Skip to main content

እኔ የምፈልገው ኢሕአዴግ ወርዶ ማየት ብቻ ነው!

ትላንት የጥላቻ ንግግርን የተመለከተ ጥናት ማሟያ ውይይት ላይ ተሳትፌ ነበር። በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በሰፊው የምመለስበት ቢሆንም፥ ቀብዱን ግን እነሆ፦

ርዕሱ በኢሕአዴግ እና በደጋፊዎቹ አተረጓጎም "የጥላቻ ንግግር" ተብሎ ሊመደብ ይችላል። አንድ የዴሞክራሲ ሕልመኛ ርዕሱ ላይ የተጠቀሰውን ዓ/ነገር ቢናገር ኢ-ዴሞክራሲያዊም ሆነ ጥላቻ ሰባኪ አያሰኘውም ባይ ነኝ እኔ ግን። እኔ ራሴ ርዕሱ ላይ የተጻፈውን ያለምንም ጥላቻ ከውስጥ ፍላጎቴ ነው ያፈለቅኩት።

ከዴሞክራሲ ዐብይ ባሕርያት አንዱ ገዢ ፓርቲዎች ወርደው የሕዝብ ምርጫ በሆኑ ተቃዋሚዎች መተካት የሚችሉበት እና ገዢ የነበሩ ተቃዋሚ ሆነው የሚሮጡበት ስርዓት ማመቻቸት ነው። ስለዚህ ለኔ ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊነት መፍጨርጨሯ ሐቀኛ ነው ልል የምችለው ኢሕአዴግ ወርዶ ተቃዋሚ ሆኖ ሳየው ነው።

የጥላቻ እና የፍቅር ንግግሮች የሉም ማለት አልችልም። ነገር ግን የጥላቻም ይሁን የፍቅር ንግግሮች ዋጋቸው ከአንድ ክበብ አያልፍም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ነክ የአገር ውስጥ እና የውጭ ሚዲያዎች በባሕሪያቸው መድባቸው ብባል በሦስት እመድባቸዋለሁ፦
1ኛ) አፍቃሬ-ኢሕአዴግ፣
2ኛ) ኢሕአዴግን-አያሳየኝ እና
3ኛ) I-don't-know-what-to-doዎች በማለት።

የመጀመሪያዎቹ [አፍቃሬ-ኢሕአዴግ]ዎቹ ዋነኛ ሥራቸው በማንኛውም መንገድ ኢሕአዴግን ማንቆለጳጰስ እና ከተቃዋሚዎች ክፉ ዓይን መጠበቅ ናቸው። አዳም ሲፈጠር ጀምሮ "በስም መስጠት ነው (naming)" ነው ሥራውን የጀመረው እንዲሉ እኔም በዚህ ምድብ የምፈርጃቸውን ጥቂቶች ልዘርዝር፤ ኢቴቪ፣ ዛሚ ኤፍኤም፣ ኢትዮ-ቻናል፣ ትግራይ ኦንላይን እና ወዘተ ናቸው።

ሁለተኛው ምድብ ውስጥ የሚገኙት [ኢሕአዴግን-አያሳየኝ]ዎች ደግሞ የሚደግፉት (የሚያፈቅሩት) የተለየ የተቃዋሚ ቡድን የላቸውም፣ የሚራሩለት እንጂ። ነገር ግን ያለምንም ጥርጥር ኢሕአዴግን አይወዱም። ስለዚህ ሥራቸው ኢሕአዴግን መተቸት ነው። እነዚህ ውስጥ ኢሳት፣ ፋክት፣ ኢትዮጵያን ሪቪው እና ወዘተ ይገኛሉ።

ሦስተኛው ምድብ [I-don't-know-what-to-do]ዎች ውስጥ ያሉት ደግሞ በመሐል ቤት ይዋልላሉ። ለዚህ ቡድን አሪፍ ምሳሌ የሚሆኑት ደግሞ አዲስ አድማስ ጋዜጣ እና ሸገር ኤፍ ኤም ናቸው። በተረፈ ጥቂቶች ብቻ ለመፈረጅ የማይመች የሚዲያ ሥራ እና ሊረዱት የሚከብድ የአቋምና አቀራረብ ልዩነት ያሳያሉ።

ለምን እነዚህን ፍረጃዎች እና ስየማዎች ማድረግ አስፈለገኝ? ምክንያቱም የጥላቻ ንግግሮች በማን፣ እንዴት እንደሚተረጎም ቀላል ማስረጃ ስለሚሆነኝ ነው። ምድብ አንድ ውስጥ ለሚገኙ ማንኛውንም ዓይነት ኢሕአዴግ ላይ የተሰነዘረ ትችት የጥላቻ ንግግር ነው።
ምድብ ሁለት ውስጥ ለሚገኙትም ከኢሕአዴግ አፍ የሚወጣ ሁሉ ክፉ ነገር ነው። ሦስተኛው ምድብ ከቻለ ሁሉንም ለማስደሰት ካልቻለ ሁሉንም ላለማስከፋት ይፈጨረጨራል። በመሐል ቤት እውነት ማደሪያ ታጣለች። ሁሉም ለዓላማው እጇን ይጠመዝዛታል።

በአገራችን የጥላቻ ንግግር የሚባሉት ሁሌም ከጥላቻ የመነጩ ላይሆኑ ይችላሉ። በባሕላችን የሰውን ስህተት ፊት ለፊቱ መንገርን እንደአለመከባበር የሚያስቆጥር ስህተት ነው። ስለዚህ የአንድን ሰው ጉልህ እንከን እንዲህ ነህ ብሎ መንገር በጣም አስደንጋጭ ነው የሚሆነው። እንዲያውም በጠብ ወቅት ብቻ የሚከሰት ነገር ነው። ስለዚህ በትልቁ (በፓርቲና በፖለቲካዊ አመለካከት ላይ) ሲሰነዘር የእርምት አስተያየት መሆን ቀርቶ የትችት ማዕረግ እንኳን አያገኝም። የጥላቻ ይመስላል (ይባላል)።

ነገር ግን፤ ድክመትን እየሸሸጉ ብርታትን እንደመንገር ያለ አደገኛ ንግግር (dangerous speech) አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ለግለሰብም ይሁን ለቡድን ግብዝነት ይዳርጋል። ድክመት ሲነገረው እልል ብሎ በፈገግታ ተጉመጥምጦ የሚውጥ ግለሰብም ይሁን ቡድን ገጥሞኝ አያውቅም፤ ከትችቱ አለመማር ግን እየሰሙ አይቻልም፤ ከስህተት ላለመማር መፍትሔው እንደኢሕአዴግ ተቺውን ማፈን ብቻ ነው። ትችት ካደመጡት ግን ምናልባት ለመዋጥ ጊዜ ይወስድ ይሆናል እንጂ ዘልቆ መቆጥቆጡ አይቀሬ ነው።

ይሄ ሁሉ ግን ስለጠሉ ብቻ የሚተቹ፣ ስለወደዱ ብቻ የማይሞገሰውን የሚያወድሱ የሉም ማለት አይደለም። ጥላቻና ፍቅርም ምክንያታዊ አይሆኑም ማለት ይከብዳል። ነገር ግን ክርር ያሉት የሥነ ልቦና ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

የጥላቻ ንግግርን መብት ከሐሳብን የመግለጽ መብት ለይቶ ለማስቀረት ሁነኛው መፍትሔ የማንፈልገውን ብቻ ሳይሆን የምንፈልገውንም ጭምር ማወቅ አለብን፤ አራማጅ ተራማጅነታችንም በመርሕ እንዲመራ ማድረግ መድኃኒቱ ነው።

Comments

Popular posts from this blog

The "Corridor Development" is a Façade of the Prosperity Party

Befekadu Hailu I have seen a news report claiming that 40% of central Addis Ababa will be demolished for the corridor development; I am not able to confirm the validity of the news but it sounds real to me given the size of massive operations in the demolition of old neighborhoods and construction of bike lanes, green areas, and glittering street lights. I like to see some beauty added to my city but cannot help mourning the slow death of it too. Addis Ababa was already in a huge crisis of housing and the demolition of houses is exacerbating it. Apparently, Prime Minister Abiy Ahmed is eager to showcase his vision of prosperity by demonstrating how fast his administration can do magic by beautifying the front sides of the streets with lights, new pavements, and painted fences ("to fake it until he makes it" in my friend's words). Therefore, he and his party do not care about the miserable human stories behind the scenes and they will harass you if you tell it (Azeb Woku...

መጽሐፍ የሚወጣው፣ የተዋነይ ዘ ጎንጅ 5 መሥመር ቅኔ

ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል። “የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።” (ተዋነይ ዘ ጎንጅ። ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ) ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን ...

የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ

በፍቃዱ ዘ . ኃይሉ “የአዲስ አበባ ብሔርተኝነት” ቢኖር ኖሮ መሪው ልጅ ሚካኤል ይሆን ነበር። አሁን አሁን እሱ ስለ አዲስ አበባ የዘፈናቸውን ዘፈኖች ቁጥር ራሱ በትክክል መቁጠር ይቸግረኛል። ለአዲስ አበባ ከተዘፈኑ ዘፈኖቹ ውጪም በየዘፈኑ ውስጥ የሚጨማምራቸው መልዕክቶች በራሳቸው መወድሰ አዲስ አበባ ናቸው። ለምሳሌ፣ በቅርቡ በለቀቀው ‘አዲስ አራዳ’ በተሰኘው አልበሙ ውስጥ ‘የድሬ ልጅ’ የሚል ዘፈን አለው። ዘፈኑ የተዘጋጀው ያው የአዲስ አበባ እህት ተደርጋ የምትቆጠረውን ድሬ ዳዋን ለማወደስ ነበር። ልጅ ሚካኤል ግን የአዲስ አበባ ፍቅሩ ያመልጠውና የሚከተለውን ያቀነቅናል፦ “መጣልሽ በሏት፣ ድሬ ድረስ፣  ከአዱ ገነት፣ ከሸገር፣ ከአዲስ ደረሰ፣... የሸገር ልጅ አራዳ ነው፣ ሰው አክባሪ፣ ሰው ወዳዱ፣ ቀላጅና ተረበኛ፣ ፍቅር ይዞ የሚተኛ፣ ‘አለው’ የለ፣ ‘የለው’ የለ፣ ከሁሉ ጋ፣ ግባ ጀባ...፤” ፤ ልጅ ሚካኤል በዚህ አልበሙ ብቻ አዲስ አበባን የሚያውድሰባቸው ሌሎችም ዘፈኖች አሉ፤ ‘ አዲስ አራዳ ’ የሚለው የአልበሙ መጠሪያ እና ‘ሸገር’ የሚሉት ዘፈኖቹ ዋነኞቹ ናቸው። ታዲያ እንዲህ በአዲስ አበባ ፍቅር የሚቃጠለው ልጅ ሚካኤል "ሊነግረን የሚፈልገው ምንድን ነው?" የሚለው ጥያቄ ደጋግሞ ይመጣብኛል። ይህ የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ ምንነትን ለመረዳት የሚጥር ፖለቲካዊ መጣጥፍ ነው። ‘አዲሱ አራዳ’ ማነው? በዚህ ዘፈኑ በብዙዎቻችን ዕድሜ የትዝታ ማኅደር ውስጥ የሚገኙ ነገር ግን በአዲስ አበባ ልማት ሥም የፈረሱ እና እየተረሱ ያሉ ሰፈሮችን ሥም ያነሳሳል። ዘፈኑ በግጥሙም በዜማውም፣ የሐዘን እንጉርጉሮ ያለበት ነው። ምሳሌ እንውሰድ፦ “ጨርሰሽ ስትወጪ ከቡፌ ዳ’ላጋ፣ ጠብቂኝ እንዳልል፣ ቆመሽ መሐሙድ’ጋ፣ አገር ...