ትላንት የጥላቻ ንግግርን የተመለከተ ጥናት ማሟያ ውይይት ላይ ተሳትፌ ነበር። በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በሰፊው የምመለስበት ቢሆንም፥ ቀብዱን ግን እነሆ፦ ርዕሱ በኢሕአዴግ እና በደጋፊዎቹ አተረጓጎም "የጥላቻ ንግግር" ተብሎ ሊመደብ ይችላል። አንድ የዴሞክራሲ ሕልመኛ ርዕሱ ላይ የተጠቀሰውን ዓ/ነገር ቢናገር ኢ-ዴሞክራሲያዊም ሆነ ጥላቻ ሰባኪ አያሰኘውም ባይ ነኝ እኔ ግን። እኔ ራሴ ርዕሱ ላይ የተጻፈውን ያለምንም ጥላቻ ከውስጥ ፍላጎቴ ነው ያፈለቅኩት። ከዴሞክራሲ ዐብይ ባሕርያት አንዱ ገዢ ፓርቲዎች ወርደው የሕዝብ ምርጫ በሆኑ ተቃዋሚዎች መተካት የሚችሉበት እና ገዢ የነበሩ ተቃዋሚ ሆነው የሚሮጡበት ስርዓት ማመቻቸት ነው። ስለዚህ ለኔ ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊነት መፍጨርጨሯ ሐቀኛ ነው ልል የምችለው ኢሕአዴግ ወርዶ ተቃዋሚ ሆኖ ሳየው ነው። የጥላቻ እና የፍቅር ንግግሮች የሉም ማለት አልችልም። ነገር ግን የጥላቻም ይሁን የፍቅር ንግግሮች ዋጋቸው ከአንድ ክበብ አያልፍም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ነክ የአገር ውስጥ እና የውጭ ሚዲያዎች በባሕሪያቸው መድባቸው ብባል በሦስት እመድባቸዋለሁ፦ 1ኛ) አፍቃሬ-ኢሕአዴግ፣ 2ኛ) ኢሕአዴግን-አያሳየኝ እና 3ኛ) I-don't-know-what-to-doዎች በማለት። የመጀመሪያዎቹ [አፍቃሬ-ኢሕአዴግ]ዎቹ ዋነኛ ሥራቸው በማንኛውም መንገድ ኢሕአዴግን ማንቆለጳጰስ እና ከተቃዋሚዎች ክፉ ዓይን መጠበቅ ናቸው። አዳም ሲፈጠር ጀምሮ "በስም መስጠት ነው (naming)" ነው ሥራውን የጀመረው እንዲሉ እኔም በዚህ ምድብ የምፈርጃቸውን ጥቂቶች ልዘርዝር፤ ኢቴቪ፣ ዛሚ ኤፍኤም፣ ኢትዮ-ቻናል፣ ትግራይ ኦንላይን እና ወዘተ ናቸው። ሁለተኛው ምድብ ውስጥ የሚገኙት [ኢሕአዴግን-አያሳየኝ]ዎች ደግሞ የሚደግፉ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.