(በፍቃዱ ዘ. ኃይሉ)
አምባገነናዊ
ስርዓቶች ግለሰብ፣ ፓርቲ፣ መንግሥት እና አገርን ለዜጎቻቸው እንደማይነጣጠሉ አስመስለው ያቀርባሉ። ግለሰቡን ከነካችሁ ፓርቲው ይፈርሳል፣ ፓርቲውን ከነካችሁ፣ መንግሥቱ ይፈርሳል፣ መንግሥቱን ከነካችሁ አገሩ ይፈርሳል። እውነት አላቸው። አምባገነኖች እና የአገዛዙ ጥቅመኞች ሕልውናቸውን ከአገሩ ሕልውና ጋር አስተሳስረው ነው የሚኖሩት። ኢሕአዴግ ከመውደቁ ትንሽ ሰሞን ቀደም ብሎ በአማርኛ ዝና ያገኘ አንድ የትግርኛ አባባል ነበር “ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትትረፍ።” በግለሰቦች እና አገዛዞች መተሳሰር ምክንያት ዜጎች አምባገነኖችን ለመጣል ሲታገሉ አገራቸውንም ራሳቸው ላይ ይማፍረስ ስጋት አላቸው። ስለዚህ አምባገነኖችን መታገል በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ነገር ግን የማይቻል አይደለም።
ይባስ
ብሎ፣ በአምባገነናዊ ስርዓቶች ውስጥ ግን ሥልጣን ላይ መውጫ እና ሥልጣን ላይ መሰንበቻው መንገድ ነውጥ ብቻ ነው። ባለ ፍፁም ሥልጣኑ - አምባገነኑ - በወደቀ ቁጥር፣ ቢያንስ በየትውልዱ ትርምስ ይኖራል። አጥኚዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ ላለፉት ሁለት መቶ ዓመታት፣ ትልቅ ጦርነት ያላየ ትውልድ የለም የሚሉት ለዚህ ነው።
መንግሥት
በግለሰብ እጅ ተጠልፎ እንዳይወድቅ ለማድረግ የተፈጠረው ሞዴል ማዲሰኒያን ሞዴል ይባላል። ከአሜሪካ መንግሥት መሥራቾች መካከል ጄምስ ማዲሰን በጻፈው ጽሑፍ ላይ የተመሠረተ ሞዴል ነው። ሞዴሉ፣ ቢያንስ እስካሁን ለብዙ ዴሞክራሲያዊ አገሮች ሠርቷል። የጀምስ ማዲሰን
ጽሑፍ እንዲህ ይላል፤ “ሰዎች መልዓክ ቢሆኑ ኖሮ፥ መንግሥታት አያስፈልጉም ነበር። ሰዎችን የሚገዟቸው መላዕክት ቢሆኑም ኖሮ፥ መንግሥታት ላይ ቁጥጥር መጣል አያስፈልግም ነበር። ሰዎችን ሰዎች በሚያስተዳድሩበት ሁኔታ መንግሥትን መቅረፅ፥ ከባድ ፈተና አለበት። መጀመሪያ ገዢው ተገዢዎቹን መቆጣጠር መቻል አለበት፤ ከዚያ ገዢው ራሱን እንዲገዛ ማስገደድ ያስፈልጋል።” ("ፌዴራሊስት ፔፐርስ 51")
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም የማዲሰንያንን ሞዴል ለመኮረጅ ሞክሯል። በመነባነብ እንደሚነገረው ሕግ አውጪ አለ (ፓርላማው)፣ ሕግ ተርጓሚ አለ (ፍርድ ቤቶችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ)፣ እንዲሁም አስፈፃሚ አካል አለ (ጠቅላይ ሚኒስቴሩ፣ ካቢኔው፣ የፀጥታ ኃይሉ፣ ወዘተ።) ነገር ግን ሁለቱ የመንግሥት ቅርንጫፎች የአስፈፃሚው አካል እስረኞች እንጂ ሚዛን ጠባቂዎች አይደሉም።
ሥልጣን በአንድ ግለሰብ እጅ ላይ ከተከማቸ፣ ግለሰቡ መልዓክ ቢሆን እንኳን አደገኛ ነው። የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምንም እንኳን ተቀዳሚ ዓላማው ለብሔረሰቦች ነጻነት (autonomy) መስጠት ቢሆንም፣ መሐል አገር የተከማቸውን ሥልጣንን ወደታች ማከፋፈል ሌላኛው ተጨማሪ ውጤቱ ነው። ስለሆነም ክልሎች ቀድሞ በማዕከላዊው መንግሥት እና ማዕከላዊውን መንግሥት በተቆጣጠረው አካል ተጠቃልሎ/ተከማችቶ የነበረው ሥልጣን በከፊል ተቀናንሷል። አልፎ ተርፎም ክልሎቹም የየራሳቸው ሕግ አውጪ፣ ተርጓሚ እና አስፈፃሚ አላቸው። ይሁን እንጂ ከሦስቱ የመንግሥት ቅርንጫፎቻቸው ውስጥ የአስፈፃሚው አካል ጡንቻ እዚያም ፈርጣማ ነው።
ስለዚህ፣ አስፈፃሚው ሲያሻው ሕግ እያስወጣ እና እያስሻረ፣ እንዲሁም እንደሚመቸው እያስተረጎመ ይገዛል። ነገር ግን የክልል አስፈፃሚ አካላትም ነጻነት እንዲሁ አለቃ አለበት፤ የፌዴራሉ አስፈፃሚ አካል የክልሎቹ የሥራ አስፈፃሚ አካላት ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ። ይህ በሕግ አግባብ መሠረት የለውም፤ ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲ አወቃቀሩ ለዚህ ይመቻል። የፌዴራሉ ሥራ አስፈፃሚ አካልም ቢሆን ከሌሎቹ የመንግሥት ቅርንጫፎች አንፃር ፈርጣማ ሁኖ ይታይ እንጂ ነፃ የሚመስለውን ያክል ነፃ አይደለም። ከሁሉም ሁሉም የመንግሥት ቅርንጫፎች በገዢው ፓርቲ ጫና ሥር ናቸው።
ገዢው ፓርቲውም፣ በተለይ በአሁኑ አካሔድ የሊቀ መንበሩ ጥላ የተጫነው ፓርቲ ነው። ምክንያቱም የአሁኒቱ የኢትዮጵያ ስርዓተ ፖለቲካ በገቢር አሃዳዊ ፓርቲ የሚመራው ነው። ኢሕአዴግ ውስጥ ትልቁ ሥልጣን የተከማቸው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውስጥ ነበር፤ የተማከለ ዴሞክራሲያዊነት ይሉት ነበር። የግንባሩ አባላትም ከፊል ሥልጣን ተክፈፋፍለው በሥራ አስፈፃሚያቸው የበላይነት ይመሩት ነበር። ኢሕአዴግ ፈርሶ በዳግም ውልደት ብልፅግና ፓርቲ ሆኖ ሲመጣ ግን ሥልጣንን ከሥራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ወደ ፓርቲው ፕሬዚደንት መዳፍ አውርዶታል።
ስለሆነም
ኢትዮጵያ ውስጥ “ሚዛንና ቁጥጥር” - አንደኛው የመንግሥት
ቅርንጫፍ ሌላኛው በሥልጣኑ እንዳይባልግ የሚቆጣጠርበት ሁኔታ - በነቢብ እንጂ በገቢር የለም። ይህንን ለመቅረፍ
የሚያስችል ዘላቂ የመፍትሔ ሐሳብም ሲቀርብ እምብዛም አይደመጥም። ተቃዋሚዎችም ቢሆኑ የትኩረታቸው ዋነኛ አቅጣጫ እንዲህ ዓይነት ስርዓት መዘርጋት ላይ አይደለም። በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊነት ላይ ተስፋ የሚያስቆርጠው፣ ዴሞክራሲያዊ አለመሆኗ ሳይሆን ለመሆን በቂ ጥረት የሌለ መሆኑ ላይ ነው። ለምሳሌ፣ “የአገራዊ ምክክር” ጅምር አለ። ብዙዎች የፖለቲካ ተዋናዮች ሒደቱ ገለልተኛ እና አካታች መሆኑን ስላላመኑ ራሳቸውን አግልለዋል። በተስፋ እየተሳተፉ ያሉትም ቢሆኑ ሥልጣን እንዴት ይገራ፣ እንዴት የአገሩን ሕልውና ከፓርቲው ሕልውና የፓርቲውን ከግለሰቡ ሕልውና እንነጥለው የሚለው ላይ አጀንዳ ሲወያዩ አይደመጡም።
ይህ
በእንዲህ እያለ፣ የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ እና የሚወስዷቸው ዋልታ ረገጥ ውሳኔዎች፣ የአሜሪካ የራሷ ቁጥጥር እና ሚዛን ደካማ ጎን እንዲጋለጥ አድርጓል። አሜሪካውያን እንደ አዲስ “ለካስ ያለ ፕሬዚዳንቱ ይሉኝታ
(restraint) አስፈፃሚውን አካል ከሥልጣኑ አልፎ እንዳይባልግ ማስገደጃ በቂ የቁጥጥር እና ሚዛን መጠበቂያ የለንም”
አስብሏቸዋል። እንግዲህ፣ በዴሞክራሲ ከሁለት መቶ ዓመት በላይ ልምድ ያላት አሜሪካ እንዲህ ያለ ፈተና ከገጠማት፣ የምዕተ ዓመታት አምባገነናዊነት ልምምድ ያላቸው ኢትዮጵያን የመሰሉ አምባገነናዊ አገራት ምን ያህል እንደሚፈተኑ መገመት አይቸግርም።
በኢትዮጵያ
የብሔርተኝነትን መካረር ለመግራት ፕሬዚደንታዊ ስርዓት፣ ከፓርላመንታዊ ስርዓት የተሻለ መፍትሔ ሊሆን ይችላል የሚል እምነት አለኝ። ግምቴ ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ ፖለቲከኞች ከአንድ ብሔረሰብ በላይ ተቀባይነት ካላገኙ የማሸነፍ ዕድል ስለማይኖራቸው፣ አቃፊ የሆነ የፖለቲካ ትርክት እና አማራጭ ይዘው ለመምጣት ስለሚገደዱ፣ ቀስበቀስ የተካረረ ብሔርተኝነት እየከሰመ እና እየተሸነፈ የሚመጣበት ዕድል ይኖራል የሚል ነው። ነገር ግን፣ ከታሪክ ተሞክሮ ፕሬዚደንታዊ ስርዓት ከፓርላመንታዊ ስርዓት ይልቅ ለአምባገነናዊነት ተጋላጭ ነው፤ ፕሬዚደንታዊ ስርዓቶች ከፓርላሜንታዊ ስርዓቶች አንፃር ብዙ አምባገነን ማፍራታቸው
በታሪክ
(empirically) ታይቷል።
በአንድ
በኩል፣ ፕሬዚደንታዊ ስርዓት ሲኖር፣ የፕሬዚደንቱ ፓርቲ ፓርላማው ውስጥ አብላጫ ድምፅ እንዲኖረው የሚያስገድድ ሁኔታ ስለሌለ፣ ፓርላማው በከፊል ጥርስ ያወጣል ተብሎ ይገመታል። ምክንያቱም የፕሬዚዳንቱ ሥልጣን የሚመነጨው ከመራጮች ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ፓርላማው ውስጥ አብላጫ መቀመጫ ካለው ፓርቲ ነው። ይህም፣ እንደፓርላመንታዊ ስርዓት ፓርላማው (ሕግ አውጪው) እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ሕግ አስፈፃሚው) ተመካክረው እንዳይጨቁኑ በማድረግ አምባገነንነትን መከላከል ያስችላል ተብሎ ሊገመት ይችላል። ነገር ግን እውነታው ከዚህ በተቃራኒው ነው። ፕሬዚዳንታዊ ስርዓት ለፕሬዚደንቱ የሚሰጠው ሥልጣን የሕግ አስፈፃሚ አካላትን (ፖሊስ፣ ደኅንነትን እና መከላከያ ኃይልን ሳይቀር) በበላይነት የመምራት ሥልጣን ስለሆነ ፓርላማውንም ይሁን ፍርድ ቤቱን ማንበርከክ ለፕሬዚዳንቱ ቀላል ነው የሚሆነው።
ከፕሬዚደንታዊ
ስርዓቶች አንፃር ፓርላመንታዊ ስርዓቶች አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን አምባገነኖችን ቢያፈሩም ቅሉ፣ ፓርላመንታዊ ስርዓቶችም ቢሆኑ አምባገነኖችን ከማፍራት ነፃ አይደሉም። በተለይ “የይስሙላ ምርጫ አምባገነንነት” በፓርላመንታዊ ስርዓቶች የበለጠ ሊከፋ ይችላል። ስለሆነም፣ ዋናው ጉዳይ በርካታ እና ጠንካራ የቁጥጥር እና ሚዛን ማነቆዎችን ማብዛት ነው። በተለይም፣ ከሦስቱ የመንግሥት ቅርንጫፎች ውጪ፣ ነጻ ሚዲያ እና ነጻ ሲቪል ማኅበረሰብ እንዲያብብ እና እንዲጎለብት የሚያደርግ ሕግ እና አሠራር ማኖር አራተኛ እና አምስተኛ የመንግሥት ሚዛን ጠባቂ እንዲኖር ያደርጋል።
“የኢትዮጵያ
አገራዊ ምክክር” - በፖለቲካ ልኂቃን
ዘንድ ተቀባይነት ኖረውም አልኖረውም - በመንግሥት እስከ
ጥግ እየተገፋ ነው። መንግሥት ይፈልጋቸዋል ከተባሉ ተጠባቂ ውጤቶች መካከል አንደኛው እና ዋነኛው ስርዓቱን ወደ ፕሬዚዳንታዊ መቀየር ነው። ይህ ከሆነ፣ የፕሬዚዳንቱን የሥልጣን ዘመን ብቻ ሳይሆን፣ ሥልጣኑን የሚገዳደሩ ሕግ አውጪዎች እና ሕግ አስፈፃሚዎች እንዲኖሩ የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀቦች እንዲኖሩ መረባረብ ያስፈልጋል። ይህ ካልተደረገ በስተቀር ውጤቱ ከድጡ ወደ ማጡ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው።
አምባገነናዊ
መንግሥታት ከምንም በላይ ነጻ ሚዲያ እና ነጻ ሲቪል ማኅበረሰብ ይጠላሉ። ምክንያቱም ሥልጣናቸውን በአግባቡ መጠቀም አለመጠቀማቸውን ይገመግሙባቸዋል። ዜጎቻቸውን ያነቁባቸዋል። አምባገነኖች ነጻ ሚዲያ እና ሲቪል ማኅበረሰብ ይጥሉ እንጂ ራሳቸው የሚጠቀሙባቸው ሚዲያዎች ሁሌም ይኖሯቸዋል። እነዚህን ሚዲያዎች እንደ ልሳን ይጠቀሙባቸዋል። ሚዲያዎቹ የነርሱን ገጽታ እንዲገነቡ፣ የተቀናቃኞቻቸውን ደግሞ እንዲያጠለሹ ተደርገው ይቀረፃሉ። የግለሰቦችን እና የፓርቲዎችን ሥልጣን ለመገደብ ሚዲያ ላይ ያላቸውን ሥልጣን መገደብ አንዱ መንገድ ነው። ለምሳሌ፣ "በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ ሚዲያዎች ላይ ያላቸው ሥልጣን ምን ያህል መሆን አለበት?" የሚለው ለክርክር መቅረብ አለበት። "በመንግሥት በጀት የሚተዳደር ሚዲያ መኖርስ አለበት ወይ?" የሚለውም ጥያቄ መነሳት አለበት።
አምባገነኖች ጥገኛ ሚዲያን፣ ጥገኛ ሲቪል ማኅበረሰብን፣ ጥገኛ የኢኮኖሚ መዋቅሮችን፣ እና ክፍተት ያላቸውን ሕጎች እና ተቋማትን እንዲሁም የፀጥታ መዋቅር ላይ ያላቸውን የበላይ አዛዥነት፣ ሥልጣን ላይ ለመሰንበቻነት፣ የራሳቸውን ሕልውና ከአገሩ ሕልውና ጋር ለማቆራኘት ይጠቀሙበታል። እነዚህ ነገሮች ላይ ያላቸውን የቁጥጥር አቅም መበጣጠስ ካልተቻለ፣ አምባገነንነትን መከላከል አይቻልም ብቻ ሳይሆን፣ የአምባገነኖቹ ሕልውና የአገሩ ሕልውናም ሊሆን ይችላል። ነጻ እና ንቁ ሚዲያ እና ሲቪል ማኅበረሰብ የሌለበት ፖለቲካዊ ምኅዳርም ነጻ እና ገለልተኛ የሕግ አውጪ እና የሕግ ተርጓሚ አካል ይኖረዋል ብሎ መጠበቅ ይቸግራል።
ኢትዮጵያውያን ብዙ ትግሎች ታግለዋል፣ ብዙ ለውጦች አምጥተዋል። ሆኖም፣ ትግላቸው አምባገነኖችን ለመጣል እንጂ አምባገነንትን ለመጣል ሊሆንላቸው አልቻለም። ምክንያቱም ሥልጣንን መግራት አልቻሉም። ሥልጣንን መግራት የሚቻለው፣ የትልቁ ባለሥልጣን፣ የገዢው ፓርቲ፣ የሥራ አስፈፃሚው የመንግሥት ቅርንጫፍ ሲገደቡ እና ሕግ አውጪው እና ሕግ ተርጓሚው አካል ከሥራ አስፈፃሚው አካል ጫና ነፃ ወጥተው ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ ሲችሉ ነው። ምናልባት ያኔ የባለገ ባለሥልጣንን ማውረድ ቀላል ይሆናል ብቻ ሳይሆን፣ የእርሱ ጦስ ለንፁህ ብዙኃን እንዳይደርስ ማደረግ ይቻላል።
Thank you for writing this deeply important and timely piece. As an Ethiopian who cares deeply about our country's future, your reflection on the Madisonian model touched me profoundly.
ReplyDeleteA few months ago, I had the opportunity to visit the museum in Philadelphia where the U.S. Founding Fathers debated, struggled, and finally agreed on the foundations of a democratic state. Standing in the room where the Constitution was debated, I couldn’t hold back my tears. I felt a deep ache for my own country — a nation rich in history, culture, and courage, but still striving to build a system that truly serves the people. Ethiopia, the land of ancient empires, of unbroken independence, of sacred traditions and resilient people — yet still grappling to build a functioning system. My heart grew heavy as I thought of how our ancestors built one of the earliest organized states in the world, stood as a beacon of sovereignty, and preserved a civilization rich in culture, spirituality, and wisdom — and yet today, we still struggle to form a functioning, inclusive government.
We, a people who once rivaled the powers of the ancient world, now wrestle with the basics of governance. We who protected our independence with blood and prayer still struggle to protect our people's basic rights. We have churches and mosques older than some modern nations, yet still lack institutions that deliver justice and dignity. We who possess centuries of traditional medicine and an abundance of medicinal flora still suffer from curable diseases. We are a nation of poets and prophets, of music and fasting, of generosity and honor — and yet, we continue to repeat cycles of broken promises, fragile peace, and power that corrupts instead of heals.
You are absolutely right in arguing that revolutions alone do not build democracy. In Ethiopia, we have seen multiple regimes fall — often with the hope that things would finally improve — only for the next leaders to repeat the same patterns of authoritarianism. The problem isn’t just about individual leaders; it's about the absence of strong, self-regulating institutions — the very thing James Madison understood so well.
Madison’s wisdom speaks directly to our reality. As he wrote in Federalist No. 51: "If men were angels, no government would be necessary. If angels were to govern men, neither external nor internal controls on government would be necessary."
He recognized that human beings, no matter how well-intentioned, are susceptible to ambition, corruption, and the abuse of power. That’s why a real democracy requires more than elections and slogans. It needs a carefully designed structure, where power is divided, balanced, and checked — not to weaken government, but to protect freedom.
For Ethiopia to move forward, we need to stop hoping for angelic leaders and start building Madisonian systems: constitutional limits, judicial independence, separation of powers, protection for minorities, and mechanisms preventing any group from controlling everything. Only then can we have a democracy that endures beyond personalities and parties.
Your article is a call to action. Let’s not waste this moment in our history. Let’s plant the seeds of real constitutionalism and real power for all Ethiopians for our generation and beyond.
ኢትዮጵያውያን ብዙ ትግሎች ታግለዋል፣ ብዙ ለውጦች አምጥተዋል። ሆኖም፣ ትግላቸው አምባገነኖችን ለመጣል እንጂ አምባገነንትን ለመጣል ሊሆንላቸው አልቻለም።
ReplyDelete