Pages

Thursday, November 15, 2018

Understanding Privileges

[This piece is posted on 'Ekool Ethiopia' in Amharic.]

Some of my Facebook friends make fun of other Facebook users for not being stylish enough like them, for not knowing Amharic/English the way the formers do, for not being ‘Arada’ enough and for being comparatively ‘Fara’. They ridicule the way the formers pose for a photo and also the captions they use when they post their photographs on social media. The terms ‘Arada’ and ‘Fara’ are both coined by the city dwellers in Ethiopia and ‘Arada’ is a title given to the “cool”, “cheer leading”, “stylish” people while ‘Fara’ is a label against those who are oppositely perceived. However, the term ‘Fara’ is mostly applied to refer to those people who were raised in rural areas and those who are desperately struggling to urbanize themselves (or trying to look like one). The division and categorization gets on Facebook from the ground. ‘The Aradas’ consider themselves as superior to ‘the Faras’ and think they deserve better treatment (megalothymia, as Fukuyama calls it) than those of ‘the Faras’. Even worse, they think they earned Arada-being. In this piece, I argue otherwise.

What about your privileges?

It is ironical that it is easier for everyone to understand one's under-privileges but not privileges. Human societies of our planet are built in multiple and complex hierarchies where everyone despises being at the bottom but never minds being on top. As it appears to be, at this time and in the most commonly agreed standards, whites are more privileged than blacks, men are more privileged than women, the rich are more privileged than the poor, the urbanite are more privileged than the rural dwelling, the able-bodied are more privileged than the disabled, the educated than the illiterate and the list goes on. Consequently, in our global social system, the able-bodied, educated rich white men who live in urbanized neighborhoods are most privileged people while the disabled, illiterate poor black women who live in rural areas are the most underprivileged. However, failing to understand and/or recognize the role of privileges in our lives do much more damage than the social hierarchies that existed among us. It is dangerous because we cannot be working to make adjustments if we don’t understand it.

Saturday, November 10, 2018

ምርጫ፦ ቄሮ ‘መንግሥት’ ይሁን ‘ፅንፈኛ’?

በቄሮ ምንነት እና "ድርጊቶች" ላይ በርካታ ውዝግቦች እየተነሱ ነው። ውዝግቦቹ የሚነሱት በሁለት ፅንፎች ነው፦ ፩ኛው ፅንፍ ያሉት ሰዎች "ቄሮ ቅዱስ ነው" ሲሉ፣ ፪ኛው ፅንፍ ያሉት  ሰዎች ደግሞ "ቄሮ እርኩስ ነው" ይላሉ። እኔ ደግሞ ቄሮ እኛ ነህ የምንለውን ይሆናል ባይ ነኝ።

እንደኔ እንደኔ የውዝግቡ ሁሉ መንስዔ የቄሮን ምንነት እና የንቅናቄውን ዓይነት፣ እንዲሁም "የትግሉን" ወይም ደግሞ "የድሉን" ባለቤት ካለመረዳት የመጣ ነገር ይሆን ይሆናል በማለት ነው ይህንን ጽሑፍ ለአማራጭ አስረጅነት ያዘጋጀሁት። እግረመንገዴንም ለውዝግቡም ይሁን ለውዝግቡ መንስዔ የሆኑ ተቃርኖዎችን እዳስሳለሁ። ዓላማዬ ከፅንፉ እና ከፅንፉ ወዲህ ዓለም እንዳለ ለማሳየት እንጂ መሞከር ብቻ ሳይሆን ፍረጃችን ተፅዕኖ እንዳለው ማስታወስም ጭምር ነው።

ቄሮ - ሥያሜው ምን ይነግረናል?

'ቄሮ' ቃሉ 'ያላገባ፣ ያልወለደ' ወጣትን ይወክላል። ነገር ግን ወጣት የሚለውን ቃል የሚተኩ ሌሎች የኦሮምኛ ቃላት አሉ። እነዚህም 'ደርደሩማ'፣ 'ደርገጌሳ' እና 'ጎሮምሳ' የሚሉት ቃላት ምሳሌ ይሆናሉ። ቄሮ የሚለው ቃል ምንጩ 'ቄረንሳ' ከሚለው እና ነብር የሚል ትርጉም ካለው ቃል የተቀዳ እንደሆነ ይነገራል። ስለዚህ ቄሮ ማለት እንደነብር ያለ ብርቱ ወጣት ማለት ነው፣ ማለት እንችላለን። ይሁን እንጂ አሁን በተለይ በኦሮሞ ፖለቲከኞች ዘንድ 'ቄሮ የሚለው ቃል ፍቺ 'አብዮተኛ ወጣት' የሚል ትርጉም አለው።

"የቄሮ ንቅናቄ" ውልደት እና ዕድገት

ቄሮ የሚለው ቃል የፖለቲካ መድረኩ ውስጥ የገባው እ.ኤ.አ. በ2011 የአረቡ አብዮት በፈነዳበት ወቅት ነበር። መቀመጫውን ዳያስፖራ ያደረገው ንቅናቄ ከዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ግንኙነት በመመሥረት 'ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ' የሚባል ኢመደበኛ ማኅበር ፈጠረ። የዚህ ማኅበር አባላት መረጃዎችን በኢሜይል እና በድረገጻቸው እየተለዋወጡ በርካታ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ቀጠሉ። ሥማቸው በይፋ የተነሳው ግን በ2006 የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር  ፕላንን ተከትሎ በተነሳው እና ዩኒቨርስቲዎችን ባዳረሰው የተቃውሞ ሰልፍ ወቅት ነው።

ከዚያ በኋላ የተጋጋለው የተቃውሞ ሰልፍ መላው ኦሮሚያን ሲያዳርስ በየአካባቢው ያሉ ወጣቶች ራሳቸውን ቄሮ ብለው መጥራት ጀመሩ። የመጀመሪያው የቄሮ አደራጅ የነበረው (qeerroo.org የተባለ) ድረአምባም ይሁን የፌስቡክ ገጹ አሁን እምብዛም ተከታታይ የላቸውም። ይልቁንም የወጣቶቹ ኅብረት መሪ ተደርጎ በዘልማድ የሚወሰደው የኦኤምኤን ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጃዋር መሐመድ ነው።

ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ ክልል፣ በየአካባቢው የሚነሱት ተቃውሞዎች ውስጥ የሚሳተፉ የተደራጁም ይሁኑ ያልተደራጁ ወጣቶች በሙሉ - ራሳቸውን ሲገልጹም ይሁን ሌሎች ሲገልጿቸው - ቄሮ በሚል ሥያሜ ሆነ። ቄሮ በዚህ አካሔድ በማንም ግለሰብ ወይም ቡድን ቁጥጥር ሥር ያልሆነ፣ ነጻ ነገር ግን በኦሮሙማ (ኦሮሞነት) የተሰባሰበ ኢመደበኛ ቡድን ሆነ። ይህ ማለት ግን ወጣቶቹ በፖለቲካ ፍልስፈፍናቸውም ይሁን ብስለታቸው፣ በኢትዮጵያ እና ኦሮሚያ ታሪክም ይሁን ፖለቲካ አረዳዳቸው ወጥ አቋም አላቸው ማለት አይደለም።

ይህ በእንዲህ እያለ በአማራ ክልል የነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ላይ የሚሳተፉትን ወጣቶች ሥም ለመስጠት ተሞከረ። 'ፋኖ' የሚለው ሥያሜ 'ቄሮ' ከሚለው ጎን ለጎን መጠቀሱ የተለመደ ነገር ሆነ። ያን ጊዜ በቄሮ ሥምም ሆነ በፋኖ ሥም የሚደረገው ነገር በሙሉ፣ ማዕከላዊ መንግሥቱን እስካስጨነቀ ድረስ "ትክክል" ነበር። ይሁን እንጂ መሬት ላይ "ቄሮ ነኝ" የሚሉትን ያክል፥ "ፋኖ ነኝ" የሚሉ ወጣቶች እምብዛም አልነበሩም። እንዲያውም 'ፋኖ' የግንቦት ሰባት ፈጠራ ነው የሚሉ የአማራ ብሔርተኞች ገጥመውኛል። ይሁንና የመንግሥት ባለሥልጣናት ሳይቀሩ አሁን ለምናየው የለውጥ አዝማሚያ አስተዋፅዖ ያበረከቱ ወጣቶችን ሲጠሩ "ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ…" እያሉ መጥራትን 'ፕሮቶኮል' አድርገውታል።

የትግሉ እንዲሁም የድሉ "ባለቤቶች"

የያኔዎቹ ኦሕዴድ እና ብአዴን ተባብሮ ትሕነግ ላይ ማበይ፥ ከወጣቶቹ አመፅ ባልተናነሰ (ወይም በበለጠ መልኩ) ኢሕአዴግን ነቀነቀው። የፓርቲዎቹ ከወጣቶቹ ጋር ያልተጻፈ መግባባት ላይ መድረስ ደግሞ የቀድሞውን ኢሕአዴግን ገድሎ፣ አዲሱን ኢሕአዴግ ወለደ። አሁን ከትሕነግ/ኢሕአዴግ ወደ ኦዴፓ/አዴፓ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ተሸጋግረናል። ይሁንና ገና አመፁ አልሰከነም። የትግሉ ባለቤት ተቃዋሚዎች በሙሉ፣ በተለይም አደባባይ የወጡት የኢትዮጵያ ወጣት አመፀኞች ናቸው፤ የድሉ ባለቤቶች ግን የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች፣ በተለይም ኦዴፓ እና አዴፓ ናቸው። ያለእነሱ ከቀድሞ አቋማቸው መቀልበስ፣ እንዲሁም ለማበር መወሰን በኢሕአዴግ ቤት አሁን ያለው ወደ ዴሞክራሲ የመሸጋገር ዕድል ፈፅሞ አይመጣም ነበር ብዬ እገምታለሁ።

ይሁንና ወጣቶቹ የልኂቃን ተቃዋሚዎችን ጥያቄ ከማስተጋባት ባሻገር ለእንዲህ ያለ ነፍስን አሳልፎ እስከመስጠት የሚደርስ ብሶት የዳረጋቸው ሥራ አጥነት እና 'የሪከግኒሽን' ጥያቄ መልስ ቢሰጠው ኖሮ፥ ድሉን የጋራ ድል አድርገን መቁጠር የምንችልበት ዕድል ይኖር ነበር።

አሁን ባለው ሁኔታ ብዙኃን ሥራ አጦች በየአደባባዩ በከፈሉት መስዋዕትነት፥ 'እነዚህ ሥራ ፈቶች ደግሞ መረበሽ ጀመሩ' እያሉ ይበሳጩባቸው የነበሩ ልኂቃን በአንድ በኩል፣ እንዲሁም በሌላ በኩል ደግሞ 'እስከመቼ እንዲህ ተዋርዳችሁ ትኖራላችሁ፣ ታግላችሁ ነጻ ውጡ እንጂ' እያሉ ሲቆሰቁሷቸው የነበሩ ልኂቃን ሥልጣን እየተቆጣጠሩ ሲመጡ ወጣቶቹ ችላ መባላቸው ሐቅ ነው።

ይህ ነገር ምናልባትም የትግሉ "ባለቤቶች" እና የድሉ "ባለቤቶች" ወይም "ተጠቃሚዎች" መካከል መቃቃር ሳያስከትል አይቀርም። ይህ ጉዳይ አዲስ ብሶት የሚወልድ መሆኑም የጊዜ ጉዳይ ነው።

"ጀግኖች" የነበሩ "ፅንፈኞች"
(የውክልና ጦርነት መሣሪያዎች)

በየአካባቢው በሥራ አጥነታቸው ምክንያት ዋጋ አጥተው፣ በአደገኛ ቦዘኔነት ተፈርጀው ከፊሉ ስደት እየበላቸው፣ ከፊሉ ሱስ እየዋጣቸው የነበሩ ወጣቶች ድንገት የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመፅ ማገዶ ነበሩ። ያኔ "ጀግኖች" ተብለዋል። ምክንያቱም ለልኂቃኑ ፖለቲካ ሁነኛ መሣሪያ ነበሩ። ወጣቶቹ ምናልባትም አእምሮ ከሚያላሽቅ የሥራ አጥነት ስሜት ወጥተው፥ ለራሳቸው ያላቸው ዋጋ እና ግምት የጨመረው በዚህ አመፅ ባደረጉት ተሳትፎ ይሆናል። ሕዝባዊ አመፁ ቆሞ ድንገት አገር መረጋጋት ሲጀምር ግን ወደ "መንደር ያሰለቹ አደገኛ ቦዘኔነት" መመለሳቸው ሆነ። ከተሰጣቸው ሥም መውረድ ከባድ ነው። ስለሆነም የአብዮታቸው ጠባቂ ሆኑ - ከሳሽ፣ ፈራጅ እና ቀጪ። የደቦ ፍርድ፤ በዚህ ወቅት ነው በፅንፈኝነት መፈረጅ የጀመሩት።

በዕውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የምትመራው 'ኢትዮጲስ' ጋዜጣ (በጥቅምት 24, 2011 እትሟ) በርዕሰ አንቀፅዋ ቄሮዎችን ለዘብተኛ እና ፅንፈኛ በሚል ከለያየቻቸው በኋላ ፅንፈኞቹን የማስቆም ሥራ መሠራት እንደሚገባ ጠቁማለች። የኢትዮጲስ ስህተት ምናልባት (አንድም) በአገሪቱ የደቦ ፍርዶች እና ወደ ስርዓት አልበኝነት የሚወስዱ እንቅስቃሴዎችን ለቄሮ ብቻ ለይታ መስጠቷ ነው። መቼም በድንጋይ ወግሮ መግደል እና በእንጨት ላይ ዘቅዝቆ መስቀልን የመሳሰሉ የደቦ ፍርዶች አንዱ ከሌላው የሚሻሉበት መንገድ አለ ተብሎ አይታመንም። በዚህ ረገድ ጉዳዩ 'ወጣት ፅንፈኞች' በሚል ሊጠቃለል ይችል ነበር ብዬ አምናለሁ። (ሁለትም) ቄሮ የተጻፈ ፕሮግራም የሌለው፣ አባላቱ በዝርዝር የማይታወቁ፣ አንድ ስትራቴጂ እና ግብ የሌለው የግፉአን ማኅበር መሆኑን ከግምት ውስጥ ያላስገባ መደምደሚያ መሆኑ ስህተት ያደርገዋል። ይህም ማለት ማንም ተነስቶ ቄሮ ነኝ ብሎ ማወጅ እና በዚያ ሥም ወንጀልም ይሁን መልካም ጀብዱ መፈፀም ያስችለዋል ማለት ነው። ብዙኃን መገናኛዎች ግን ቡድኑን ግልጽ ቅርፅ እና መዋቅር እንዳለው እንዲሁም "ተግባሩን" አቅዶ እንደፈፀመ ማኅበር ተመልክቶ "እንዲህ ነው" ወይም "እንዲያ ነው" ማለት የተሳሳተ ትርጉም ይሰጣል። (ሦስትም) የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች - ለምሳሌ የጃዋር "የቄሮ መንግሥት" እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ "ፀጉረ ልውጦችን መቆጣጠር" የመሳሰሉ - ንግግሮች ወጣቶቹን የውክልና ጦርነት ውስጥ እንደከተታቸው ከግንዛቤ ያላስገባ መደምደሚያ መሆኑ ነው።

ፍረጃ እና ተፅዕኖው፤
እስመ ሥሙ ይመርሖ ሀበ ግብሩ
(nomen est omen)

ቄሮንም ይሁን ፋኖን ወይም ሌላ የፖለቲካ ቡድኖችን በተመለከተ ለምናደርጋቸው ፍረጃዎች ማድረግ የሚገባን ጥንቃቄ አለ። ፍረጃ (labeling) በሥነ-ልቦና ግንባታ የሚያሳድረው ተፅዕኖ እንዳለ በርካታ ጥናቶች ያሳያሉ። «እነ እከሌ ይህን አያደርጉም»፣ «እንትን ሆኜ እንዲህ አላደርግም» የሚሉ አባባሎች የሚያስረዱን ቁምነገር ቢኖር የሆኑ ሰዎች ስብስብን የሚገልጽ ማንነትን የምንበይንበት (labeling/defining) መንገድ መልሶ የአባላቱን ድርጊት እንደሚወስን መረዳት እንደሚያሻን ነው። "ቄሮ አብዮተኛ ወጣት ነው" በተባለ ጊዜ አደባባዮችን በተቃውሞ ሰልፎች ንጧል። የለውጥ ጀምበር ሲከፈት "ለውጡን ጠብቁ" ሲባል እንደዚያው ለማድረግ እየሞከረ ነው። ወጣቶቹ በልኂቃኑ የሚሰጣቸውን ሥያሜ ለመመጠን እየተፍጨረጨሩ ነው። "ቄሮ መንግሥት ነው" ብለን ከአቅሙ በላይ ሥራ ከምናሸክመው፣ "ቄሮ የዴሞክራሲ እና የሥልጡን ፖለቲካ ጠበቃ ነው" ብለን በዚህ አቅጣጫ እንዲተጋ ብናደርገው ይመረጣል። "ቄሮ ፅንፈኛ ነው" እያልን ወደዚያ ከምንገፋው "ቄሮ ይህንን አያደርግም" ብለን ብንገስፀው ይሻላል።

ቺርስ ለጥንቃቄ!

Sunday, September 23, 2018

በዴሞክራሲ ተስፋ መቁረጥ? (አይታሰብም!)

ትላንት አንድ የስዊድን ጋዜጠኛ "ሐሳብን ከመግለጽ ነፃነት ይልቅ ደኅንነቴን እመርጣለሁ" የሚል አስተያየት አዲስ አበባ ላይ እንደገጠማት ነገረችኝ። ዛሬ ደግሞ በጥዋቱ አንዲት አሜሪካዊ ጓደኛዬ በዋትሳፕ "ብጥብጥ ካለበት ዴሞክራሲ ይልቅ ሠላማዊ አምባገነንነት ይሻላል" የሚል ክርክር እንደገጠማት ነገረችኝ። በጣም ነው ያዘንኩት፤ ምክንያቱም እዚህ ድምዳሜ ላይ እንድንደርስ የሚፈልጉ የፖለቲካ ቡድኖች እንዳሉ አውቃለሁ።

በመሠረቱ ዛሬ በጉዳዩ ላይ በአጭሩ መሞነጫጨር የፈልግኩት በነዚህ ሰዎች ብቻ አስተያየት ተነሳስቼ አይደለም። "ጭቆና ለምደን ነፃነት መሸከም አቃተን" የሚሉ አስተያየቶችን ደጋግሜ እሰማለሁ። ስህተቱ የሚጀምረው ዴሞክራሲም ይሁን ነፃነት ላይ "ደርሰናል" ከሚለው ድምዳሜ ነው። አሁን ያለንበት ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ ነፃነት ለማዋለድ በምጥ ላይ ነው ቢባል ይሻላል። እንደ አዋላጆቹ ብቃት ፅንሱ (ዴሞክራሲው) ይወለዳል ወይም ይጨናገፋል። አዋላጆቹ ካላወቁበት ደግሞ ፅንሱ እናትየውን ጨምሮ ይዞ ሊሔድ ይችላል። ስለዚህ ድምዳሜያችን ጥንቃቄ የሚያሻውን ጉዳይ ችላ እንድንለው ሊያደርገን ይችላል። ግን ዋነኛው የአረዳድ ችግር የዚህ ጉዳይ ብቻ አይደለም።

ሠላም በአምባገነንነት እና በዴሞክራሲ ውስጥ

አምባገነንነት ሕዝቡ "በቃኝ" ብሎ ቀና እስከሚል ድረስ ረግጦ የመግዛት ስልተ መንግሥት ነው። አምባገነኖች የበቃኝ ነጥብ ከመድረሷ በፊት ሁሉንም ነገር ስለሚያፍኑ ሠላም ያለ ያስመስላሉ። በአምባገነናዊ ስርዓት ውስጥ ፀጥታ ስላለ ሠላም ያለ ይመስላል። ነገር ግን የታፈነ አመፅ አለ፤ የታፈነ ደም መፋሰስ አለ። ስለ አመፁም ይሁን ስለ ደም መፋሰሱ መነጋገር አይፈቀድም። የመረጃ ምንጮችም ይታፈናሉ። በአምባገነናዊ ስርዓት ውስጥ የአመፁ መሪ መንግሥት ነው።

በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግን ሰዎች ቅሬታቸውን ሁሉ ያጮኻሉ፣ ትንሿም ብሶት ሳትቀር ትሰማለች። ይህ ራሳቸውን እንደሰጎን አሸዋ ውስጥ ቀብረው የሚኖሩትን ብዙዎች ከምቾት ዞናቸው ስለሚያስወጣቸው ሠላም ደፈረሰ ይላሉ። በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፀጥታው ይደፈርስ ይሆናል እንጂ እንደ አምባገነናዊ ስርዓት ሠላም አይደፈርስበትም። ግጭቶች በዴሞክራሲያዊ ስርዓትም ውስጥ አሉ። ይሁን እንጂ ንግግር ስለማይታፈን ግጭቶችን በአካል ሳይከሰቱ በድርድር መፍትሔ ይፈለግላቸዋል፤ ከተከሰቱም በኋላ በአጭሩ ለመቅጨት ፈጣን መፍትሔ ለመፈለግ ዴሞክራሲ ያስችላል።

በጣም ስኬታማ የሚባሉት አገሮች ውስጥ ልዩነቶቻቸውን በዴሞክራሲያዊ ስርዓት አቻችለው ኖረዋል፤ እኛም እንችላለን!

ሐሳብ እና አመፅ

"እመፅ ማነሳሳት" እና "የጥላቻ ንግግር" የሚባሉ ችግሮች አሉ። ነገር ግን ብዙዎች ቃላቱን የሚጠቀሙባቸው የማይፈልጉትን ሐሳብ ለማፈን ሲሆን ብቻ ነው። በመሠረቱ ዓለም ዐቀፍ ስምምነቶች ላይ ሐሳብን የመግለፅ ነፃነት እንዲከበር ቁርጠኛ አቋም የተወሰደበት አንዱ ምክንያት ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት "አመፅ" እና "ለውጥ" መካከል ሚዛን መፍጠር ስለሚችል ነው። ሐሳባቸውን በነፃነት እንዲገልፁ ያልተፈቀደላቸው ሰዎች በአመፅ ያደርጉታል። እንዲናገሩት ሲፈቀድላቸው ግን የሚጋጩ ፍላጎቶቻቸውን ሳይቀር ማስታረቂያ መንገድ በመነጋገር ይፈልጋሉ።

በአገራችን መደራጀትም ይሁን ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት ታፍነው መኖራቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህ በእንዲህ እያለ የማኅበራዊ ሚድያ መከሰት ተናደው መድረክ ያጡትንም፣ የተስማሙ የሚመስላቸውንም የሚጋጩትንም በአንድ ግንባር አገናኛቸው። በዚህ መሐል ጎራ ለይተው በሐሳብ መቆሳሰላቸው የሚጠበቅ ነው። መሬት ላይ ለመግባባት መነጋገርን፣ የዜግነት መብት እና ግዴታዎችን ማወቅ እና ማክበርን የሚያስተምሩ ሲቪል ማኅበራት ቢያብቡ ኖሮ፥ ሐሳቦች በየጉዳዩ ላይ ዕውቀት ካላቸው ሰዎች አንደበት ተቀብለው የሚያንሸራሽሩ ሚድያዎች ቢያብቡ ኖሮ፥ ዛሬ አላዋቂዎች ባሻቸው ጉዳይ ላይ ደፋር ተንታኝ ሆነው ብዙ ተከታይ እና አድማጭ አያፈሩም ነበር። ለዚህ ያበቃን አምባገነንነት እንጂ ዴሞክራሲ አይደለም።

አሁንም ቢሆን መፍትሔው ማዕቀብ አይደለም፤ ነፃነት ነው። ሁሉም ሰዎች በነፃነት በተነጋገሩ ቁጥር አሸናፊ ሐሳቦች እየተንጓለሉ ይወጣሉ። "እውነት ለሐሰትም ሳይቀር ምስክር ነች" እንደሚባለው፥ የሚዋሹት እውነት በሚናገሩት ይጋለጣሉ፤ ጥላቻ የሚሰብኩት ፍቅር በሚሰብኩት ይሸነፋሉ።

መፍትሔው በሰው ልጅ ማመን ነው

አምባገነናዊነት እና ዴሞክራሲያዊነት በሰው ልጆች ላይ ያለን እምነት መገለጫዎች ናቸው ብዬ አምናለሁ። አምባገነን ስንሆን ሰዎች መጥፎዎች ናቸው። ቁጥጥር፣ እገዳ እና ቅጣት ያስፈልጋቸዋል ብለን እናምናለን። ዴሞክራት ስንሆን ደግሞ በተቃራኒው በሰው ልጆች ቀናነት እምነት ይኖረናል። ሰዎች ሲያጠፉ እንኳን ለክፋት ወይም ክፉ በመሆን ሳይሆን በመሳሳት ነው ያደረጉት ብለን እናምናለን። ስለዚህ ዴሞክራት ስንሆን ለሰዎች ነፃነት፣ ከኃላፊነት እና ተጠያቂነት ጋር እናጎናፅፋለን።

በዴሞክራሲ ተስፋ ቆረጥን ማለት በሰው ልጆች ተስፋ ቆረጥን ማለት ነው።

Wednesday, August 1, 2018

የትግራይ ፖለቲካ እንደምን ወደዳር አገር ፖለቲካ ተገፋ?

የኢትዮጵያ ሥርወ መንግሥት መነሻ ማዕከሉ (core state የሚሉት) ሰሜን ላይ ነበር - አክሱም። ቀስ በቀስ ወደ ደቡብ እያፈገፈገ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማገባደጃ ላይ ሸዋ ላይ ከትሞ እስከ ዛሬ ዘልቋል። 'የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ' በአሁኑ ቅርፅዋ የተሠራችው በ19ኛው ክፍለዘመን ማገባደጃ ነው። ከዛሬዪቱ ኢትዮጵያ በፊት የነበረችው 'ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ' ነች። ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ እንደሌሎቹ የዓለማችን ጥንታዊ አገራት ሁሉ፣ ድንበር አልነበራትም - የተፅዕኖ አድማስ እንጂ።  የተፅዕኖ አድማሷ ደግሞ እንደ ጊዜው እና እንደ ነጋሹ አቅም ሲሰፋና ሲጠብ ነው የከረመው።

ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ የአማርኛ ተናጋሪዎች እና የትግርኛ ተናጋሪዎች በዋነኝነት የሚዘውሯት ነበረች። በተለይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ወዲህ ያለችው ኢትዮጵያ በሁለቱ ፉክክር እና ማመቻመች (compromise) ነበር የቆመችው። ዳግማዊ ምኒልክ ደቡቡን እና ምሥራቁን የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ አካል ባደረጉበት ወቅት ግን በቁጥር ከትግርኛ ተናጋሪዎቹ እና ከአማርኛ ተናጋሪዎቹ የሚበልጡ ኦሮሞዎች የአገረ መንግሥቱ አካል በመሆናቸው፥ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች በፊት ከነበራቸው ተቀናቃኝነት የበለጠ ኃይል አግኝተዋል። ይህ ክስተት ኢትዮጵያን ሦስተኛ የሥልጣን ተፎካካሪ እንድታገኝ አድርጓታል። (ይህ ማለት ግን ከዚያ በፊት ኦሮሞዎች የአገረ መንግሥቱ አካል አልነበሩም ማለት አይደለም፤ ሸዋ ቀድሞውንም ቅይጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ በ16ኛው ክፍለ ዘመን 'ታላቁ የኦሮሞ ፍልሰት' የኦሮምኛ ተናጋሪዎች ሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል ተቀላቅለዋል። ይህም የወሎና የጁ ኦሮሞ ፖለቲከኞችን አፍርቷል። በዘመን ወደኋላ በነጎድን ቁጥር ታሪኩ ይለዋወጣል፤ ስለዚህ ርቀን ባንሔድ ጥሩ ነው። የዚህ ጽሑፍ ዓላማም ዛሬን በሚጫኑ የቅርብ ጊዜ ታሪካዊ መቀናቀኖች ላይ ማተኮር ብቻ ነው። እንዲያውም ትግራይን ከተፎካካሪ ሕዝቦች የነጠሉ የታሪክ ኩነቶችን መለየት ነው።)

የኤርትራ (ባሕር ምላሸ) የጣልያን ቅኝ ግዛት መሆን የትግራዋዩን ቁጥር በግማሽ ቢቀንሰውም ትግራይ የመንግሥት መነሻ ማዕከል በመነበሯ ምክንያት የመሐል አገር የሥልጣን ፉክክሩ ውስጥ ተፅዕኖዋ ሳይቀንስ ከርሟል። በዳግማይ ምኒልክ ሰዐት ትልቁ ኃይል እና ሥልጣን ሸዋ ላይ ተከማችቶ የነበረ ቢሆንም፣ ትግራይ እና ደቡቡም በየአካባቢ ንጉሡ የተወሰነ ነጻነት ነበረው። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ (ቀኃሥ) ግዜ ግን የአካባቢ ነገሥታት ሁሉ ከስመው ማዕከላዊነት ሰፈነ። ቀኃሥ የሥልጣን መስህቡን ሁሉ አዲስ አበባ ላይ - በመዳፋቸው ሥር አኖሩት።

ደርግም የቀጠለበት ይህንኑ የቀኃሥ እጅግ የተማከለ መንግሥታዊ ስርዓት ነው። ኢሕአዴግ ሲመጣ ምንም እንኳን በፌዴራል ስርዓት የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን በሕግ (de jure) ለክልሎች ቢያከፋፍልም በተግባር (de facto) ትልቁ ሥልጣን ግን በማዕከላዊ መንግሥቱ ቁጥጥር ሥር ነበር። የኢሕአዴግ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት በእጅ አዙር የሥልጣኑን ቁጥጥር ለኢሕአዴግ ፈላጭ ቆራጮቹ ትሕነግኦች (TPLFs) ስላጎናፀፈ መቐለን ከአራት ኪሎ ያላነሰ ባለ ሥልጣን አድርጓት ነበር።

Monday, July 30, 2018

ብሔርተኝነት፤ ቅዱስ ወይስ እርኩስ?

በዚህ ርዕስ ረዥም መጣጥፍ መጻፍ ከጀመርኩ ረዥም ግዜ ሆነኝ፡፡ እስካሁን አላለቀም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፤ ጉዳዩ ስሜት የሚነካ እና በስሜት የሚነዳ ስለሆነ ፈርቼው ነው፡፡ የፖለቲካ ተዋስኦዋችንን በተከታተልኩት ቁጥር የተረዳሁት አንድ ነገር ቢኖር "ብሔርተኛ ነኝ" በሚሉ እና "ብሔርተኛ አይደለሁም" በሚሉት ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ብሔርተኝነትን የማመን እና የመሸሸግ ችሎታ ልዩነት ነው፡፡ ወይም ደግሞ አንዳንዴ ልዩነቱ ግለሰቦቹ የሚያራምዱት ብሔርተኝነት የሚያቅፋቸው ሰዎች ቁጥር የበዛ መሆኑ ‹ብሔርተኝነቱን› የመሸሸግ ዕድል ያገኛል፡፡ በጣም በተሳሳተ መደምደሚያ ላለመጀመር ያክል "ብሔርተኝነት" ደረጃው እና ልኩ ይለያይ ይሆናል እንጂ ሙሉ ለሙሉ ከውስጡ የወጣለት ሰው የማግኘት ዕድላችን ጠባብ ነው ብለን እንስማማ፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ‹ብዙኃን ብሔርተኛ ናቸው› የሚል መደምደሚያ ይዤ ነው ይህንን የምር አጭር ያልሆነ መጣጥፍ፣ ረዘመብኝ ካልኳችሁ መጣጥፌ ጨልፌ እና ጨምቄ የማስነብባችሁ፡፡

የመጀመሪያው አንቀፄ እንደሚያመለክተው ‹ብዙኃን ብሔርተኞች ናቸው›፡፡ ‹ብሔርተኝነት ቅዱስ ነው ወይስ እርኩስ?› የሚል ጥያቄ ማንሳት ‹ብዙኃን ቅዱስ ናቸው ወይስ እርኩስ?› የሚል ጥያቄ እንደማንሳት ያስፈራል፡፡ ቢሆንም እንጋፈጠዋለን።

ብሔርተኝነት ሲበየን

ብዙዎቹ ዓለም ዐቀፍ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ያሉ ምሁራን ለብሔርተኝነት ያላቸው ንቀት የትየለሌ ነው፡፡ ንቀቱ አንድም ብሔርተኝነት ‹ማኅበራዊ ፈጠራ› (social fabrication) ነው ከሚል የመነጨ ሲሆን፣ በሌላ በኩል የሰው ልጅን ያክል ባለ ብሩሕ አእምሮ በአጋጣሚ በበቀለበት ማኅበረሰብ ብቻ መበየን ከእውነታው የራቀ ስለሚሆን ነው፡፡ የሆነ ሆኖ የብሔርተኝነት የመዝገበ ቃላት ፍቺው "ተመሳሳይ ባሕል ያላቸው ሕዝቦች ፖለቲካዊ ነጻነት መፈለግ" ወይም "በአገር በጣም የመኩራት ስሜት" ነው (P.H. Collin (2014))፡፡

ኢንሳይክሎፔዲያ ብሪታኒካ ብሔርተኝነትን የሚበይነው እኔንም በሚያስማማ መልኩ ነው፡- "የአንድ ግለሰብ ታማኝነት እና ቁርጠኝነት ከሌሎች ግለሰቦች እና ቡድኖች ፍላጎት በላይ ለብሔረ-መንግሥቱ (nation state) ማድላት ላይ የተመሠረተ ርዕዮተዓለም ነው"። በዚህ መሠረት ቀጣዮቹን ርዕሰ ጉዳዮች እያነሳን እንጥላለን፡፡

ሰዎች ለምን ብሔርተኛ ይሆናሉ?

ለዚህ ጥያቄ ቀላል መልስ እሰጣለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች ብሔርተኛ የሚሆኑት ፈቅደው እና አቅደው ሳይሆን ባጋጣሚ ነው፡፡ አጋጣሚው የሚጀምረው ‹የት እና ከማን ተወለዱ?› ከሚለው ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ብሔርተኝነትን በንባብ እና በውይይት ሊያዳብሩት ይችላሉ እንጂ የሚጀምሩት ግን በውርስ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ብሔርተኝነት ራሳቸውን በአንድ የብሔር አባልነት የሚጠሩ ሰዎች እስኪኖሩ ድረስ አይኖርም፡፡ የሆኑ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ እና የሚያስተሳስራቸው ማኅበራዊ አጀንዳ ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን በአንድ ማንነት ለይተው መጥራት ሲጀምሩ ወይም በሌሎች በዚያ ማንነት መጠራት ሲጀምሩ ብሔርተኝነት ተጀመረ ማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ብሔርተኝነት በስሎ እና ጎርምቶ የሚወጣው እነዚያ ሰዎች ራሳቸውን ከሌሎች የተሻሉ እንደሆኑ ሲያስቡ፣ እና/ወይም በማንነታቸው ሳቢያ በሌሎች እየተጠቁ እንደሆኑ ሲያስቡ ነው፡፡ ብሔርተኝነት የሚጎመራው የጋራ ማንነት ላይ ጥቃት ያደርሳሉ ተብለው የሚታሰቡ የተለየ ማንነት እንዳላቸው የሚታመኑ ጠላቶች ሲኖሩ ነው፡፡

Sunday, July 22, 2018

የማንን ግዛት ማን ያስተዳድር?

ነገሮችን አቃልሎ እና ሸንሽኖ ለመረዳት መሞከር ጠቃሚ የሚሆንበት አጋጣሚ ቢኖርም፥ ሁሌም ትክክለኛ ውጤት አያስገኝም። አገርን የሚያክል ትልቅ ፅንሰ-ሐሳብ በግለሰብ ርስት ዓይን  ለመረዳት መሞከርም ከዚህ ዓይነቱ አደገኛ ስህተቶች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ 'እከሌ የተባለው ግዛት የማን ነው?' እና 'እከሌ የተባለውን ግዛት ማን ያስተዳድር?' የሚሉት ጥያቄዎች ዐውድ በጣም አሳፋሪ እና 'ገና በዚህ ጉዳይ እንኳ መግባባት አልቻልንም እንዴ?' በሚል ራሳችንን እንድንታዘብ የሚያደርግ የዘወትር ገጠመኝ ነው። 

'አዲስ አበባ የማነች?' የሚለውን ጥያቄ ደጋግሞ መስማት አስደናቂ አይደለም። የቡድን ሥም እየጠሩ፣ ታሪክ እየደረደሩ የባለቤትነት ማስረጃ ለማምጣት የሚሞክሩትን ሰዎች መከራከሪያ ማድመጥም የከተማዋን ኅልውና ያክል አዲስ ነገር አይደለም። የዚህ ጽሑፍ መነሻም የምክትል ከንቲባዋን ሹመት ተከትሎ የዚህ ክርክር እንዳዲስ ማገርሸት ነው። አዲስ አበባ የማን ነች? እነማን ናቸው ሊያስተዳድሯት የሚገባቸው? መጀመሪያ ግን ኢትዮጵያ ራሷስ የማነች?

ኢትዮጵያ የማነች?

ቢያንስ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ኢትዮጵያ የምንላት ሕዝቧን፣ ግዛቷን፣ መንግሥቷን እና ሌሎች የዓለም መንግሥታት የሚቀበሉትን ሉዓላዊነቷን ነው። ሉዓላዊነት የአገር ፅንሰ-ሐሳብነት መገለጫ ነው። በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ላይ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች "የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች" ናቸው (አንቀፅ 8)። ይህ ማለት 'ኢትዮጵያ የኦሮሞ፣ አማራ፣ ሶማሌ፣ ትግራዋይ፣ ወዘተ የጋራ ንብረት ናት' የሚል ትርጉም ይሰጣል። ከላይ ሲታይ 'ኢትዮጵያ የሁሉም ናት' የሚል ጭብጥ ያለው ይመስላል። ነገር ግን በዚህ ብያኔ እያንዳንዱ ዜጋ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለድርሻ መሆን አይችልም። 'የኢትዮጵያ' የሚባሉት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች አባል ያልሆነ የኢትዮጵያ ዜጋ የሉዓላዊ ሥልጣኑ ባለቤት መሆን አይችልም።

Tuesday, July 3, 2018

ለውጥ እና ውዥንብር

አሁን ያለንበት ሁኔታ "ታስሮ የተፈታ ጥጃ" ሁኔታ ነው። መዝለል እና መቦረቅ - የነፃነታችንን ልክ መፈተን የምንፈልግበት ወቅት ነው። ምክንያቱም ነፃነታችን ከእስር የተፈታው ገና አሁን ነው፣ የዴሞክራሲ ባሕል አልነበረንም፣ በዚያ ላይ ያልተመለሱ እልፍ ጥያቄዎች አሉን። ይሁን እንጂ ሲደክመን እንሰክናለን። መዝለል ስለምንችል ብቻ አንዘልም። መርገጥ ስለምንችል ብቻ አንራገጥም። ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በተደራጀ፣ በሕጋዊ እና ሠላማዊ መንገድ ታግለን ማስመለስ እንጀምራለን። ከዚያ በፊት ግን ዝላያችን እና እርግጫችን ለገዢዎቻችን የለውጡን ተስፋ ለመቀልበሻ፣ እኛን መልሶ ለመርገጫ ምክንያት እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

አንዲት ኤርትሪያዊት የትዊተር ተጠቃሚ፣ 'ሰውያችሁ ባለ ግርማ ሞገስ እና ጥሩ ተናጋሪ በመሆኑ እንዳትሸወዱ፣ የእኛም መሪ እንደዛ በመሆኑ የለውጡን ተቋማዊነትን ሳናረጋግጥ ነው ለዚህ የተዳረግነው' የሚል መልዕክት ለኢትዮጵያውያን አቻዎቿ አስተላልፋለች። አዎ፣ የዛሬው ታላቁ አምባገነን ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የዛሬ 27 ዓመት ገደማ በኤርትራውያን ዘንድ ታላቅ ሕዝባዊ ይሁንታ ያለው መሪ ነበር።

"ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከራሳቸው መጠበቅ" በሚለው ጽሑፌ 'ብዙዎቹ ነጻ አውጪዎች ኋላ አምባገነን ይሆናሉ' ማለቴን እንደ ጅምላ ድምዳሜ የወሰዱብኝ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። እኔ ለማመልከት የፈለግኩት በአንድ ወቅት 'ነጻ አውጪ' የነበረ፣ ሌላ ግዜ 'አምባገነን' እንደማይሆን አያረጋግጥም ነው። ይህ እንዳይሆን ብቸኛው ዋስትና 'ቁጥጥርና ሚዛን' (check and balance) ነው። ትላንት ጓደኞቼ ስለ ኢዲ አሚን ዳዳ አንድ ጽሑፍ እያስነበቡኝ ነበር። ከዓለማችን የምንግዜም አምባገነኖች አንዱ የሆነው ኢዲ አሚን በሥልጣን አፍላው ዘመን በምዕራባውያን ሚዲያዎች ሳይቀር የተንቆለጳጰሰ ሰው ነበር። ሰውን አምባገነን የሚያደርገው ተቋማዊ ነጻነት አለመኖሩ እና የግለሰቦች ሥልጣን አለመገደቡ ነው። 

ኢትዮጵያ ለውጥ ለምን አይዋጣላትም?

ይህንን ጥያቄ ያነሳሁት አሁን ያለንበትን የለውጥ ተስፋ ጥላሸት ለመቀባት ወይም ተቀልብሷል ለማለት አይደለም። ለውጡ ከግለሰቦች በጎ ፈቃድ ወደ ተቋማዊ እውነታነት እንዲሸጋገር ካለኝ ጥልቅ ጉጉት ነው። ሁሉም ሰው የለውጡን አካሔድ በጥንቃቄ እንዲመለከተው ስለምፈልግ ነው።

ኢትዮጵያ እንዲህ የለውጥ ተስፋ ውስጥ የገባችው አሁን ብቻ አይደለም። የንጉሣዊው ስርዓት መደርመስ እና የመሬት ላራሹ መታወጅም ግዙፍ ሕዝባዊ ይሁንታ እና ተስፋ ፈንጥቆ ነበር። የምርጫ 1997 ዋዜማ አገራችን የመጀመሪያውን ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ልታካሒድ ነው በሚል ትልቅ ተስፋ

Monday, June 25, 2018

የማንነት ብያኔ አፈና…

ከእኛ አገር የማያልቁ ችግሮች መካከል አንዱ የማንነት አረዳድ እና አበያየን ጉዳይ ነው። ማንነት እና ምንነት የፖለቲካ ጫወታችን አስኳል ሆኖ ሳለ፣ የማንነት አበያየናችን ግን ግለሰቦች የራሳቸውን ማንነት የሚበይኑበት ነጻ ዕድል የማይሰጥ ነው። 

የኦነጉ በያን አሶባ ባንድ ወቅት ከኢሳት ቴሌቪዥን "ኦሮሞ ማነው?" የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። "ኦሮሞ ነኝ ያለ" የሚል ምርጥ መልስ ሰጥተዋል። ነገር ግን ብዙዎች ማንነትን በዘር የሚወረስ እንጂ በማኅበራዊ-ሥሪት (social construction) የሚመጣ ነገር አድርገው አይመለከቱትም። እውነት መሆኑን ከራሷ ማረጋገጥ አልቻልኩም እንጂ ድምፃዊ ሴና ሰለሞን ከአማራ ተወላጆች የተወለደች ኦሮሞ ነች፤ "ኦሮሞ ነኝ" ስላለች። ራሷን የምትገልጸው እንደ ኦሮሞ ሲሆን፣ በዘፈኖቿ የታገለችውም ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት ነው። የወላጆቿ የማንነት ታሪክ የሐሰት ወሬ ቢሆን እንኳ ነባራዊ ምሳሌ እናጣለን እንጂ፣ ምሳሌው ማንነትን የመምረጥ ግለሰባዊ ነጻነቱን የተሳሳተ አያደርገውም። 

'ኢትዮጵያዊ ማንነት አለ፣ የለም? ጎጃሜ ማንነት አለ፣ የለም? አዲሳበቤ ማንነት አለ፣ የለም?' የሚሉት ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ምንጫቸው የግለሰቦች ማንነት እኛ ራሳችንን እንዲሁም ሌሎችን ከምንረዳበት መንገድ ውጪ መወሰን የለበትም ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ነው። በቀላል ቋንቋ ለመግለጽ አባባሉ "እኔ ናችሁ ከምላችሁ ውጪ መሆን አትችሉም" ነው። 

በበኩሌ ሰዎች የራሳቸውን ማንነት ብለው የሚጠሩት ወይ 'የሚኮሩበትን' አሊያም 'የተበደለባቸውን' [ወይም የተበደለባቸው የሚመስላቸውን] ማንነታቸውን ነው ብዬ ነው የማምነው። ይሁን እንጂ ሁሉም ሰዎች ማኅበራዊ ሥሪታቸው ከብዙ ድርብ፣ ድርብርብ ማንነቶች የተገነባ ነው። ጥቁር ሕዝብ መሐል ላደጉ ኢትዮጵያውያን ጥቁርነት የማንነታቸው መገለጫ መሆኑ ትዝ ብሏቸው አያውቅም። ነገር ግን ከኢትዮጵያዊ ወላጆች ተወልደው ነጮች አገር ያደጉ ኢትዮጵያውያን "ምንድን ነህ/ምንድን ነሽ?" የሚል ጥያቄ ቢቀርብላቸው፣ ጥቁርነታቸው ቀድሞ የሚመጣባቸው መልስ ሊሆን ይችላል? "ምንድን ነህ/ነሽ?" የሚለው ጥያቄ የማንነት ወይም የምንነት ጥያቄ መሆኑ አያጠራጥርም። መልሱ ግን ወጥ አይደለም። እንደ ሁኔታው እና ቦታው ይለያያል። አንዱ "አካውንታንት ነኝ" ብሎ ሙያውን እንደማንነቱ መገለጫ ሊጠቅስ ይችላል፣ ሌላዋ "ሙስሊም ነኝ" ልትል ትችላለች። በሁኔታው፣ በወቅቱ እና በቦታው ሰዎች ስለማንነታቸው የሚሰማቸው ስሜት የተለያየ ሊሆን ይችላል። ይህም የማንነትን ወጥ አለመሆንና ድርብርብነት ያረጋግጣል።

እኔ በማንነቴ ቀረፃ ውስጥ "የድሀ ልጅ" መሆኔን ያክል ተፅዕኖ የፈጠረብኝ ነገር አለ ብዬ አላምንም። የድሀ ልጅ ሆኖ ማደግ ያለንን ነገር 'ላጣው እችላለሁ' በሚል ፍርሐት እና የሌለንን ነገር 'ላገኘው አልችልም' በሚል ስጋት ውስጥ መኖር ማለት ነው። ይህ ማንነት ነው። በድህነት ውስጥ ላደገ ሰው፣ ዓለም ማለት የመግዛት አቅም ባላቸው እና በሌላቸው ሰዎች የተሞላች ናት። የአዲስ አበባ ድሀ፣ ከብራዚል ድሀ ጋር በሥነ ልቦና የሚያግባባ ማንነት አለው። ነገር ግን "የድሀ ልጅ" የሚባል ማንነት በኛ የፖለቲካ መዝገበ ቃላት የለም። ስለዚህ ከዚህ ውጪ ብዙ ማንነቶች አሉኝ። ለምሳሌ ጦማሪነት። ከዚህ በፊት ስታሰር ስፈታ የነበርኩት ተቺ ጦማሪ ስለሆንኩ ነው። ስለዚህ ምንድን ነህ ስባል 'ብሎገር ነኝ' የምልባቸው ግዜያት ብዙ ናቸው። ለምሳሌ እስር ቤት በማንነቴ ነው የታሰርኩት የሚሉ ነበሩ። እነሱ "ኦሮሞ በመሆኔ"፣ "አማራ በመሆኔ" ሲሉ እኔ ደግሞ "ብሎገር በመሆኔ" እል ነበር። ይህም ማንነት ነው። ይህንን ብነፈግ እንኳ በትምህርት ያፈራሁት፣ በተወለድኩበት አካባቢ ያፈራሁት፣ በእምነቴ ወይም ባለማመኔ ያፈራሁት ብዙ ማንነቶች አለኝ። 

ነገር ግን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ብያኔ መሠረት እነዚህ ሁሉ ማንነቶቼ ዋጋ የላቸውም። "ምንድን ነህ?" ስባል የወላጆቼን የዘውግ ማንነት እንድናገር ይጠበቅብኛል። ወላጆቼ ቅይጥ ቢሆኑ እንኳን የአባቴን [ይህ ካልሆነ ደግሞ የእናቴን] የዘውግ ቡድን ማንነቴ ብዬ እንድናገር ይጠበቅብኛል። እኔ እኔን ይገልጸኛል የምለው ማንነት እንዲኖረኝ ነጻነቱ የለኝም። በዚህ አካሔድ "ኦሮሞ ነኝ" ማለት፣ ወይም "አማራ ነኝ" ማለት፣ ወይም "አዲሳበቤ ነኝ" ማለት ምንም ዋጋ/ጥቅም የለውም። ምክንያቱም በኔ ማንነት ላይ እኔ የመወሰን ነጻነቱ የለኝም። 

Wednesday, June 20, 2018

የተዘነጋው የኮንሶ እስረኞች ጉዳይ ("እኛስ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወይ?")

ፎቶው ላይ ከግራ ወደቀኝ የሚታዩት፤ የኮንሶ መሪ ካላ ገዛኸኝ እና ወንድማቸው

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ሕዝባዊ አመፆች በተቀጣጠሉበት ወቅት፣ በሕዝብ ብዛት ትንሿ ኮንሶም ከዐሥር ወራት ላላነሰ ጊዜ ሕዝባዊ ተቃውሞ ታደርግ ነበር። በወቅቱ የመብት ተሟጋቾች አመፁ አገር ዐቀፍ እንደሆነ ለማስረዳት እንደምሳሌ የኮንሶን ጉዳይ ደጋግመው ይጠቅሱት ነበር። በወቅቱ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሠላማዊ ተቃውሞዎችን በኃይል በመበተን፣ ብዙዎችን ወደ እስር ቤት አጉረዋል። ከነዚህ እስረኞች ውስጥ የኮንሶ የጎሳ መሪ የሆኑት ካላ ገዛኸኝ ወልደዳዊት ካዮቴ ይገኙበታል። ('ካላ' በጎሳ መሪነት የሚገኝ የጎሳ ሐረግ ማዕረግ ነው።)

ካላ ገዛኸኝ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በሲቪል ምሕንድስና ተመርቀዋል። የጎሳ መሪነቱን ከአባታቸው የወረሱት በጥቅምት 2006 በባሕላዊው ወግ መሠረት ከአባታቸው ነበር። የጎሳ መሪው በኮንሶ ማኅበረሰብ ልማድ መሠረት ልማዳዊ ዳኝነት፣ ግልግል እና ሌሎችም ማኅበራዊ አስተዳደር ይሰጣል። ይሁን እንጂ የአሁኑ የጎሳ መሪ ካላ ገዛኸኝ ሠላማዊ ሕዝባዊ ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት ከሌሎች የኮንሶ ብሔረሰብ አባላት ጋር ለእስር ከተዳረጉ እና ከማኅበራዊ ኃላፊነታቸው ከተገለሉ አንድ ዓመት ከ10 ወራት አለፏቸው። ካላ ገዛኸኝ በተከሰሱበት መዝገብ ብቻ 43 ሰዎች ተከስሰዋል። ያነጋገርኳቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እንደነገሩኝ ግን የጠቅላላ እስረኞቹ ቁጥር 467 ነው። እነዚህ ሕዝባዊ ጥያቄ ያነሱ የኮንሶ ብሔረሰብ አባላት በጊዶሌ ማረሚያ ቤት፣ ኮንሶ ፖሊስ ጣቢያ እና አርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት ታስረው ይገኛሉ። ካላ ገዛኸኝ እና ሌሎችም 180 ገደማ ሰዎች የታሰሩት በአርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት ነው። 

ከእስር ውጪ ከመንግሥት የሥራ ገበታቸው ተባርረው (እና ከግንቦት 2008 ጀምሮ) ቤተሰባቸው የኅልውና አደጋ ላይ የወደቀባቸው ከ250 በላይ የኮንሶ ብሔረሰብ አባላት እንዳሉ ዝርዝሩን እና አቤቱታ ያቀረቡበትን ደብዳቤ ተመልክቻለሁ። 

የኮንሶ ጥያቄ ምንድን ነው?

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደነገሩኝ ኮንሶ ተጠሪነቷ ለደቡብ ክልላዊ መንግሥት የነበረች ልዩ ወረዳ ነበረች። ይሁን እንጂ ከመጋቢት 2003 ጀምሮ ልዩ ወረዳነቷ ቀርቶ፣ ተጠሪነቷም ለዞን ሆኗል። ነዋሪዎቹ በአሁኑ ወቅት 'በሰገን አካባቢ ሕዝቦች' አስተዳደር ሥር 'እንደተጨፈለቁ' የነገሩኝ ሲሆን፣ ይህም የራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ከመጣሱም በላይ ከተለያዩ የመንግሥት አገልግሎቶች የመገለል ጦስ እንዳመጣባቸው አጫውተውኛል። ይህንንም በመቃወም በ2008፣ የ81ሺሕ ሰዎች ፊርማ በማሰባሰብ 12 አባላት ያሉት ኮሚቴ በመወከል ጥያቄያቸውን ለክልሉ ምክር ቤት እንዲሁም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል። ሆኖም ያገኙት መልስ የለም። ይልቁንም የፀጥታ ኃይሎች 12ቱን የኮሚቴ አባላት ሊያስሯቸው ሲሞክሩ ሕዝቡ ሆ ብሎ ወጥቶ በማስቆም፣ የኮሚቴ አባላቱ እንዳይታሰሩ በሚል ውክልናቸውን አንስቷል። 

ኮሚቴዎቹ ቢነሱም ተቃውሞዎቹ ግን የቀጠሉ በመሆኑ በወቅቱ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አሰፋ አብዩ ተወካዮቻችሁን ላናግር በማለታቸው 23 ሰዎች ተወክለው አነጋግረዋቸዋል። ወትሮም ጥያቄያቸውን ማስተናገድ የነበረበት ሌላ አካል በመሆኑ የፌደራል ፖሊስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ካላ ገዛኸኝን ጨምሮ ሁሉንም ለቃቅሞ ለእስር ዳርጓቸዋል። በእስሩ ወቅት የጎሳ መሪውን እና ልማዱን በሚያዋርድ መልኩ ካልሞተ በቀር ከክንዱ የማይወልቀውን ከዝሆን ጥርስ እና ከአውራሪስ ቀንድ የተሠራ የቃልኪዳን አምባር ፖሊሶች መሰባበራቸውን በምሬት ነግረውኛል።

ክሱ ምን ይላል?

የታሰሩት ሰዎች ከ400 በላይ ቢሆኑም ፍርድ ቤት እየቀረቡ ያሉት ግን የተወሰኑት ብቻ እንደሆኑ ተነግሮኛል። ፍርድ ቤት ከሚቀርቡት ታሳሪዎች መካከል የነካላ ገዛኸኝ መዝገብ (እዚህ ሙሉውን ማየት ይቻላል) ላይ እንደሚነበበው ከሆነ ክሱ የፖለቲካ ነው። "የወረዳው ሕዝብ በመንግሥት ላይ በአመፅና በአድማ ካልተሰለፈ ይህ ጥያቄ በሠላማዊ መንገድ ምላሽ አያገኝም" በማለት ቅስቀሳ አድርገዋል በሚል ታስረው እስካሁን ፍርድ አላገኙም። እንደሌሎች ፖለቲካ እስረኞችም ክሳቸው አልተቋረጠላቸውም። አሁን ቀጣዩ ቀጠሯቸው በመጪው ሰኞ ሰኔ 18/2010 ነው። 

ለምን አልተፈቱም?

የኮንሶ እስረኞች ከኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በተቃውሟቸው ምክንያት ተለቃቅመው እንደታሰሩት ዜጎች ሁሉ የፖለቲካ እስረኞች ናቸው። ይሁን እንጂ ከኮንሶ እስረኞች መካከል እስካሁን አንድም ሰው አልተፈታም። በዚህም "እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወይ?" የሚል ቁጭት ተሰምቷቸዋል። ከ350 ሺሕ በላይ ነዋሪ ባላቸው 42 የኮንሶ ቀበሌዎች የተውጣጡ ሽማግሌዎች ይህንን አቤት ለማለት ተሰብስበው አኔቱታዎቻቸውን ለክልሉ መንግሥትም፣ ለፌዴራሉ መንግሥትም አቅርበው ነበር። ይሁን እንጂ ማንም መልስ አልሰጣቸውም። ይልቁንም አሁንም በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች እየተዋከቡ ነው። ከሽማግሌዎቹ መካከል አንድ ሰው ባለፈው ሳምንት ሲታሰር ሌሎችም ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው። 

አሁን ዜጎች የፀጥታ ኃይሎች ማዋከብ በመቅረቱ መፍራት ባቆሙበት ሰዐት፣ የኮንሶ ሰዎች ግን አሁንም ከእስር ስጋት ጋር ተፋጥጠዋል። ይህንን እጅግ በጣም አሳጥሬ የጻፍኩትን መረጃ የሰጡኝ ሰዎች ሥማቸውን መጥቀስ ይፈቅዱልኝ እንደሆነ ስጠይቃቸው፣ "እኛ አካባቢ ያለው ሁኔታ እንደ አዲስ አበባ አይደለም። ለኛ ጥሩ አይደለም" ብለውኛል። 

ለኮንሶ ብሔረሰብ ዜጎቻችን የሚደርስላቸው ማን ይሆን? [እባካችሁ ይህንን መረጃ እንዲሰራጭ በማገዝ የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ የኮንሶ ዜጎቻችንን ከእስር እንዲፈታ የበኩሎን አስተዋፅዖ ያድርጉ።]

Monday, June 4, 2018

በማንነት ማፈናቀልን እንዴት መቀነስ ይቻላል? (የግል ጥቆማ)

(ከታች ያስቀመጥኳቸው ጥቆማዎች በጥናት ላይ የተመሠረቱ የመፍትሔ ሐሳቦች ሳይሆኑ በግል ትዝብት የተጠቆሙ ናቸው። በምስሉ ላይ የሚታየው (ፎቶ: ቴዎድሮስ አያሌው) በ1977 ድርቅ ወቅት ደርግ ቄለም ወለጋ አስፍሯቸው የነበሩ እና አሁን ተፈናቅለው አላማጣ የሚገኙ ናቸው። በምስሉ እንደሚታየው አብዛኛዎቹ የተወለዱት እዚያው አካባቢ ሲሆን፣ ወላጆቻቸው እና አያቶቻቸው ናቸው ከአላማጣ ነበር ቄለም ወለጋ እንዲሰፍሩ የተደረጉት።)

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ 'የማንነት' እና 'የብሔር' ፖለቲካ ወይም ጥያቄ ተምታተዋል። ብዙ ግዜ ሁሉም ነገር 'የብሔር ጥያቄ' ነው፤ መልሱም የሚገኘው 'በብሔርተኝነት' ነው የሚባለው ጉዳይ ከማንነት ጋር የተያያዘውን ጥያቄ ያድበሰብሰዋል። እንዲያውም አንዳንዴ ብሔርተኝነት ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል። የማንነት ወይም የብሔር ትርጉሙም እንዲሁ የተምታታ ነው። ምክንያቱም ማንነትም ይሁን ብሔር በተለምዶ የሚበየነው በቋንቋ ላይ ተመሥርቶ ነው። ስለዚህም በተምታታ ትርጉም ላይ የተመሠረተ ብሔርተኝነትም ለተሳሳተ ጥያቄ የተሳሳተ መልስ ለመስጠት ይዳርጋል። ማንነት በቋንቋ ሊመሠረት ይችላል፤ ነገር ግን አንድ ቋንቋ እየተናገሩ የተለያየ ማንነት ያላቸው ግለሰቦች ወይም ሕዝቦች አሉ። ማንነት በፆታ ብቻ ሊወሰን ይችላል። ወይም ደግሞ በፆታዊ ግንኙነት ምርጫ ሊወሰን ይችላል። በመልክ ወይም በቆዳ ቀለም። ወዘተ… ለምሳሌ ያክል ቱትሲዎች እና ሁቱዎች አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሆነው፣ ልዩነታቸው የመልክ (እና የታሪክ ድርሻ) ነው። 

ፌዴራሊዝሞች የአወቃቀር ስርዓታቸው ምንም ቢመስል፣ ዋነኛ ዓላማቸው በብሔርተኝነቶች መካከል ውጥረቶችን ሥልጣን በማከፋፈል እና በማጋራት ማርገብ ነው። የእኛው ግን ውጥረቱን ምናልባትም አባብሶታል አልያም ገሀድ አውጥቶታል። በሕገ መንግሥቱ ባይሰፍርም "የእንትን ክልል፣ ለእነ 'እንቶኔ'" የሚል ያልተጻፈ ሕግ አለ። 'እንቶኔነት' ከወላጆች በደም የሚወረስ መሆኑም እንዲሁ ያልተጻፈ ሕግ ነው። ስለዚህ በእንትን ክልል ያሉ ከእነ እንቶኔ ውጪ ያሉ ነዋሪዎች በሙሉ የመገለል፣ የመጠቃት፣ የመሰደድ ዕድላቸው ሰፊ ነው። በእርግጥ በዚህ መሰሉ ጥቃት እና ስደት በተደጋጋሚ የሚጠቁት ሰዎች በተለይ በብዙ ክልሎች የተበተኑት ብሔረሰብ አባላት ናቸው። ነገር ግን ይሔ ዕጣ ያልገጠመው አለ ለማለት ይከብዳል። ባለፈው ዓመት ከሶማሌ የተፈናቀሉት 600 ሺሕ የኦሮሞ ተወላጆች ጉዳይ ሪከርድ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ የአማራ ተወላጆች የመፈናቀል ዜናን መስማትም ለጆሮ እንግዳ አይደለም። የሆነ ሆኖ ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር 1 ሚሊዮን ተኩል ገደማ ነው። በየዘውጉ ተጎራባቾች አንዱ አንዱን በውኃ እና ግጦሽ/እርሻ መሬት ማጥቃት እና ማፈናቀል የነበረ፣ እና የበለጠ ፖለቲካዊ እየሆነ የመጣ ነገር ነው። ማንነትን መሠረት ያደረጉ መፈናቀሎች በተከሰቱ ቁጥር የዘውጉን ቡድን እየቆጠሩ የአንድ ወገን ጉዳይ ብቻ ማስመሰሉ ለብሔተኝነት ፖለቲካ ይበጅ ይሆናል እንጂ ችግሩን ለመቅረፍ እምብዛም አይበጅም። ልብ በሉ፣ የተፈናቀሉት ሰዎች በማንነታቸው እስከሆነ ድረስ የተፈናቃዮቹን ማንነትም ይሁን የአፈናቃዮቹን ማንነት መጥቀሱ ላይ ችግር የለውም። ነገር ግን ለብሔርተኝነት ትርፍ ሲባል ብቻ ነገሩ በሁለት ሕዝቦች መካከል የተደረገ ፍጥጫ ማስመሰል እሳቱ ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ ነው። ከዚያም በላይ ሰዎች ችግሩን በገለልተኛ ዓይን አይተው እንዳይከላከሉት ወይም ጥብቅና እንዳይቆሙለት ይገፋል።

ለምሳሌ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል አንድ ቀበሌ ውስጥ የተፈናቀሉ የአማርኛ ተናጋሪዎች ጉዳይ "የቤንሻንጉል-ጉሙዝ ሕዝብ የአማራን ሕዝብ አፈናቀለ" ብሎ መዘገብ የተሳሳተ ምስል ከመስጠቱም በተጨማሪ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል መቃቃር ይፈጥርና በክልሉ ሌሎች ቀበሌዎች ነዋሪዎች የሆኑ አማርኛ ተናጋሪዎችንም ለበለጠ ጥቃት ሊዳርግ ይችላል። አንዳንዴ መፈናቀሎቹ የሚከሰቱት በቀበሌዎቹ አስተዳደሮች ሆኖ ሳለ፣ የሕዝቡ ሥራ አስመስሎ ማቅረቡም ነዋሪዎቹን ከጎረቤቶቻቸው ጋር ማቀያየም ነው።

ችግሩ እንዴት ይቀረፍ?

በመጀመሪያ ደረጃ የችግሩን ምንጭ በአግባቡ መፈተሽ አስፈላጊ ነው። ዋነኛው ችግር የሚመስለኝ የአስተሳሰብ ነው። 

1ኛ፣ ክልሎች የየትኛውም ክልል ተወላጅ በክልላቸው የመኖር መብት እንዳለው መቀበልና መብቱን ማረጋገጥ አለባቸው።

የትኛውም ክልል የየትኛውም ብሔረሰብ ተወላጅ የግል ንብረት አይደለም። የትኛውም ብሔረሰብ ተወላጆች በየትኛውም ክልል ውስጥ ከየትኛውም ብሔረሰብ ተወላጅ የበለጠ ወይም ያነሰ መብት የላቸውም። የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 32/1 "ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቷ ውስጥ የሚገኝ የውጭ አገር ዜጋ በመረጠው የአገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመሥረት፣" መብት አለው ይላል። ይህ ደግነቱ ሕገ መንግሥቱ አክብሮታል አንጂ ባያከብረውም የማይሻር የተፈጥሮ ሕግ ነው። በክልሎች ቀርቶ በአገራት ድንበሮች ይህንን መገደብ ከተፈጥሮ ሕግ ያፈነገጠ፣ ነገር ግን ለስርዓት (order) ሲባል የምንታገሰው ሕግ ነው። ይህንን ከልብ መቀበል ያስፈልጋል። በሕግ እና ደንቦች የሚተገበርበት መንገድ ይመቻቻል እንጂ በልዩነት የሚታደልበት/የሚነፈግበት መንገድ ሊኖር አይገባም። 

ፌደራሊዝሙ ያልተማከለ አስተዳደር ፈጥሯል። (በፌዴራሊዝሙ አወዛጋቢው ጉዳይ አከላለሉ ዘውግ-ተኮር መሆኑ ላይ ነው። ይሔ ጽሑፍ መዋቅሩ ሳይለወጥ ችግሩን መቅረፍ ላይ ያተኮረ ስለሆነ ወደዛ ውዝግብ አንገባም።) እነዚህ አስተዳደሮች በእየርከኑ ባሉ የአስተዳደር ክፍሎች ውስጥ የነዋሪዎችን ቁጥር ከግምት ውስጥ ያስገባ የብዙኃን አመራር እና የድሀጣንን መብት የማክበር ግዴታ አለባቸው። ብዙኃኑ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆነ ቋንቋው የክልሉ የሥራ ቋንቋ ባይሆን እንኳ የአስተዳደር ክፍሉ የሥራ ቋንቋ መሆን ይኖርበታል። ይህ ግን ለአስተዳደር ቅልጥፍና እንጂ መብትን ለማከፋፈል አይደለም። ድሀጣኑ ከብዙኃኑ ዕኩል መብቶች እና ዕድሎች ሊኖሯቸው የግድ ነው። በሕጋዊ መንገድ መኖሪያ ቦታ የማግኘት እና የመሥራት መብታቸው ያለቁጥራቸው ወይም ያለማንነታቸው ገደብ ሊከበርላቸው ይገባል። የአካባቢ አስተዳደሮች ይህ አረዳድ እንዲሰርፃቸው ያልተቋረጠ የብዙኃን መገናኛዎች ዘመቻ እና የግንዛቤ ማስበጫ ሥልጠናዎች ሊሰጧቸው ይገባል። (በነገራችን ላይ በብዙ ክልላዊ አስተዳደሮች ውስጥ በርካታ አማርኛ ተናጋሪ ነዋሪዎች ያሉ ቢሆንም፣ ከአማርኛ ተናጋሪዎቹ ቁጥር ያነሰ ተናጋሪ ያላቸው ቋንቋዎች የሥራ ቋንቋ ሳይሆኑ ሌሎቹ የሆኑበት ብዙ ምሳሌ አለ። የአማርኛ ተናጋሪዎቹ ቁጥር እና አሰፋፈር እስከፈቀደ ድረስ ልዩ የአስተዳደር ዞን፣ ወይም ተደራቢ የሥራ ቋንቋ መሆን የማይችልበት ሕጋዊ አግባብ የለም።)

2ኛ፣ ከትውልድ ክልላቸው ውጪ የሚኖሩ ግለሰቦች የሚኖሩበትን ክልል ሕግ እና ደንቦች (ፍትሓዊ ወይም በሁሉም ላይ የተጣሉ እስከሆኑ ድረስ) ማክበር አለባቸው። 

አንዳንድ ከትውልድ ቀዬአቸው ውጪ የሚኖሩ ዜጎች፣ ማኅበረሰቤ ብለው የሚጠሩት የተወለዱበትን እንጂ የሚኖሩበትን ቀዬ አይደለም። ይባስ ብሎ የተወለዱበት፣ ያደጉበትን ቀዬ ሳይሆን የወላጆቻቸውን ደም እና የትውልድ ቀዬ ቆጥረው ቀዬዬ ብለው የሚጠቅሱ አሉ። "የኔ" የሚሉትን ማኅበረሰብ መምረጥ የግል ድርሻቸው ቢሆንም የሚያስከፋው ነገር የሚኖሩበትን ማኅበረሰብ የሚንቁ ሰዎች መኖራቸው ነው። እነዚህኞቹ፣ በሚኖሩበት አካባቢ የአስተዳደር ችግር ሲደርስባቸው 'አቤት' የሚሉት ለሚኖሩበት ክልል አስተዳደር የላይኛው ክፍል ሳይሆን፣ ለመጡበት ክልል አስተዳደር ነው። ይህ ያልተማከለ አስተዳደር የሥልጣን ክፍፍልን የሚጋፋ እና በክልሎች መካከል ውጥረት የሚያነግሥ አካሔድ ነው። በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል አንድ ቀበሌ ውስጥ አስተዳደራዊ በደል የደረሰባቸው ዜጎች፣ ከዚያ በላይ ላለው አስተዳደር ወይም ፌዴራል መንግሥቱ ያመለክታሉ እንጂ ለመጡበት/ለሚወለዱበት ክፍል ማመልከት የለባቸውም። 

ዜጎቻችን አገር ለቀው ሲወጡ፣ የሚቀበላቸውን አገር ባሕልና ስርዓት አክብረው እንደሚኖሩ ሁሉ፣ በአገር ውስጥ ከአንዱ ቀዬ ወደሌላው ሲሔዱ፣ አዲስ ለሚኖሩበት አካባቢ ልማድ እና አሠራር (መሠረታዊ መብቶቻቸውን እስካልገፈፉ ድረስ) ተገዢ መሆን ይኖርባቸዋል። የአካባቢውን ደንብና ስርዓት አለማክበር የግጭት እንዲሁም የመፈናቀል መንስዔ ስለሆነ በዚህ መንገድ መከላከልም ይቻላል።

3ኛ፣ ብሔርተኞች ብሔርተኝነት በዘውግ ሳይሆን በክልል ላይ አስተሳሰቡን እንዲወስን ማድረግ አለባቸው። 

ይህ የዘውግ ብሔርተኝነት (ethno-nationalism) ከክልሎቹ ሥያሜ ይጀምራል። አማራ፣ ሶማሊ፣ አፋር፣ ሐራሪ፣ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልሎች ለምሳሌ በክልሎቹ በሚኖረው አብዛኛው ሰው ዘውግ ሥያሜ ነው ክልሎቹ የሚጠሩት። ከዚህ በተሻለ ኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ጋምቤላ እና ደቡብ ሕዝቦች ዐቃፊ አገላለጽ አላቸው። ይሁን እንጂ እነርሱም ብሔርተኝነታቸው ክልላዊ (territorial-nationalism) አይደለም። ለምሳሌ በኦሮሚያ ገዢው ፓርቲ ኦሕዴድ (የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት) እንጂ "የኦሮሚያ ሕዝቦች" አልተባለም። በኦሮሚያ የሚኖሩት ግን የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ብቻ ባለመሆናቸው ዐቃፊነት ይጎድለዋል። በዚያው ክልል ተቃዋሚው ኦፌኮ (የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ) ነው። የኦሮሚያ አለመሆኑ ብሔርተኝነቱ በክልሉ ያሉትን ሌሎች ዘውጎች እንዳያቅፍ ከሥሙ ጀምሮ እንቅፋት ይሆናል። የሌላ ዘውግ አባላት ለመብቶቻቸው ለመታገል እነዚህን ድርጅቶች መቀላለቀል አይችሉም ማለት ነው። በብአዴንም ተመሳሳይ ችግር ነው የምንመለከተው። በትግራይ አረና ምንም እንኳን በተግባር ባይሳካለትም በአስተሳሰብ ደረጃ ክልላዊ ፓርቲ ነው። የክልሉ ነዋሪ እስከሆኑ ድረስ ትግራዋይ ያልሆኑ ሰዎችም አረናን መቀላቀል ይችላሉ። 

ብሔርተኝነትን ክልላዊ ማድረግ በክልሉ ውስጥ ከብዙኃኑ ዘውግ ያልተወለዱ ሰዎች በክልሉ ውስጥ ውክልና እንዲኖራቸው ያደርጋል። ብዙዎቹ መፈናቀሎች የሚከሰቱት ሰዎቹን የሌላ ክልል ሰው ናቸው ብሎ ከሚያስብ በመነጨ አስተሳሰብ ነው። ነገር ግን ሰዎች አንድን አካባቢ መርጠው በሕግ አግባብ ነዋሪ እስከሆኑ ድረስ መወከል የሚኖርባቸው በሚኖሩበት አካባቢ እንጂ ጥለውት በመጡት አካባቢ መሆን የለበትም። ብሔርተኝነት ክልላዊ ሲሆን በነዋሪዎቹ መካከል ያለውን የዘውግ ውጥረት ይቀንሳል። ለምሳሌ ያክል በኦሮምያ ክልል ላሉ አማራዎች የአማራ ክልል ብሔርተኝነት ነው ጥብቅና የኦሮሚያ ብሔርተኝነት እንዲሆን ያደርጋል። 

4ኛ፣ የፌዴራል መንግሥቱ ከቀዬ ለመሰደድ እና የአገር ውስጥ ፍልሰት ፖሊሲ መቅረፅ አለበት። 

አዲስ አድማስ ጋዜጣ የጠየቃቸው አንድ ተፈናቃይ ወደትውልድ መንደራቸው ለምን እንደማይሔዱ ሲናገሩ ከትውልድ ቀያቸው የተሰደዱት የእርሻ መሬት አጥተው እንደሆነ ተናግረዋል። በርግጥም የአገር ውስጥ ፍልሰት ዋነኛው መንስዔ የእርሻ መሬት ለልጅ ልጆች ሲተላለፍ እየጠበበ ቤተሰብ ማስተዳደር ባለመቻሉ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ብዙ ግዜ በመታረሱ መሬቱ እየነጠፈ ራሳቸውን ለማስተዳደር ሌላ ቦታ ሔደው ማረስ ስለሚገደዱ ነው። እነዚህ ከቀያቸው በችግር የፈለሱ ዜጎች ሌሎች መንደሮች እየሔዱ ጫካዎችን በመመንጠር፣ የግጦሽ መሬቶችን በመውረር እና በሌሎችም ሕጋዊ በሆኑና ባልሆኑ መንገዶች የሚቀይሱት መንደር ከሔዱበት አካባቢ ሰዎች ጋር ግጭት ውስጥ እየከተታቸው ነው። ስለሆነም ይህ ችግር እየተባባሰ ይሔድ እንደሆነ እንጂ እየቀነሰ የሚሔድ አይመስልም። ሆኖም የፌዴራል መንግሥቱ ይህንን ጉዳይ አቅጣጫ ለማስያዝ የሚያስችል ፖሊሲ የለውም። ችግሩ አንድም ከሕዝብ ብዛት ጋር የሚያያዝ ነው። ይሁን እንጂ ያለፉት ሁለት የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች የሕዝብ ብዛትን በተመለከተም ይሁን የአገር ውስጥ ፍልሰትን በተመለከተ ያስቀመጡት አቅጣጫ የለም። ይህ ለቀውሱ መባባስ ብቻ ሳይሆን አፋጣኝ የእርምት እርምጃ መውሰድ እንኳን እንዳይቻል አድርጓል። 

5ኛ፣ መጠባበቂያ ፈንድ መመደብ።

ምንም እንኳን ዋናው ሥራ መፈናቀልን መከላከል ቢሆንም ከሆነ በኋላም ሰብአዊ እርዳታ ለተፈናቃዮቹ በአስቸኳይ ሊደርስላቸው ይገባል። በበጀት ረገድ ምን እየተሠራ እንደሆነ አላውቅም። የሆነ ሆኖ የዘንድሮን ያክል የከፋ ባይሆንም መፈናቀል በእየዓመቱ እየተከሰተ ነው። በአሁኑ ወቅት ብዙዎቹ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ ናቸው። ግዜያዊ መጠለያዎቹ መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለሟሟላት እንኳ አይችሉም። የንፅህና መጠበቂያ እና መፀዳጃ ሥፍራዎች አልተመቻቹላቸውም። ከምግብና መጠጥ እጥረቱ በተጨማሪ መሠረታዊ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ናቸው። በዚያ ላይ ጊዜያዊ መጠለያዎቹ ውስጥ ሳይገቡ በአካባቢው ሰዎች ተጠግተው የሚኖሩም አሉ። ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር መንግሥት መጠባባቂያ በጀት በዚህ ሥም ማዘጋጀት እና የሰብአዊ እርዳታ ማድረግ እንዲሁም መልሶ ማቋቋም ይኖርበታል። 

Friday, June 1, 2018

የተቃውሞው ጎራ ለምን ደነገጠ? (What to do next?)

ኦሕዴድ እና ብአዴን በሕወሓት የበላይነት ይመራ የነበረውን የኢሕአዴግ ፖለቲካ ከውስጥ መነቅነቅ ሲጀምሩ ተቃዋሚዎች ተደስተው ነበር። ኦሕዴድ በክልሉ አንፃራዊ የተቃውሞ-ነጻነት ሲፈቅድም እንዲሁ ተደስተዋል። ነገር ግን የዐብይ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እና የተቃዋሚውን ቋንቋ መነጋገራቸው ድንጋጤ ፈጥሯል። ባጭሩ ተቃዋሚዎች ከኢሕአዴግ ጋር "መደራደር ይገባናል" ሲሏቸው የነበሩት ጉዳዮች - የፖለቲካ እስረኛ ማስፈታት እና አንዳንድ አዋጆችን ማሻሻል፣ በጥቅሉ የፖለቲካ ምኅዳሩን የማስፋት ጥያቄ እና ተቋማትን ከፖለቲካ ጥገኝነት ማላቀቅ - የመሳሰሉትን ነገሮች በራሳቸው በኢሕአዲጉ ሊቀ መንበር ሲቀነቀን፣ ተቃዋሚዎች አጀንዳ አጥተዋል። የድንጋጤያቸው ምንጭም ይኸው ይመስላል። በርግጥ የፖለቲካ ድርጅቶቹ ሲያልፉበት ከነበረው ፈታኝ ሁኔታ አንፃር በመዳከማቸው የፖለቲካ ለውጦችን እያዩ ከወቅቱ ጋር የሚሔድ ፖለቲካ መጫወት ቢያቅታቸው የሚገርም አይደለም። 

የፖለቲካ ድርጅቶቹ "የአኩራፊዎች እና የጡረተኞች መሰብሰበቢያ" እየተባሉ ሲተቹ ከርመዋል። ምንም እንኳን ከላይ ያሉ ቢመስልም ውስጣቸው በብዛት ባዶ ነው። ለኢትዮጵያ (100 ሚሊዮን ሕዝብ) የሚመጥን የመምራት አቅም ያላቸው ሰዎች ስብስብ የላቸውም። በመገናኛ ብዙኃን በሚራገቡ አጀንዳዎች ላይ የመንግሥትን አቋም ካወቁ በኋላ ተቃራኒውን ይዘው ከመሟገት በላይ ርዕዮተ ዓለማዊ አቅጣጫ የሌላቸው ድርጅቶች ቀላል አይደሉም። አንዳንዶቹ ከላይ ያሉትን ታዋቂ ሊቀ መንበሮቻቸውን የሚተኩ አባላት እንኳን አላፈለቁም። ኢትዮጵያን መምራት የሚችሉ በርካቶች ድግሞ ወይ የፖለቲካውን ትኩሳት እየፈሩ አንገታቸውን ደፍተው 'ዝምተኛ-ብዙኃን' መሐል ተቀብረዋል፤ አልያም ተሰድደዋል። በዚህም ምክንያት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶቹ የኢሕአዴግ የፖለቲካ አጨዋወት ሲቀየር፣ የራሳቸውን አጨዋወት በመቀየር ፈንታ ድንጋጤ ውስጥ መግባታቸውን የሚያሳብቁ ነገሮች ናቸው አሁን የሚታዩት። "እስረኛ የፈቱት ወደው ሳይሆን ተገደው ነው"፣ "ሰውዬው ኢሕአዴግ ናቸው፣ ኢሕአዴግ ከሚቀየር ግመል በመርፌ ቀዳዳ…"፣ "ጥቂት ሰዎች ተቀየሩ ማለት ነገሮች ተቀየሩ ማለት አይደለም"፣ "ይች ይቺ ተቃውሞ ለማስቆም የተፈጠረች የኢሕአዴግ ሴራ/ድራማ ናት"… እነዚህ ንግግሮች ለቀጣዩ የፖለቲካ ጫወታ ፋይዳቸው ምን እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእያንዳንዱ ንግግራቸው እና ድርጊታቸው የብዙዎችን ቀልብ እየገዙ እና "አለቀለት" ለተባለው ኢሕአዴግም አዲስ ነፍስ እየዘሩበት ነው። ይህ የገባቸው ተቃዋሚዎች የማጥላላት እና የማጣጣል ትርክት ለመፍጠር እየተፍጨረጨሩ ነው። ይህ ፖለቲካዊ ኪሳራ ሊያስከትል ይችላል።  የሴራ ፖለቲካዊ ትንተና እና ጫወታም መሬት ላይ ጠብ የሚያደርገው እንደሌለ ከበቂ በላይ ታይቷል። የብሽሽቅ ፖለቲካም ጉንጭ ከማልፋት በላይ ትርፍ የለውም። ሕዝብን "ተታልላችኋል" እያሉ መውቀሱም አግባብ አይደለም። ምክንያቱም ሕዝቡ የሚያየውን መዳኘት ይችላል።

ይልቁንም (በፖለቲካ ምኅዳሩ መጥበብ ምክንያት የተከተለው እና ሁለተኛው ደረጃ) "የማማረር ፖለቲካ" ተላቅቆ፣ ወደ አንደኛው ደረጃ ፖለቲካ ማለትም አማራጭን የማሳየት እና ሕዝባዊ መሠረት የመጣል ፖለቲካ መጫወት ያስፈልጋል። የፖለቲካ ምኅዳሩ ለይቶለት ሳይዘጋ በፊት ለእስር እና ስደት የተዳረጉት ፖለቲከኞች ጥያቄ ምንድን ነበር? የሕዝቦች ጥያቄ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደኅንነት እንዴት ነው የሚጠበቀው? ድንቁርና እና ድህነትን እንዲሁም ኢፍትሓዊነትን ለመቀነስ አገራችን ምን ዓይነት የፖለቲካ ስርዓት መከተል አለባት? አሁን ሰዐቱ ይህንን የመመለስ ነው። 

የፖለቲካ ድርጅቶች የሚሠሩት ሥራ በየአደባባዩ ሰልፍ ከመውጣት እና የተቃውሞ መግለጫዎችን ከማውጣት በላይ ነው። አብላጫ የምክር ቤት ወንበር አግኝተው መንግሥት ሲመሠርቱ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ አማራጭ በመኖራቸው ብቻ የሚሠሯቸው ሥራዎችም ብዙ ናቸው። በዋነኝነት አማራጭ የአገር አመራር አቅጣጫ ማሥመር አለባቸው። አገሪቱ ወዴት ነው መሔድ ያለባት? እንዴት ነው ወደዚያ መሔድ የምትችለው? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ የማኅበረ–ኢኮኖሚያዊ ፍልስፍናቸውን ለሕዝብ ማስተዋወቅ አለባቸው። ለዚህ ደግሞ ብቁ የሆኑ አመራሮችን መሰብሰብ እንዲሁም እየኮተኮቱ ማሳደግ አለባቸው። አለበለዚያ እንደሥማቸው ተቃዋሚ ብቻ ሆነው ይቀራሉ። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "ተፎካካሪ" የሚለውን መጠሪያ እንደአስታራቂ መርጠዋል። እኔ እስካሁን ያለውን ፖለቲካ የገዢ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፖለቲካ ብለው እመርጣለሁ። ምክንያቱም ገዢው ፓርቲ አገር ለመምራት ወይም ሕዝብ ለማገልገል ሳይሆን ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ለመሆን ነው ሲተጋ የኖረው። ተቃዋሚዎች ደግሞ የገዢውን አገዛዝ ሲቃወሙ እዚህ ደርሰናል። ኢሕአዴግ መቀ:የር እፈልጋለሁ ብሎ ጭላንጭል ሲያሳይ፣ የነገውን ለነገ ትተው ተቃዋሚቹም መቀየር አለባቸው። እውነተኛ አማራጭነታቸውን ለማሳየት አጋጣሚውን መጠቀም ይኖርባቸዋል። አለበለዚያ ነገ ኢሕአዴግ ስህተት እስኪሠራ ጠብቆ "ይኸው ይሄንኑ ፈርተን ነበር" ማለት አያዋጣም፤ በሥሙ ብዙ ነገር ለሚፈፀመው ሕዝብም የሚያተርፍለት ነገር የለም። ምንም እንኳን ወደፊትም የመሔድ ወይም ወደ ኋላ የመመለስ ዕድሉ ዕኩል ቢሆንም አሁን (በዚህ ቅፅበት) ከሞላ ጎደል ሰፊ የፖለቲካ ምኅዳር አለ። የፖለቲካ ምኅዳሩ ስፋት ወደኋላ እንዳይመለስ ሕጋዊ እና ተቋማዊ መሠረት አፍርቶ ለዘለቄታው ዋስትና እንዲያገኝ ከመሥራት ጎን ለጎን አማራጭ የፖለቲካ መፍትሔን ለሕዝብ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል። ሕዝብ ውስጥ የሰረፀ ፖለቲካዊ የመፍትሔ ሐሳብ ካለ፣ አመንጪዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች ባይኖሩም እንኳን የግዜ ጉዳይ ቢሆን ነው እንጂ ግቡን ይመታል።

አማራጭ የፖለቲካ ሐሳብ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ካሉ እኛም "ገዢ" እና "ተቃዋሚ" እያልን ከመፈረጅ እንገላገላለን። "ተፎካካሪ" ከሚለው እና የሥልጣን ሽሚያን ብቻ ከሚጠቁመው ቃልም ይልቅ "አማራጭ" የፖለቲካ ድርጅቶች የሚለውን እንጠቀማለን። አማራጭ የፖለቲካ ድርጅቶች ካሉ፣ የድርጅቶቹን ሥም ስንሰማ የገዢውን ሐሳብ በመቃወማቸው ሳይሆን፣ በአማራጭ ሐሳባቸው እናስታውሳለቸዋለን። 'ምረጡን' ብለው ሲመጡም እንደተቃዋሚ "ተቃውሟቸውን" ወይም እንደ ተፎካካሪ "ፉክክራቸውን" ሳይሆን አማራጭ ሐሳባቸውን እንመርጣለን። 

Time to move on, and choose your place in the board. 

Sunday, May 20, 2018

ሰው መሆን…

የሰው ልጆች ሰው ለመሆን ማለቂያ የሌለው አብዮታዊ ጉዞ ውስጥ ናቸው፡፡ እንደመታደል ሆኖ፣ የሰው ልጆች የላቀ እና እየላቀ የመጣ አእምሮ ባለቤት በመሆናቸው ምድርን እንደግል ንብረታቸው፣ ራሳቸውንም ተለይቶ እንደተመረጠ ፍጡር እየቆጠሩ፣ ምድርን ለራሳቸው ምቾት እያሾሩ ዛሬ ላይ ደርሰዋል። የሰው ልጆች በሠለጠኑ ቁጥር ርሕራሔያቸው እየጨመረ፣ አውሬነታቸው እየቀነሰ መጥቷል። የራሳቸውን ነጻነት የሚያከብሩትን ያክል የሌሎችንም ለማክበር እየተጉ መጥተዋል። የሰው ልጆች ዛሬ ከራሳቸው አልፈው ስለአካባቢያቸው ብዝኃ ሕይወት እስከመጨነቅ ደርሰዋል። የሰው ልጆች ረዥም ጉዞ ገና አላለቀም። የሰው ልጆች ሰው የመሆን ጉዞ የት ተጀመረ? በየት በኩል አለፈ? ዛሬ የት ደረሰ? ነገስ ወዴት ይጓዝ ይሆን? የዚህ መጣጥፍ ዓላማ የሰው መሆንን ጉዞ በወፍ በረር በመቃኘት የሰውነትን ዓላማ መገመት ነው።

ቶማስ ፍሬድማን ሉላዊነት 3ኛው ደረጃ ላይ እንደደረሰ ጽፏል። የመጀመሪያው ደረጃ የአገረ-መንግሥታት እርስበርስ መተሳሰር ነው። ሁለተኛው ደረጃ የንግድ ኩባንያዎች ብዙ አገራት ላይ መሥራት መቻልና እርስ በርስ ግንኙነት ነው። የመጨረሻውና ሦስተኛው ደረጃ የሰዎች ድንበር ዘለል የአንድ ለአንድ ግንኙነት፣ የትብብር እና የውድድር ዕድል መጨመሩ እና መጠናከሩ ነው። እውነትም ዛሬ ሉላዊ ዜጋ (global citizen) መሆን ከመቼውም ግዜ በላይ ቀሏል። ይህ ክስተት የሰው መሆን ጉዞ አቅጣጫ ድንበር የለሽ የዓለም ዜጋ መሆን መሆኑን ይጠቁመን ይሆን?

በዓለማችን አሁን ላይ በአንድ ወቅት 7 ሺሕ ገደማ ቋንቋዎች ነበሩ። በአጥኚዎች ትንበያ መሠረት ከነዚህ ውስጥ በመጪዎቹ መቶ ዓመታት ውስጥ የሚቀሩት መቶዎቹ ብቻ ቢሆኑ ነው። በተረፈ ቀሪዎቹ ወይ ተናጋሪ በማጣት፣ ወይ ከሌላ ጋር ተዳቅለው አዲስ ቋንቋ ተወልዶ፣ ወይም ደግሞ በሌላ ምክንያት ይሞታሉ። በዚህ አካሔድ ስንገምተው ምናልባትም የሆነ ግዜ ዓለማችን ጥቂት ወይም አንድ ቋንቋ ብቻ የሚናገር የሰው ዘር መኖሪያ ትሆናለች። ይህ ምንን ያመለክታል? የሰው ልጅ ብዙ ሆኖ ጀምሮ አንድ ሆኖ እንደሚጨርስ? ወይስ፣ በሒደቱ ከአንድ ወደ ብዙ ከዚያ መልሶ ወደ አንድ-ነት እንደሚጓዝ? ሌላም፣ ሌላም…

ጥንት የሰው ልጆችን ከአንድ ሥፍራ ከመንቀሳቀስ የሚያግዳቸው ተፈጥሮ ብቻ ነበር። ዛሬ ዛሬ፣ ተፈጥሮ በሰው ልጆች ቁጥጥር ሥር እየዋለች በሔደች ቁጥር ሰው ሠራሽ ድንበሮች የሰውን ልጆች እንቅስቃሴ እየገደቡ ነው። ሆኖም አገረ-መንግሥታዊ ኅብረቶች፣ ንግድ እና ቴክኖሎጂ እነዚህን ሰው ሠራሽ ድንበሮች መልሰው እየሰበሯቸው ነው። ዛሬ የዓለም አገራት ድንበራቸውን አጥረው በአንድ ወቅት የሁሉም የነበረችውን ዓለም ተከፋፍለው የኔ እና የእናንተ ተባብለዋል። ጆርጅ ፍሬድማን መጪዎቹን መቶ ዓመታት በተነበየበት መጽሐፉ ይህ አይቀጥልም ይለናል። እሱ እንደሚለው 21ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የዓለማችን ኃያላን አገራት እንደዛሬ ሳይሆን ስደተኞችን መፀየፍ አቁመው በገንዘብ ለመግዛት እስከ መሻማት ይደርሳሉ። ይህንን እውነት ይሆናል ብለን እንገምትና የሰው ልጅ የነገ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚመስል በምናባችን እንሳል። ግምታችን ለእውነቱ እንዲቀርብ ግን ያለፈውን ግዜ ከጥንስሱ ጀምሮ በጨረፍታ እናስታውሰው።

Sunday, April 29, 2018

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከራሳቸው ማዳን!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተስፋን-በጥንቃቄ (cautious optimism) ካነገቡት ሰዎች አንዱ ነኝ። የተስፋዬ መሠረቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን የመጡበት መንገድ፣ የገቧቸው ቃልኪዳኖች እና አሁን የታየው መረጋጋት ናቸው። አሁን የታየው መረጋጋት ስል የቄሮዎች የአደባባይ ተቃውሞ መቆሙን ማለቴ አይደለም። ተቃዋሚዎችን እያሳደዱ መከታተል፣ ማዋከብ እና ማሰር ርቀን ሳንሔድ አምና ከነበረው አንፃር እንኳ ልዩነቱ የትየለሌ ነው። ለዚህ የራሴን ስሜት እና ተሞክሮ ነው በምሳሌነት የማቀርበው። በፊትም አሁንም ሐሳቤን በነጻነት እገልጻለሁ። ነገር ግን አምና እና ካቻምና ከያንዳንዱ ጽሑፎቼ/ንግግሮቼ ቀጥሎ እስር ይመጣል እያልኩ እየሰጋሁ ነበር የማደርገው። አሁን ምን ያክል ይዘልቃል የሚለው ቢያሰጋኝም እታሰራለሁ እያልኩ በየደቂቃው አልባትትም። በፊት ሲያስሩ፣ ሲያዋክቡ እና ሲከስሱ ከነበሩት አንዳንድ ኃላፊዎችም ጋር ባጋጣሚዎች አውርቻለሁ። ከላይ ለውጥ ያለ ሲመስል እነርሱም ከታች ይለወጣሉ። አንድ ከፍተኛ የፌዴራል ፖሊስ ኃላፊ የኛን እንቅስቃሴ "የበፊቱ አመራር እንደ ወንጀል ያየው ስለነበር ወንጀል ነበር። አሁን ግን እንደወንጀል አይታይም" ብለውኛል። ይህ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰዎች ላይ የተፈጠረው የ"ለውጥ መጥቷል" ስሜት እና የፍርሐት ማጣት ከተጠቀሙበት ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ትልቅ ዕድል ነው። ሌላው ሌላው ሁሉ ለዘለቄታው ለመቅረፍ ረዥም የፖለቲካ እና የሥራ ባሕል አብዮት የሚፈልግ ፈርጀ ብዙ የሁላችንም ችግር ነው።

Saturday, April 14, 2018

From OPDO Sensation to Abiy Mania

In an inaugural speech, Prime Minister Abiy Ahmed Ali turned almost all pessimists in to EPRDF enthusiasts. It is like he has all traits of a leader 'naturally'. His charisma coupled with his fluency in three local languages of "the competing nationalities" made him look like the right person to fix the mess Ethiopian state is in. But, is he really the person to fix Ethiopia? Or, should we hope something else?

Overlaping Interests: Source of Support

It has been a bit long since OPDO officials pretend a dissenter within EPRDF. Their dissent was about their regional autonomy at first. This overlapped the interests of opposition groups and has gotten OPDOs unprecedented support from the protestors and general population. The overwhelming support OPDO received regionally encouraged them to have a deserved representation in the Federal Government. Besides, the regional autonomy was interfered by federal authorities who didn't like to accept OPDO's dissent. 

Revolutionary Democracy, EPRDF's ideology, is a practical application of twin principles: equality principle and democratic centralism. The former is about equal votes member parties of EPRDF have to make decisions regardless of differences in number of their respective constituencies; while the latter is about making all decisions centrally (top-down) contrary to genuine democratic principles of making decisions bottom-up. The new leadership of OPDO, under Lemma Megersa and Abiy Ahmed, has been seen divergent in this regard. Their divergence has been taken as rush to anarchy by some but welcomed by many others as progress to reform. OPDOs divergence has been witnessed when House of Peoples Representatives (HPR) passed the second State of Emergency. Contrary to the democratic centralism principles, most OPDO representatives voted against it. This was, with other multiple incidents, unusual gesture of change leading to overlapped interests to opposition groups from a member party of EPRDF.

Subdued Background: Cause of Suspicion

The establishment of OPDO is embarrassing. The founders were surrenders of TPLF during the armed insurgency before 1991. They were advised and organized as per the standards and principles of TPLF. EPRDF's establishment was made convenient to TPLF's targeted regime and its structure. The member parties, including OPDO, are now regional parties but their respective regions didn't exist when they were established. TPLF manipulated a transitional government to restructure the country in a way it had already planned. In this way, the member parties were able to have regional governments to administer with supervision of TPLFites in the Central Committee (CC) of EPRDF. Even though there was equality principle in the CC, bosses (TPLFites) and their subordinates (OPDOs and others) could not have equal confidence to discuss matters objectively.

Monday, March 19, 2018

Resignation of the Prime Minister: Beginning of Collapse to EPRDF or of Reform?

(Recap the Past Decades of EPRDF's Rule)

It all started when the Ethiopian national election ended in crisis 13 years ago. But, it became very interesting when the beginning of an end of an era gives a hint with the resignation of a Prime Minister for the first time in Ethiopia's experience. 

On the 15th of February 2017, expected yet surprising breaking news hit Ethiopian media. The Prime Minister wrote a letter of resignation from both his premiership of the country and chairmanship of the ruling coalition of Ethiopian People's Democratic Revolutionary Party, EPRDF. Prime Minister Hailemariam Desalegn's resignation was expected because it was rumored; and, it was also surprising because the news came earlier than the long-awaited EPRDF conference which is a feast of reshuffle. The resignation is a combination of both lack of his competency and manifestation of internal dispute within the coalition. 

Thirteen years ago, the contested national election in 2005 ended in crisis when the government jailed leaders of major opposition group - Coalition for Unity and Justice (CUD), civil society members and journalists. It was followed by massive closure of the free press and civil society. What started in a de facto repression became de jure when the House of People's Representatives (HPR) that was overwhelmingly dominated by EPRDF passed two proclamations in 2009. One of the proclamations is the infamous Anti-Terrorism Proclamation (ATP), which used as an excuse to jail thousands of politicians, activists, journalists and bloggers. The other is Charities and Societies Proclamation (commonly known as CSO law), which restricted the working space and finance source of civil societies consequently forcing out many civil rights organizations. 

Saturday, March 17, 2018

የኢትዮጵያ ስርዓተ ናሙና እውን (ከሕግ አንፃር) ፌዴራላዊ ሊባል ይችላል?

(ይህ ጽሑፍ በ1992 ከታተመው "Ethnic Federalism in a Dominant Party State: The Ethiopian Experience 1991-2000" ከሚለው የሎቪስ አለን ጥናት ውስጥ ካለ ንዑስ ርዕስ ተቀንጭቦ የተተረጎመ ነው።)

በሽግግር መንግሥቱ ግዜ የታተሙት ዐዋጆች ሁሉ ክልሎች እና ንዑስ ክፍሎቻቸው የማዕከላዊ መንግሥቱ ምንዝሮች እንደሆኑ ተመልክቷል። የሽግግር ምክርቤቱ ለብሔሮች ‹የራስን ዕድል በራስ መወሰን› የሚል ቃል በስተቀር የክልሎች ሥልጣን የተገደበ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተማከለ፣ አሀዳዊ፣ ወይም ፌዴራላዊ ስለመሆኑ ምንም አይታወቅም ነበር። የ1987ቱ ሕገ መንግሥት ግን ይህንን ግራ መጋባት ቀርፎታል። አሀዳዊውን ስርዓት በመተው ፌዴራላዊውን እንደሚከተል በግልጽ ያስቀምጣል (አንቀፅ1)። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የፌዴራል አወቃቀር ላይ በርካታ እንግዳ እና አሻሚ ነገሮች አሉ። ይህም ከነባር ፌዴሬሽኖች የፌዴራል ኅልዮት እና አተገባበር አንፃር ይገጥማሉ ወይም ይጋጫሉ የሚለውን የመደምደሙን ነገር  ከባድ ያደርገዋል። የመገንጠል መብት፣ ለፌዴሬሽኑ አባል አገረ-መንግሥታት ፈንታ ሉዓላዊነት "ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች"  መሰጠቱ፣ ገለልተኛ የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት አለመኖር፣ እና ጠንካራው የሥራ አስፈጻሚ አካል ለዚህ ውስብስብ ባሕሪው ተጨማሪ ምክንያቶች ናቸው።

የክልሎች ሥልጣን ተቃርኖ

በኢትዮጵያ ፌዴራል አወቃቀር ግልጽ የሆነ አያዎ እንዳለ ብዙ ጸሐፊዎች አስፍረዋል። በአንድ በኩል ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የተወሰኑ ሁኔታዎችን አሟልተው የመገንጠል መብት ተሰጥቷቸዋል። ይህ ከሌሎች የፌዴራል ስርዓታት በተለየ የፌዴራሉ አካላትን ነጻነት የተለጠጠ ያደርገዋል። በሌላ በኩል፣ የአባል አገረ-መንግሥታቱ ሥልጣን በአንፃሩ በጣም ውሱን ነው። የክልል መንግሥታቱ ሥራቸውን ለመሥራት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ጥገኛ ናቸው። በብሬዝኬ እንደተገለጸው፣ ሕገ መንግሥቱ "ጥቂት የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብቶችን መድኅን" ያቀርብና፣ እስከ መገንጠል በሚለው መካከል ምን እንዳለ ስላልተገለጸ፣ ጠባብ የራስን ዕድል የመወሰን ቅርፅ እና የተገደበ የባሕል ነጻነት ያጎናፅፋል።"

ዱካቼክን ጨምሮ የተወሰኑ የፌዴራሊዝም አጥኚዎች የመገንጠል መብት አንድን አገረ መንግሥት ፌዴራላዊ ለመባል እንዳይበቃ ያደርገዋል በማለት እስከመከራከር ይደርሳሉ። የመገንጠል መብት ዜጎች ለማዕከላዊ መንግሥቱ ያላቸው ታማኝነት ቀስ በቀስ እንዲቀንስ ያደርገዋል። በተጨማሪም፣ ክልሎች ኅብረቱን የመልቀቅ ነጻነቱ ሲኖራቸው፣ በማዕከሉ እና አገረ መንግሥታቱ መካከል ያለው የፖለቲካ መዋቅር ከፌዴሬሽን ይልቅ የላላ ንዑስ ብሔራዊ ቁጥጥር ያለው ኮንፌዴሬሽን ዓይነት ይሆናል። ሉዓላዊነት ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መሰጠቱም ቢሆን ብሔረሰቦች ከፌዴሬሽኑ ብቻ ሳይሆን ከክልሉ አገረ መንግሥታት ሳይቀር እንዲገነጠሉ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ያልተለመደ ሕገ መንግሥታዊ ስርዓት ከመሆኑም ባሻገር የሚመስለው አንድም የፌዴራል ስርዓት ዛሬ ላይ የለም። የመገንጠል መብት መኖር ኢትዮጵያን ፌዴራላዊ ለመባል አያበቃትም የሚለው እንደ አስተያየት ሰጪው ይወሰናል። ሌሎች የፌዴራል ስርዓቶችን ብንመለከት፣ አንዳንድ የዘውግ ቡድኖችን ወይም ክልሎችን የመገንጠል መብት የሰጡ ስርዓቶች አሉ። ነገር ግን እነዚህኞች ከሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች ውጪ የተሰጡ ናቸው።

Wednesday, March 14, 2018

የኃይሌ ገ/ሥላሴ ችግሩ፣ በሀብት መክበሩ!

ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ የዛሬ 8 ዓመት ገደማ፣ በመስከረም ወር 2003ቱ የኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ ተገኝቶ ንግግር አድርጎ ነበር። እናም "እናንተ ፖለቲካውን ሥሩ፣ ንግዱን ለኛ ተዉልን" የሚል ንግግር አድርጓል። ንግዱን አልተዉለትም። ሆኖም ምንጩ በሚታወቀው ሀብቱ እየተፎካከራቸው ነው። እነርሱ በወቅቱ የፈለጉት በሕዝቡ የሚወደደውን ሰው ወደ መድረካቸው በማምጣት ከሕዝባዊ መውደዱ መሻማት/መፎካከር ነበር። ከዚያ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ግዜ ክብረወሰን ሲሰብር የለበሰውን ቲሸርት ለወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሥጦታ አበረከተላቸው። መብቱ ነው ግን ይህም አልበቃው፣ በአትሌቲክስ ሜዳ ክብረወሰን ሲሰብር ከተሰማው ደስታ ይልቅ እዚያ መድረክ ላይ በመገኘቱ የተሰማው ደስታ እንደሚበልጥ ተናገረ። ይሁን። ዞሮ ዞሮ ግን ኃይሌ ለዚህ ሙገሳው በምላሹ የጠየቀው 'ውለታ' "ንግዱን ተዉልን" የሚል ብቻ ነበር። በርግጥ ከዚያ በፊት "የአገር መሪነት ማን ይጠላል?" የሚል ቃል ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፤ የግንባሩ አባል ቢሆን የሆነ የአመራር ቦታ የሚከለክሉት አይመስለኝም። ሆኖም ከዚያ በፊት የነበረው የፖለቲካ ልምድ ግን የቅንጅት አመራሮችን በሽምግልና ሥም ይቅርታ ያስፈረመው የአገር ሽማግሌዎች አባልነት ብቻ ነበር። 

ኃይሌ ገብረሥላሴን በመተቸት ለመጻፍ ስንጀምር "ኃይሌ ለአገር ውለታ የዋለ፣ ከአትሌቲክስ ጡረታ ቢወጣም በኢኮኖሚው መስክ ብዙ ሰው ለመቅጠር የበቁ ኢንቨስትመንቶች ላይ የተሠማራ" የሚሉ ማባበያዎችን ማስቀመጥ እንደ ደንብ ተቆጥሯል። እኔ ይህን አላደርግም። ለትችት የሚቀርቡት ሰዎች ስለአገር ምንም ውለታ ያልዋሉ ሰዎች ናቸው ማለት አይደለም። ሁሉም የአቅሙን አዋጥቷል። ኃይሌም ቢሆን በፍትሕ ዓይን ከማንም አይበልጥም። አሁን በኢትዮጵያ ያለው ተቃውሞ ደግሞ የፍትሓዊነት ጥያቄ ነው። የፍትሓዊ አስተዳደር፣ የፍትሓዊ ውክልና፣ የፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል፣ የፍትሓዊ ዳኝነት፣ ወዘተ።

ከሁለት ዓመት በፊተ፣ በሕዳር ወር 2008 ቢቢሲ ሬድዮ ላይ ቀርቦ የነበረው ኃይሌ "ዴሞክራሲ ለአፍሪካውያን ቅንጦት ነው" ብሏል። 'ዳቦ ይቅደም' ማለቱ ነው። ሆዱን ያልሞላ ሰው ነጻነት አያስፈልገውም ከሚለው "የባርነት ለዳቦ" አስተሳሰብ ጋር የተስተካከለ አባባል ነው። አንድም በድሃ መሳለቅ ሲሆን፣ አንድም ደግሞ በዘር መፈረጅ ነው። ኃይሌ ለመናገር ያለው ድፍረት መልካም ነበር። የሚያሳዝነው ለሚናገረው ነገር ይዘት እና ውጤት ቅንጣት አለመጨነቁ ነው። ብዙ ሰዎች በሱ ንግግር የሚበሳጩት ካለው ሕዝባዊ ተቀባይነት አንፃር ንግግሩ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ነው። 'ከነጻነት ዳቦ ይቀድማል' የሚል መልዕክት ያለው ንግግር ሲያደርግ፣ ለሕዝቡ ጭቆናውን ለልማት ሲባል ቻሉት ማለቱ ነው፤ ለመንግሥቱ ደግሞ ሕዝባችሁን ዳቦ እየሰጣችሁ፣ ብትረግጧቸው ምንም አይለይም እያለ ነው። ነገሩ ከዘረኛ ነጮች አመለካከት ጋርም ይሠምራል። ለቅኝ አገዛዝ የተሰጠው አስተያየት (ማብራሪያ) ተመሳሳይ ነው። አፍሪካውያን ድህነት ይዘው እንጂ የምዕራባውያኑን ልብስ ቢያጌጡበት ያምርባቸዋል። የተመጣጠነ ምግብ ቢበሉ ይስማማቸዋል። እንደ ሕዝብ ሉዓላዊነታቸው ቢከበርላቸው ደስ ይላቸዋል። አፍሪካዊ ስለሆኑ የቅንጦት አይሆንባቸውም። ልማትና ዴሞክራሲም የሚጣረሱ ነገሮች አይደሉም። ሁለቱንም ባንዴ ማቅረብ ይቻላል። አፍሪካውያንም እንደሌላው ሁለቱንም ባንዴ ቢያገኙ አይጠሉም።

ከሰሞኑም በድጋሚ ኃይሌ አወዛጋቢ መልዕክቱን በድጋሚ አስተላልፏል። በኢቢሲ ከፓስተር ዳንኤል ጋር ቀርቦ የተናገረው ንግግር ውስጥ የሚያስቆጣ ይዘት ያላቸው ንግግሮች ደንቅሯል። ለምሳሌ "የውጭ እንትን ያለበት… የሚታይበት ነገር" በማለት የገለጸው እና በኋላ ሲተነትነው የግብጽ ስፖንሰርነት አለበት ለማለት እንደፈለገ የሚያስታውቀው ንግግሩ አንዱ ነው። ኢትዮጵያውያን በቂ ብሶት የሌላቸው ይመስል የመንግሥትን ፕሮፓጋንዳ ሰምቶ የውጭ ተልዕኮ አስፈፃሚዎች ሥራ ማስመሰል ተገቢ አይደለም። የውጪ ኃይሎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ተቃውሞ ሊደግፉ ይችላሉ እንጂ ሊፈጥሩት አይችሉም። አለቀ። 

ሲቀጥል ደግሞ "ቤት በመዝጋት፣ ትራንስፖርት በመዝጋት" መቃወም "የትም አገር የሌለ" ነገር ነው። ብሎ አጣጥሎታል። በመሠረቱ ኃይሌ ብዙ አገራት መሔዱ እውነት ነው። ነገር በሔደባቸው አገሮች ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ስርዓት፣ ለተቃዋሚዎች ተሳትፎ የሚሰጡትን ቦታ እና የሕዝብን ጥያቄ የሚያስተናግዱበትን መንገድ ያጠና ወይም ለማጥናት ግዜ ያገኘ አይመስለኝም። 

ሕዝቦች ወይም የሕዝብ ክፍሎች ጥያቄ ወይም ቅሬታ ሲኖራቸው፣ ሲያሻቸው በመሾምና በመሻር፣ ሲያሻቸው ፖሊሲ በማስወጣት እና በማስከለስ የሚኖሩበት ዘመን ላይ ነን። የኛው መንግሥት ደግሞ መጀመሪያ በነፍጥ ራሱን ሾመ፣ በመቀጠል ፍትሓዊ ባልሆኑ የምርጫ ሒደቶች ሥልጣኑን አስቀጠለ። የሕዝብ ወኪል ማኅበራትን እና ሚድያዎችን አደከመ። በዚህ መንገድ ተናጋሪ እራሱ፣ ፖሊሲ ቀራጭ እራሱ፣ ሁሉ ነገር ራሱ ከመሆኑ የተነሳ የተቃውሞ መንስዔዎቻችሁን ሳይቀር እኔ ራሴ ነኝ የምነግራችሁ አለ። ሕዝቦች በድርጅት የጀመሩትን ተቃውሞ አደናቀፈ። ድርጅቶች ፈርሰውና ተዳክመው ዜጎች በየፊናቸው መቃወም ቀጠሉ። 

ኃይሌ የተቃወመው የሠላማዊ ትግል መንገዶችን ነው። በመሠረቱ በሠላማዊ ትግል ሦስት ደረጃዎች አሉ። የመጀመሪያው ማግባባት ነው፤ በጽሑፍ፣ በሠልፍ… ብዙ ተሞክሮ ሰሚ አልተገኘም። ሁለተኛው፣ አለመተባበር ነው፤ መንግሥት መር ጥፋቶች ሲፈፀሙ የነዚያ ተግባራት አካል ላለመሆን ብዙ ተሞክሯል፣ እየተሞከረም ነው። ግን ሦስተኛውም ተጀምሯል። ጣልቃ መግባት፤ መንግሥት ለጥያቄዎች መልስ አልሰጥም ሲል እና ችግሮች ከድጡ ወደማጡ እየገቡ ሲያስቸግሩ ጣልቃ ገብቶ ይበቃል እንደማለት። ይህ ደረጃ ችግሩ እነርሱን ስለማይነካቸው ብቻ ሠላማዊ ትግሉን የሚቃወሙት ሰዎች የችግሩ ጥልቀት ባይገባቸውም ጫፍ ጫፉ እንዲታያቸው ማድረግ ነው። ችግሩ ከማይገባቸው ሰዎች መካከል የናጠጡ ሀብታሞች ይገኙበታል። 

በመሠረቱ የኃይሌ ችግር የብቻው አይደለም። የሙለር ሪል ኢስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ ከአንድ ታዋቂ የጀርመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ዝግጁ አይደለችም" ብለዋል። የሚገባቸው መልስ ከላይ ለኃይሌ ከተሰጠው የተለየ ሊሆን አይችልም። ጥያቄው 'ሀብታሞችን ከሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተፃራሪ የሚያቆማቸው ምንድን ነው?' የሚል ነው። 

ለመልሱ ደጋግሜ ወደጠቀስኩት የአሴሞግሉ እና ሮቢንሰን 'Economic Origin of Democracy and Dictatorship' የሚል መጽሐፍ ላይ ያገኘሁት ኅልዮትን ልዋስ። የኢኮኖሚ ልኂቃን ሁሌም የአምባገነንነት ደጋፊዎች ናቸው። የሀብት ክፍፍል በሰፋ ቁጥር ሕዝቦች ያምፃሉ። ይህ ዴሞክራሲ በግዚያዊነት ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። ነገር ግን አሁንም የኢኮኖሚ ልኂቃኑ የመንግሥት ግልበጣ ደግፈው በኢኮኖሚ የብቻ የበላይ የሚያደርጋቸውን አምባገነናዊ ስርዓት ያቆማሉ። ማለትም ከድሀው ብዙኃን እጅግ የራቀ ሀብት ያላቸው ባለፀጎች ባሉበት አገር ዴሞክራሲ አይፈጠርም፤ ቢፈጠርም አይፀናም። ኃይሌ ገ/ሥላሴ እና ሌሎቹም ባለፀጎች ኢትዮጵያ እና አፍሪካ ለዴሞክራሲ እንዳልተዘጋጁ የሚናገሩት ወይም እንዳይዘጋጁ የሚፈልጉት የኢኮኖሚ ልኂቅነት ጥቅማቸውን (privileges) ለማካፈል ስለሚቸግራቸው ነው። 

አሁን ኃይሌ በይፋ ፖለቲከኛ መሆን እንደሚፈልግ እየተናገረ ነው። ፖለቲከኝነት የሕዝብን ውክልና አግኝቶ ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚሠራበት መሆኑን ተረድቶ፣ ይህን የኢኮኖሚ ልኂቅነት ቦታውን እስከመታገል መድረስ መቻል እንዳለበት ከአሁኑ በይፋ ያስብበት ዘንድ ጊዜው አሁን ነው። 

Wednesday, February 28, 2018

An African Portrayal of Adwa!

A few years ago, there was a movement by African media leaders to create an African narration of itself. The proposal aimed at reversing the racist or colonial perspective of Africa and telling African stories in African way.

To understand this, I usually think of ways of things are done at home, Ethiopia. Let me give you an example from home. Foreign media or any reference of an Ethiopian is so strange until that Ethiopian learns about it. In my little experience of travel and even in reference of foreign media, I found myself usually referred as someone whom I am not. The wikipedia page that has my profile, for example, reads my story as Hailu's, my father. Jokes aside, foreigners usually referred to me by my father's name mostly, and by my grandfather's name seldom. They call it Sur Name or Family Name while we have no such thing. I want to be called in my own way, the cultural way I have lived. But no one cares because the standard is set in the European way. 

We Ethiopians preserved the Ethiopian way of name-system We preserved it because we were not colonized. Things would have continued in multiple different/diverse ways in Africa and elsewhere if there were no colonization. 

In Adwa, Ethiopians defeated Italian colonizers but I don't really believe we lived through our independence. The governments of Ethiopia are manipulated by European powers since then. Migration, importing innovations, and our very perception of white people made us submit to white or European supermacy. The European way is taken as the best way, the norm.  However, some things of our own have survived  until today. (By the way, "our own" way in itself is not pure invention of our own. It may be adoptation of something or modification of it through years until we forget the origin of it.)

One of the survived traditions exists our name-system. Even it was debated in parliament during the emperor's time. Fortunately, the parliamentarians of the time rejected the proposal to adopt European system and resumed the local name system. I'm not saying the Ethiopian name system (calling a person with her/his given name and adding her/his father's given name, and grandfather's given name respectively after the given name of a person to write a full name) is a perfect one nor a system that lived forever in Ethiopia. (In fact, I can't deny that sometimes I see family name system as tribal.) Anyway, what I wanted to write about is ours has evolved with its own bureaucracy and it always feels OK to do things in one's way. When I want to be referred by my name, and not by what foreigners think my family name is, it is an appeal to decide who I am.

Black Panther is awed by many because it is almost all blacks' movie. However, in my opinion, had had an African country that hasn't been colonized and remained hidden from the colonizers' indirect influence existed, it would have a chance to evolve even in a very different way than it is imagined in this movie. The movie, of course is produced to western audience, in a way that impresses black westerners. As a person who lives in a country where there is very little black/white race division, I couldn't see Black Panther more than just another super hero movie. But, what if it was authored, directed and produced by people who have actual experiences of being never colonized? 

Addis Ababa is not a good place to think of because it is trying to look like everyone else except Africans. I refer to my own experience of rural life two decades ago in Northern Shoa to imagine what a developed African nation, without colonial powers influence, would look like. Every item I saw there was made of resources found in that environment. The 'tefir' bed, that is made of leather ropes and wood without using a single nail attaching the woods; the cooking pan made of clay; the drinking cup, 'shikina', made of calabash; the plate, 'erbo', made of grass leaves; the house itself and everything is different and friendly to the environment. Imagine this to evolve and get advanced without any outside influence. It can be a lot of things but the possibility for it to look like as it is portrayed in Black Panther is very unlikely. 

Anyway, what I'm trying to explain is that it may not be better but it is always different when genuinely Africans portray themselves. I will use one more example to explain what I'm saying. 

In Ethiopia's traditional paintings, people's are usually painted two-eyed if they have done good and one eyed if they did evil. The traditional painting of Adwa, for example, displays two groups of warriors: one group is two-eyed and these are the colonialism-defenders; the other group is one-eyed because they have done evil things by trying to conquer Ethiopia.

Tuesday, January 9, 2018

No Diplomacy, No Dependency!

I believe all changes must come from within Ethiopia. It is the people of Ethiopia who should have the chance to have the ultimate say to make decisions on its fate. However, realities on ground give foreign powers disproportionate opportunity to interfere in internal affairs; and often times they use it to consolidate powers of authoritarians. World conventions, pacts, partnership values and etc. are lip services to let the hopeless mass hope for a promise that will never be fulfilled, letting citizens settle down while diplomats continue empowering authoritarians to consolidate power through their support.

In post election 2005, foreign powers supported EPRDF financially to rise up after a wave of public protests. Similarly, today too, foreign powers and most of their diplomats in Ethiopia are in favor of the status quo with EPRDF (which is dominated by TPLF) because of mainly the following reasons:

1. Fear of the Unknown

Horn of Africa is capital of crises. Somalia is statess for decades, South Sudan is home of conflict, Eritrea and Sudan are disobedient to the west. Kenya has no strong force and Djibouti is a small partner. Ethiopia, with 100 of millions of population, is a place where no one wants to take the risk of destability. Besides, it hosts a lot of refugees from Eritrea, South Sudan and Somalia. No one wants her to add tens of million of immigrants to the rest of the world. (By the way, the aid to host refugees in Ethiopia goes to National Intelligence and Security Services (NISS) and it is the very institution that represses the whole nation with the money it has.)