ ዳ’ላጋ፣ ጠብቂኝ እንዳልል፣ ቆመሽ መሐሙድ’ጋ፣ አገር ...