Skip to main content

የባለፀጋዋን አገር ዜጋ፤ አቶ ድህነትን እናስተዋውቅዎ


ከዕለታት አንድ ቀን ከምሣ መልስ ቡና የምጠጣበት ካፌ ተሰይሜያለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የአዲስ አበባ መስተዳደር ፕሮግራም ይተላለፋል፡፡ ፕሮግራም አቅራቢያዋ በእኛ ቲቪ ያልተለመደ ዓይነት ፕሮግራም እያቀረበች ነው፡፡ አንዷ መምህርት ትናገራለች ‹‹ልጆቹ ራሳቸውን ይስታሉ›› አለች፡፡ ልጆቹ ያለቻቸው እሷ የምታስተምርበት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎችን ነው፡፡

‹‹እናነሳቸውና ካፌ ወስደን ውሃ አጠጥተን፣ ዳቦ አብልተን ስንለቃቸው ደህና ይሆናሉ፤›› አለች መምህርቷ፡፡ ‹‹በኋላ ላይ ሲደጋገምብን ጠይቀናቸው- ለካስ የሚወድቁት ምግብ ከበሉ ሁለት ሦስት ቀን እየሆናቸው ነው፡፡››

ያንን ፕሮግራም ተመልክተው ከእንባቸው ጋር ያልታገሉ ሰዎች አልነበሩም፡፡ ሕፃናቱ በተለያዩ ምክንያቶች ከወላጆቸቸው የተነጠሉ ሲሆኑ፣ ያልተነጠሉትም ቢሆኑ ቤተሰቦቻቸው በየቀኑ የመመገብ አቅም የሌላቸው ነበሩ፡፡ የኋላ ኋላ በደረሰኝ መረጃ ያንን ፕሮግራም ያቀረበችው ጋዜጠኛ ‹‹በመርዶ ነጋሪነት›› ከአለቆቿ ተግሳፅ ደርሶባታል፡፡

- - -

ኢቴቪ ጫወታ አማረልኝ ብሎ ያቀረባቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ ኮሌጅ ዘልቀው ዲግሪ እንደጨበጡ ተናግረዋል፡፡ አሁን ግን በኮብል ስቶን ጠረባ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ ኢቴቪ ይሄንን ‹‹ሥራ ፈጠራ›› ብሎታል፡፡ በሥራ ፈጠራና በሥራ አለመናቅ በኩል መስመር አለ፡፡ እነዚህ የተማሩ ኃይሎች፣ የፈለገ ሥራ ባይንቁ እንኳን የተማረ ኃይል እጥረት አለባት የምትባለው አገር ውስጥ ምናልባትም ከዚያ ውጪ ሌላ የሥራ አማራጭ የሌላቸውን ሥራ እየተሻሙ ነው፣ በልተው ለማደር፡፡

- - -

ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ፕሮፌሰር መስፍን መወያያ ንግግር አቅርበው ነበር፡፡ ከታዳሚዎቹ አንዱ ‹‹ማስተርስ አለኝ፤›› አለ፡፡ ‹‹ነገር ግን ሥራ አጥቼ በስንት መከራ አሁን አንድ ሺህ ከምናምን ደሞዝ እየበላሁ ነው፡፡ ነገር ግን የክፍለሃገር ልጅ በመሆኔና የቤት ኪራዩን ስለማልችለው ዛሬ አንዱ፣ ነገ አንዱ ጓደኛዬ ቤት እያደርኩ ነው፡፡ ለዚህ ኑሮ ያበቃኝን ኢሕአዴግ እግዚአብሔር ይስጠው›› አለ፡፡ ሪፖርተርም ይህ አይግረማችሁ ሲለን እንዲያውም ‹‹ዲግሪ ያላቸው ዜጎች የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነዋል›› የሚል ዜና አስነብቦናል፡፡

- - -

አንድ መምህር ጓደኛዬን አገኘሁት፡፡ በተለይም እዚህ ከተማ ውስጥ ቤተሰብ ስለሌላቸው መምህራን ባልደረቦቹ ሕይወት ይነግረኝ ገባ፡፡ መምህራኑ ርካሽ ከሚባለው ከት/ቤቱ ካፍቴሪያ ይመገባሉ፡፡ ነገር ግን ተቆራርጣ የምትደርሳቸው ደሞዛቸው በዕዳ ‹‹ኔጌቲቨ›› ትገባለች፡፡ አንዳንዴ ምህረት ይደረግላቸዋል፣ ባብዛኛው ግን ለሚቀጥለው ወር ይሸጋገርባቸዋል፡፡

ጓደኛዬ ሲነግረኝ ‹‹አንዱ፣ የደሞዝ ቀን ዕዳውን ሲያወራርድ 35 ሳንቲም ቀረው፡፡ እሷኑ ሲጃራ ገዝቶ አጨሰባት፡፡›› ይህንን የነገርኩት ሌላ ሰው ‹‹ሲጃራ በ35 ሳንቲም ማግኘቱም ጥሩ ነው፡፡›› አለኝ፡፡

- - -

ከሰሞኑ 43 ኢትዮጵያውያን በኮንቴይነር ታሽገው ወደደቡብ አፍሪካ በሕገወጥ መንገድ ሲሰደዱ የመሞታቸውን እና የቀብራቸውን ዜና ኢቴቪ አቅርቦት ነበር፡፡ የነዚህን ድህነት ያበረራቸው ኢትዮጵያውያን የቀብር ዜና ከማጠናቀቋ በፊት የኢቴቪዋ ጋዜጠኛ ‹‹በሃገሪቱ በተፈጠረው ምቹ የሥራ ሁኔታ ተበረታትተው ብዙ ወጣቶች ሥራ እየፈጠሩ ባለበት በዚህ ጊዜ ብዙ ገንዘብ እያወጡ ራሳቸውን ለአደጋ የሚያጋልጡት ወጣቶች….›› ሟቾቹን ወቀሰቻቸው፡፡

Comments

  1. ዝግንን የሚል ነገር ነው፡፡ ምን ይሻለን ይሆን

    ReplyDelete
  2. ከመዘግነን አልፎ የሚያስደነግጥ ነገር ነው! ብሎም የሚያሳፍር እና ልብ የሚሰብር ነው፡፡ ግን መፍትሄ የሌለው ችግር የለም፡ የተማረው የሰው ሃይል ቁጥር በዝቶ ካለው ፍላጎት ጋር ካልተመጣጠነ ትልቁ ችግር ይሄ ነው፡፡ እውነት ነው ብዙ በዲግሪ እና በማስተርስ የተመረቁ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ምሁራን በየጊዜው ይመረቃሉ ነገር ግን እነዚህ ምሁራን የሚቀበል መስሪያ ቤት እና ድርጅቶች በቂ አይደሉም፡፡ በቂ እንዲሆኑ አልተፈለገም ይሁን ለምን አልኖሩንም የሚለው ቀጣይ ዋና ችግር ነው! እንደው ከጀመርኩት አይቀር የግድ አንድ ሰው ተመረቀና ስራ ፈልጎ መቀጠር አለበት በሚለው ነጥብም ብዙ አልስማማም፡፡ እንዲያውም የስራ ፈጣሪ ነው መሆን ያለበት በሚለው የበለጠ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን በአጠቃላይ የትምህርት ፖሊሲያችን ስራ ፈጣሪነትን የሚያበረታታ እና የሚያሳድግ አይደለም እዚህ ጋር መስተካከያዎች ቢደረጉበት የተማረው ምሁር በትንሽ ነገር ተነስቶ ሀገር እስከመለወጥ ይደርሳል፣ ለሌላውም ይተርፋል፡፡
    ሌላው ነጥብ ደግሞ አዳዲስ የሚመሰረቱ ማንኛውንም አነስተኛ እና ጥቃቅን ድርጅቶችን በደምብ እራሳቸውን ችለው እስኪቋቋሙ ድረስ ማበረታታት እና መደገፍ ያስፈልጋል፡፡ ቀደም ባለው ስርአት እስከ 6 ወር አንድ አመት ድረስ ታክስ አይከፈልም ነበር አሁን ስርዓቱ ተቀይሯል፡ አይደለም ድርጅቱ እስኪቋቋም ቀርቶ ያለውንም ማፈናፈን ያልቻለ አሰራር ነው የተመሰረተው ነገር ግን ማስተካከያ ቢደረግበት የተሻለ ውጤት ያመጣል፣ አልፎ ተርፎም ቅድም ከላይ የተነሱትን የምሁራን ጉዳይ በቂ መልስ ይሰጣል፡፡ እርግጠኛ ያልሆንኩት ግን የሰማሁት፡ የቻይና መንግስስት አዲስ ለሚመሰረቱ ትናንሽ ድርጅቶች በተቻለው መጠን ያግዛል፡፡ አንድ ቻይናዊ ድርጅት መክፈት ቢፈልግ የሚያስፈልገውን ካፒታል እና አትራፊ ነው አይደለም የሚለው ታይቶ መንግስት ጣልቃ ገብቶ በጋራ ባለቤትነት ወይም በፐርሰንት ተካፍሎ ያስተዳድራል፡፡ በዚህ ባለቤቱም ተጠቀመ፣ መንግስት ተጠቀመ፣ ሃገር ተጠቀመ ማለት ነው! አሁን ግን በትክክል መንግስት ከቅሚያ ያልተናነሰ ስራ ነው እየተሰራ ያለው፡፡
    ምነው ከነቻይናና ህንድ እንደዚህ እንደዚህ አይነት ሃሳቦችን ከመውሰድ ነጻነትን ማፈኛ መሳሪያ መግዛት በለጠባቸው???

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

The "Corridor Development" is a Façade of the Prosperity Party

Befekadu Hailu I have seen a news report claiming that 40% of central Addis Ababa will be demolished for the corridor development; I am not able to confirm the validity of the news but it sounds real to me given the size of massive operations in the demolition of old neighborhoods and construction of bike lanes, green areas, and glittering street lights. I like to see some beauty added to my city but cannot help mourning the slow death of it too. Addis Ababa was already in a huge crisis of housing and the demolition of houses is exacerbating it. Apparently, Prime Minister Abiy Ahmed is eager to showcase his vision of prosperity by demonstrating how fast his administration can do magic by beautifying the front sides of the streets with lights, new pavements, and painted fences ("to fake it until he makes it" in my friend's words). Therefore, he and his party do not care about the miserable human stories behind the scenes and they will harass you if you tell it (Azeb Woku...

መጽሐፍ የሚወጣው፣ የተዋነይ ዘ ጎንጅ 5 መሥመር ቅኔ

ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል። “የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።” (ተዋነይ ዘ ጎንጅ። ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ) ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን ...

የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ

በፍቃዱ ዘ . ኃይሉ “የአዲስ አበባ ብሔርተኝነት” ቢኖር ኖሮ መሪው ልጅ ሚካኤል ይሆን ነበር። አሁን አሁን እሱ ስለ አዲስ አበባ የዘፈናቸውን ዘፈኖች ቁጥር ራሱ በትክክል መቁጠር ይቸግረኛል። ለአዲስ አበባ ከተዘፈኑ ዘፈኖቹ ውጪም በየዘፈኑ ውስጥ የሚጨማምራቸው መልዕክቶች በራሳቸው መወድሰ አዲስ አበባ ናቸው። ለምሳሌ፣ በቅርቡ በለቀቀው ‘አዲስ አራዳ’ በተሰኘው አልበሙ ውስጥ ‘የድሬ ልጅ’ የሚል ዘፈን አለው። ዘፈኑ የተዘጋጀው ያው የአዲስ አበባ እህት ተደርጋ የምትቆጠረውን ድሬ ዳዋን ለማወደስ ነበር። ልጅ ሚካኤል ግን የአዲስ አበባ ፍቅሩ ያመልጠውና የሚከተለውን ያቀነቅናል፦ “መጣልሽ በሏት፣ ድሬ ድረስ፣  ከአዱ ገነት፣ ከሸገር፣ ከአዲስ ደረሰ፣... የሸገር ልጅ አራዳ ነው፣ ሰው አክባሪ፣ ሰው ወዳዱ፣ ቀላጅና ተረበኛ፣ ፍቅር ይዞ የሚተኛ፣ ‘አለው’ የለ፣ ‘የለው’ የለ፣ ከሁሉ ጋ፣ ግባ ጀባ...፤” ፤ ልጅ ሚካኤል በዚህ አልበሙ ብቻ አዲስ አበባን የሚያውድሰባቸው ሌሎችም ዘፈኖች አሉ፤ ‘ አዲስ አራዳ ’ የሚለው የአልበሙ መጠሪያ እና ‘ሸገር’ የሚሉት ዘፈኖቹ ዋነኞቹ ናቸው። ታዲያ እንዲህ በአዲስ አበባ ፍቅር የሚቃጠለው ልጅ ሚካኤል "ሊነግረን የሚፈልገው ምንድን ነው?" የሚለው ጥያቄ ደጋግሞ ይመጣብኛል። ይህ የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ ምንነትን ለመረዳት የሚጥር ፖለቲካዊ መጣጥፍ ነው። ‘አዲሱ አራዳ’ ማነው? በዚህ ዘፈኑ በብዙዎቻችን ዕድሜ የትዝታ ማኅደር ውስጥ የሚገኙ ነገር ግን በአዲስ አበባ ልማት ሥም የፈረሱ እና እየተረሱ ያሉ ሰፈሮችን ሥም ያነሳሳል። ዘፈኑ በግጥሙም በዜማውም፣ የሐዘን እንጉርጉሮ ያለበት ነው። ምሳሌ እንውሰድ፦ “ጨርሰሽ ስትወጪ ከቡፌ ዳ’ላጋ፣ ጠብቂኝ እንዳልል፣ ቆመሽ መሐሙድ’ጋ፣ አገር ...