ሰሞኑን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የተሰኘ እና መቀመጫውን ሰሜን አሜሪካ ያደረገ ቡድን ባጋለጠው መረጃ መሰረት INSA (Infromation Network Security Agency) በመባል የሚታወቀው መንግስታዊ ድርጅት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የ‹‹ተጠርጣሪ›› ግለሰቦችን ንግግር በመጥለፍ ሲያዳምጥ እና ሲቀዳ ይውላል ይለናል፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ምን እንደተከሰተ ባይታወቅም ይኸው INSA ከዚህ በፊት ከነበረው ትጋት በበለጠ በአንድ ሳምንት ብቻ ከመቶ በላይ ድረአምባዎችን እና ጦማሮችን አግዷል፡፡ የጦማር እገዳው ዘመቻ ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ አንዳንድ ጦማሪዎች ሲዘጋባቸው፣ አዲስ ሲከፍቱ፤ ሲዘጋባቸው፣ አዲስ ሲከፍቱ ሰንብተዋል፡፡ በፖለቲካዊ ሽሙጦቹ መንግስትን የሚያንጰረጵረው አቤ ቶክቻው (ይህንን ጽሁፍ እስከጻፍኩበት ጊዜ ድረስ ብቻ) ሰባት ጦማሮችን በመክፈት ክብረወሰን ለመስበር በቅቷል፡፡
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.