እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ በዚህ ዓመትም ሰዎች ከፌስቡክ ውጪ እንዴት እንደሚኖሩ ለማወቅ ጉግል ውስጥ ፈልጌም፣ አስፈልጌም መልስ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ስለዚህ በፌስቡክ ውስጥ መኖሬን ቀጥያለሁ፡፡ በርግጥ ፌስቡክ ምንም አልጎደለበትም፤ እንኳን የሆነው የታሰበው ሳይቀር ይወራበታል፡፡ ለአብነትም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርን ሞት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፌስቡክ ምድር ላይ ካለው ‹እቤት-እመስሪያቤት› ምልልስ የተሻለ ፋይዳ ያለው ሥራ ለመስራት የተመቸ ዕድልም ይፈጥራል፡፡ የዳቦ ጉዳይ (bread winning) ሁላችንንም በየሙያችን ቢያሰማራንም፣ የምንናፍቀው እና የሚናፍቀን ሌላ ነገር የለም ማለት መቼም አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ የምንዋደደውን ያክል የምንወደውና የሚወደንን ዓይነት መንግስት ያገኘንበት ጊዜ እምብዛም ነው፡፡ ይህንን መናፈቅ እና መማከር ደንብ ሆኖ፣ በሌላም፣ ዓመቱን ሙሉ በጻፍናቸው ነገሮች ያስደሰትነው ሰው እንዳለ ሁሉ ያስቀየምነው የለም ማለት ዘበት ነውና፣ ያው የግል ጥቅም ይዞን አለመሆኑ ታውቆ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ይቅር መባባልን የመሰለ ነገር የለም፡፡ በዚህ ዓመት በፌስቡክ ገጼ ላይ ያሰፈርኳቸውን እና ከወዳጆቼ ጋር ቅኔ የተዛረፍኩባቸውን ግጥሞች በአንድ መድብል ‹‹ የፌስቡክ ትሩፋት ›› በሚል ጠርዠዋለሁ፡፡ ማንም ቢፈልግ እዚያው ባለበት ማንበብ፣ ወይም ዳውንሎድ ማድረግ ይችላል፡፡ አምና ሁለት ሺህ ሦሰትን በአርባ ሁለት በሚል በ2003 የጻፍኳቸውን ጦማሮች አንድላይ ቢጠረዙ መልካም ነው በሚል ማስቀመጤ ይታወሳል፡፡ አሁንም ዘንድሮ የሞነጫጨርኳቸውን እዚህ አስቀምጫለሁ፡፡ በስህተቴ ያረማችሁኝን እና የነቀፋችሁኝን፣ በብርታቴ ላይ አበርታች የሆነ አስተያየታችሁን ለሰጣችሁኝ፣ በዝምታ ስታነቡኝ ከርማችሁ መንገድ ላይ ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.