Pages

Sunday, September 17, 2017

የአራማጅነት ሀሁ…

‘አክቲቪዝም’ በአማርኛ ቁርጥ ትርጉም አልተገኘለትም። እንዲሁ በየዐውዱ "የለውጥ አራማጅነት"፣ "የመብቶች አቀንቃኝነት"፣ ወዘተ… ነው የሚባለው። የእንግሊዝኛ ቃሉን ግርድፍ ትርጉም ከወሰድን "ንቁ ተሳታፊ" ከሚለው የሰፋ ትርጉም የለውም። በኢትዮጵያ ቃሉ በተደጋጋሚ መደመጥ የጀመረውና ራሳቸውን ‘አክቲቪስት’ ብለው የሚጠሩ ሰዎች የተከሰቱት ከማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ማደግ ጋር ተያይዞ ነው። በተለምዶ፣ ቃሉ በጥቅሉ ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚያደርጉ እና የሚወክሉት ድርጅት የሌላቸውን ግለሰቦች በሙሉ ለመግለጽ እየዋለ ነው። እዚህ ጽሑፍ ላይ የምጠቀምበት ገላጭ ሆኖ ያገኘሁትን "አራማጅነት" የሚለውን ቃል ነው።

አራማጅነት ምንድን ነው? 

አራማጅነት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና/ወይም አካባቢያዊ ለውጦችን ለማምጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። አራማጅነት የአጭር ግዜ ፕሮጀክት ወይም ዘላቂ ንቅናቄ ሊሆን ይችላል። አንድ ጉዳይ ላይ ብቻ ያተኮረ ወይም ብዙ ጉዳዮችን ያቀፈም ሊሆን ይችላል። አራማጅነት በብዙኃኑ ተቀባይነት ያለውን አንድ ጉዳይ በመንግሥት ተቀባይነት እንዲያገኝ፤ ወይም በመንግሥት ዕውቅና ያለውን ጉዳይ በብዙኃኑም ተቀባይነት እንዲያገኝ፤ ወይም በብዙኃኑም፣ በመንግሥትም ተቀባይነት እና ዕውቅና የሌለውን ጉዳይ በሁለቱም ተቀባይነት እና ዕውቅና እንዲያገኝ ለማድረግ ሊሆን ይችላል። አራማጅነት በብዛት ከተገለሉ ሕዳጣን ወይም ከተጨቆኑ ብዙኃን መሐል በወጡ አራማጆች የሚደረግ የመብት/የጥበቃ ንቅናቄ ነው።

የአራማጅነት ስኬት እንደመነሻው ነው የሚለካው። አንዳንዴ የተነሳውን ሐሳብ የተደራጁ ሲቪል ማኅበረሰቦች ወይም የፖለቲካ ማኅበሮች አጀንዳዬ ብለው ሲይዙት ከአራማጆች እጅ ሊወጣ ይችላል። ሌላ ግዜ ደግሞ የተጠየቀውን መብት/ጥበቃ የሚያጎናፅፍ አዋጅ ሲወጣ ሊቆም ይችላል። አንዳንዴ ደግሞ የወጣው አዋጅ እና መመሪያ አፈፃፀምን እየተከታተለ፣ የተፈለገው ማኅበራዊ የግንዛቤ ለውጥ እስኪመጣ ሊቀጥል ይችላል። እንዲሁም ቀድሞ የወጣ አዋጅ ወይም የተዘረጋ ስርዓት እስኪሻር ወይም በሌላ እስኪተካ የሚደረግ አራማጅነትም አለ። በተግባር ደረጃ የማድረግ ወይም ያለማድረግ (ሌሎችንም እንዲያደርግ ወይም እንፋያደርጉ የማግባበት) ንቅናቄ ነው።

አራማጅነት የዓለማችን ዘመናዊ ባሕል ሆኗል ማለት ይቻላል። ቃሉ በዚህ ፖለቲካዊ ይዘቱ ከተመዘገበ የመቶ ዓመት ያክል ዕድሜ ይሆነዋል። ከጊዜ ግዜ እያደገ መጥቶ ዛሬ የበይነመረብ (ኢንተርኔት) ዘመን ላይ የእያንዳንዱን ጓዳ የሚያንኳኳበት ዕድል አግኝቷል።

አራማጆች ለጋዜጦች በመጻፍ፣ በራሪ ወረቀቶችን በመበተን፣ ፊርማዎችን በማሰባሰብ፣ የአዳራሽ ስብሰባዎችን እና ንግግሮችን በማካሔድ፣ በኪነ (ሥነ) ጥበብ ሥራዎች በመግለጽ፣ ብዙኃንን ያሳተፈ የእግር መንገድ ዘመቻ በማድረግ፣ ለቀናት ያክል ድንኳን በመደኮን፣ በሰላማዊ ሰልፎች፣ በአድማዎች፣ በማዕቀቦች፣ ያልተፈለገውን ተግባር (ወይም ሌላ አትኩሮትን የሚስብ) የለት ተለት ተግባርን በማስተጓጎል፣ ወዘተ… የሚዲያ፣ የኢኮኖሚ፣ የባሕል፣ የፖለቲካ፣ የአካባቢያዊ እና ሌሎችም ተፅዕኖዎችን በመፍጠር ጉዳዩ መጀመሪያ ትኩረት እንዲስብ፣ ቀጥሎ ወደ ተግባራዊ ለውጥ ጉዞ እንዲጀመር የሚያስገድዱ ንቅናቄዎችን ይፈጥራሉ።

የኢትዮጵያውያን አራማጆች የተለመዱ ስህተቶች

በአገራችን አራማጅነት ከሆነው ይልቅ ያልሆነው ነው እንደአራማጅነት የሚቆጠረው ማለት ይቻላል። ለዚህ ምክንያት ሊሆን የሚችሉት የዳበረ የፖለቲካ ባሕል አለመኖሩ፣ የሲቪል ማኅበራት ቁጥር እና ተዳራሽነት ውሱን መሆኑ፣ የሐሳብ ነጻነት አለመከበሩ እና የመሳሰሉት ናቸው። የሚከተሉት ነጥቦች ዋና ዋናዎቹን ችግሮች ነቅሰው ያወጣሉ ብዬ እገምታለሁ።

Friday, September 15, 2017

How Much Do You Know About (mis)use of Ethiopia’s Anti-terrorism Proclamation?

Many often fail to imagine the subjective consequences of public actions. Here I want you to imagine personal crises with the numbers I will follow.

As a living victim of (mis)use of the Anti-terrorism Proclamation (ATP) in Ethiopia, I face a heartbreaking judgement oftentimes from ordinary citizens who knew that I was once charged of the ATP. They say, "you must have been involved in ‘something’ that got you suspected of terrorism". I find it difficult to explain how the ATP became a tool to stifle dissent in the country. This, however, is not my personal problem, it is a challenge of many others; nor it is the only problem, there are a lot of sufferings it caused. Once someone is charged of Ethiopia’s ATP, her/his life will turn upside down. It is mostly difficult for ex-suspect/convict of the infamous ATP to get one’s job back nor to find a new one; the blank space in one’s CV sounds to employers like “don’t give them the job, otherwise you will draw government spies’ attention towards your company”. Past suspects/convicts of ATP will remain ‘usual suspect’ anytime anti-government protests erupt. 

How many people were prosecuted of the ATP in Ethiopia? How many fled the country in fear of persecution? How many families suffered the consequences? A lot of individual stories have been reported about the ATP and its (mis)use but no significant research has been conducted uncovering the entire (mis)application of it. Who are the main targets of the ATP? How many people have so far suffered direct consequence of this – apparently – abusive Proclamation?

They say "when life gives you lemons, make lemonade"; one of my co-defendants in the ATP charges pressed against us, Zelalem Kibret, used his experience in jail to study the (mis)use of the Proclamation and developed a research on the topic as a visiting scholar in New York university, later.

Zelalem explored the [mis]application of Ethiopia’s ATP under 123 cases which involved more than 985 defendants in a research titled as “The Terrorism of ‘Counterterrorism’: The Use and Abuse of Anti-Terrorism Law, the Case of Ethiopia”. Zelalem begins by explaining the global definition gap to the term “terrorism” which gave the chance for States fill it in a definition they like; which, evidently, is helpful for their manipulation. This reminds me of Abraha Desta, the current chairman of an opposition political party named Arena Tigray and was ex-defendant of a terrorism charge in Ethiopia. When he was asked if he pleaded guilty or not by the Federal High Court, he responded by defining the term terrorism in a very simplest and clear way. He said, “terrorism is harassing civilians to meet a political goal” and continued by saying, “accordingly, it is only the government in Ethiopia itself that is terrorizing civilians for control of political power, I’m not.” I needed to recall this definition of Abraha here because I want to tell readers of this note in advance that the objective of the writing (and reference of the study) isn’t condemning counter terrorism movement but the abuse in the name of it.

You Might “unknowingly” Become a Terrorist

Zelalem explores the cases at his hand and explains that "the ATP mainly raises rabble on two core notions, an overbroad substantive conception of terrorism and an overblown executive power camouflaged as enabling legal procedures." Starting from the definition part, ATP defined “terrorism acts” without mentioning what “terrorism” is. The definition of “terrorism acts” in Ethiopia included “criminalization of the broadly listed acts like, rendering support to terrorism—knowingly or unknowingly—publications that rendered support to groups designated as terrorists—knowingly or unknowingly—individuals who knowingly and unknowingly omits to cooperation with the state in its effort of countering terrorism, and other unqualified and vaguely provided acts.”
Moreover, “the law stipulates overextended executive powers to the police, the intelligence and the public prosecutor is also a further criticism on the substance of the ATP.” This, added to the fact that all the security, intelligence and public prosecutor apparatuses of Ethiopia being entirely controlled in a single political group, made the result very abusive to all kinds of dissenting voices and movements.

Wednesday, September 6, 2017

ኢትዮጵያ ያለ«ኢትዮጵያዊነት» ልትኖር አትችልምን?

በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በጣም ተወዳጁ ኤፍኤም ሬዲዮ ሸገር ነው ቢባል የሚያጣላን አይመስለኝም። ሸገር መፈክሩ "ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር" የሚል ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፖለቲከኞችም ይህንኑ መፈክር የንግግራቸው ማሳረጊያ ዓረፍተ ነገር እያደረጉት ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ከመግለጫዎቹ ግርጌ “ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር” የሚል ዓረፍተ ነገር ያስቀምጣል። አዲሱ በእነሰይፉ ፋንታሁን እና ሠራዊት ፍቅሬ… የተከፈተው ኢትዮ ኤፍኤም ሬዲዮ "ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ" የሚል መፈክር ይዞ መጥቷል። በቅርብ ጌዜ ከተከፈቱት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አንዱ - ጄቲቪ - መፈክሩ "ኢትዮጵያዊነት መልካምነት" የሚል ነው። "ኢትዮጵያ" የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ዘፈን የአገር ውስጥ ሽያጭ ሪከርድ ሰብሯል። የሐበሻ ቢራ ማስታወቂያ ‘ኢትዮጵያዊነት’ የሚለውን ቃል ማዕከል ያደረገ እና ስለኢትዮጵያ ‘ገናና ታሪክ’ የሚያወሳ ዓይነት ነው። ሐበሻ ቢራ ገና ከመተዋወቁ ገበያው ደርቶለት የነበረውን ዋልያ ተቀናቅኖ ወጣ። ገበያው ከማስታወቂያው ነው ብለው ይመስላል፣ ሌሎቹም ቢራዎች ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው ማስታወቂያዎችን ይዘው ብቅ-ብቅ ማለት ጀመረዋል። የቴሌቪዥን ትዕይንቶች፣ የግጥም ምሽቶች፣ ሌሎችም የጥበብ ሥራዎች ከመቼውም ግዜ በላይ ‘ኢትዮጵያዊነት’ን እያንቆለጳጰሱ ነው። በምላሹም ቀላል የማይባል ጭብጨባ ይቀበላሉ።

እነዚህ ሁሉ በተለምዶ "ኢትዮጵያዊነት" የሚባለው የአንድነት ኃይሉ ፖለቲካዊ ንቅናቄ ማኅበራዊ መገለጫዎች ይመስላሉ። ነገር ግን እነዚህ ይፋዊ መፈክሮች “ንቅናቄው እያደገ መምጣቱን ያረጋግጣሉ ወይስ፣ የዘውግ ፖለቲካ ንቅናቄ እና ዕድገት ድንጋጤ የፈጠረው ግብረ መልስ ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ማንሳት አስፈላጊ ነው። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ለዚህ ጥያቄ የግሌን መልስ በመስጠት ብቻ አይወሰንም፡፡ ይልቁንም፣ “ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ተቆርቋሪ ነን የምንለው ሰዎች እውን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ስሜት እና ፍላጎት ታማኝ ነን ወይ?” የሚለውንም ጥያቄ እግረ መንገዴን አንስቼ ለውይይት ክፍት ማድረግ ነው፡፡

ግን፣ ግን ‘ኢትዮጵያዊነት’ ራሱ ምንድን ነው? 

“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” ከሚለው መፈክር የምንረዳው ነገር ቢኖር ‘ኢትዮጵያዊነት’ መሠረቱ ኢትዮጵያ እንደ አንድ አገረ መንግሥት መቀጠል አለባት የሚለውን ቁምነገር ያነገበ መሆኑን ብቻ ነው፡፡ “እንዴት?” ለሚለው ጥያቄ ግን አንድ ወጥ መልስ ያለው አይመስልም፡፡

‘ኢትዮጵያዊነት’ ከሚለው ቃል በፊት ‘ኢትዮጵያኒዝም’ የሚለው የእንግሊዝኛ ዕኩያው-መሳይ በጥቅም ላይ ውሎ ነበር። የእኛው ‘ኢትዮጵያዊነት’ እና የአፈ እንግሊዞቹ ‘ኢትዮጵያኒዝም’ ግን ለየቅል ናቸው። ‘ኢትዮጵያኒዝም’ የተባለው ንቅናቄ የተጀመረው በ1880ዎቹ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ‘ኢትዮጵያ’ የሚለው መጠቀሱ፣ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ቄሱም፣ ምዕመኑም ጥቁር መሆኑ ነበር መነሻቸው። በወቅቱ ክርስትና የነጩ ዓለም ጭቆና መሣሪያ ስለነበር ቄስ መሆን የሚችለው ነጭ እንጂ ጥቁር አልነበረም። ጥቁሮች ለመብታቸው መቆም ሲጀምሩ፣ ከፊሉ ክርስትናቸውን በእስልምና ሲተኩ፣ ከፊሎቹ ደግሞ ‘ኢትዮጵያኒዝም’ የሚል ንቅናቄ ፈጥረው፣ ጥቁር የሚሰብክበት ‘የኢትዮጵያ’ የተባሉ ቤተ ክርስትያኖችን አቋቋሙ። ከዚያም የአድዋ ድል መከተሉ ለጥቁሮቹ ንቅናቄ ኃይል ስለሰጠው ከምዕራብ አገራት (በተለይም ከአሜሪካ) ወደ አፍሪካ፣ ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት ኢትዮጵያኒዝም ተስፋፍቶና ተሟሙቆ በአፓርታይድ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ብቻ 37ሺሕ ገደማ ‘ኢትዮጲያኒስት’ ቤተ ክርስቲያኖች ተፈጥረው ነበር።