Skip to main content

‹ጠላፊው› vs. ‹አጋቹ› - ኢትዮጵያ vs. ስዊዘርላንድ

ዘላለም ክብረት

ዛሬ በጠዋቱ ዜናው በሙሉ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ሲጓዝ የነበረን 202 ሰዎችን ያሳፈረ የኢትዮጵያ አውሮፕላን 'መጠለፍ' ጉዳይ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ‹ጠላፊው ካርቱም ላይ የተሳፈረ ሰው ይመስላል› ቢሉም በመጨረሻ አውሮፕላኑ ካርቱም ላይ ከነጭራሹ እንዳላረፈና ጠላፊውም ረዳት ፓይለቱ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ረዳት ፓይለቱ ለምን ይሄን ተግባር እንደፈፀመ ሲጠየቅም ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ስጋት ላይ እንደጣለው በመግለፅ፤ ሲዊዘርላንድ ጥገኝነት እንድትሰጠው ጠይቋል፡፡

 ይህ ከሆነ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ መስሪያ ቤት እንደገለፀው ግን ጉዳዩ ጠለፋ (Hijacking) ሳይሁን እገታ ( Hostage Taking) ነው ብሏል፡፡ በሌላ በኩል ረዳት ፓይለቱ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ እንዳይሰጥ ስዊዝን ተማፅኗል፡፡ ሁለት የህግ ጥያቄዎች አሉ፡

1. ጠለፋ ወይስ እገታ?

2. በረዳት ፓይለቱ ላይ የዳኝነት ስልጣን (Legal Jurisdiction) ያለው አካል ማነው? ኢትዮጵያ ወይስ ስዊዘርላንድ?

እነዚህን ጉዳዮች የሚፈቱልን ሁለት አለማቀፍ ሕጎች አሉ (ኢትዮጵያም ስዊዘርላንድም የሁለትም የሕጎቹ ፈራሚ ሀገራት ናቸው)፡፡

1. Convention for the Suppression of Unlawful Seizure of Aircraft – Hijacking Convention on Hijacking – 1970 &,

2. International Convention Against the Taking of Hostages – Convention on Hostage taking - 1983.

በነዚህ ሁለት ሕጎች መሰረትም የረዳት ፓይለቱን ሁኔታ (Situation ) እንይ፡፡
1ኛ. ጠለፋ ወይስ እገታ?

ከላይ በመጀመሪያ የጠቀስነው የHijacking Convention 'ጠለፋ'ን በአንቀፅ አንድ ላይ እንዲህ ይፈታዋል:

Any person who on board an aircraft in flight:

unlawfully, by force or threat thereof, or by any other form of intimidation, seizes, or exercises control of, that aircraft, or attempts to perform any such act, or is an accomplice of a person who performs or attempts to perform any such act commits an offence [of Hijacking].

በሌላ በኩል ከላይ በሁለተኝነት የጠቀስነው የHostage taking convention 'እገታ'ን በአንቀፅ አንድ ላይ እንዲህ ይተረጉመዋል፡

Any person who seizes or detains and threatens to kill, to injure or to continue to detain another person in order to compel a third party, namely, a State, an international intergovernmental organization, a natural or juridical person, or a group of persons, to do or abstain from doing any act as an explicit or implicit condition for the release of the hostage commits the offence of hostage-taking.

የኢትዮጵያዊው ረዳት ፓይለት ተግባርም ጥገኝነት ለማግኝት ያደረገው ማስገደጃ መሳሪያ በመሆኑ የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ መስሪያ ቤት እንዳለው ተግባሩ ለእገታ የቀረበ ሲሆን፤ ተጠያቂነቱም ከእገታ ጋር በተያያዘ ይሆናል ማለት ነው፡፡

2ኛ. ኢትዮጵያ ወይስ ስዊዘርላንድ?

ጉዳዩ 'እገታ' ነው ካልን በጉዳዩ ላይ ተገቢ የሆነው ሕግ አለማቀፉ የፀረ እገታ ሰምምነት (Hostage taking convention) ነው ማለት ነው፡፡ በዚህም መሰረት በረዳት ፓይለቱ ላይ የዳኝነት ስልጣን ያለው የየትኛው ሀገር መንግስት ነው? የሚለው ቀጣዩ ጥያቄ ነው፡፡

ሕጉን ጠቅሰን ብናልፍ ይሻላል፡፡ ዓለማቀፉ የHostage taking convention በአንቀፅ አራት ላይ እንዲህ ይደነግጋል፡

State shall take such measures as may be necessary to establish its jurisdiction over the offence and any other act of violence against passengers or crew committed by the alleged offender in connection with the offence, in the following cases:

A. when the offence is committed on board an aircraft registered in that State (በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ስልጣን ይኖራታል);

B. when the aircraft on board which the offence is committed lands in its territory with the alleged offender still on board (በዚህ መሰረት ደግሞ ስዊዘርላንድ ስልጣን ይኖራታል ማለት ነው).

ስለዚህም በጉዳዩ ላይ የሁለት ሀገሮች የዳኝነት ስልጣን ያለ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የአውሮፕላኑ ባለቤት በመሆኗ፣ ስዊዘርላንድ ደግሞ አውሮፕላኑ በግዛቷ በማረፉ ስልጣን አላት ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ማን ቀዳሚ ስልጣን ይኖረዋል? የሚለው የሚወሰነው ተጠርጣሪውን (በአሁኑ ጉዳይ ረዳት ፓይለቱ) በቁጥጥር ስር ቀድሞ በማዋል የሚወሰን ሲሆን በአሁኑ ጉዳይ ላይ የዳኝነት ስልጣኑ የስዊዘርላንድ ነው ማለት ነው፡፡

መውጫ፡

ኢትዮጵያ ተጠርጣሪው ተላልፎ እንዲሰጣት (Extradition) በፀረ እገታ ሰምምነቱ አንቀፅ 7ና 8 መሰረት መብት ቢኖራትም ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ የአሳልፎ የመስጠት ስምምነት (Extradition agreement) ስለሌላቸው (እኔ እስከማውቀው ድረስ) ተላልፎ የመሰጠት ጉዳዩ ብዙም አድል የለውም፡፡ የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ መስሪያ ቤትም ከአሁኑ ክስ ለመመስረት ጉዳዩን እያጣራ እንደሆነ መልለጫ ሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም:

ረዳት ፓይለቱ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኝ በስዊዘርላንድ የወንጀል ሕግ SR 311.0 አንቀፅ 185 መሰረት ከ3 ዓመት እስከ 20 ዓመት (እንደ ነገሩ ሁኔታ) የሚደርስ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ በሌላ በኩል 'ድንገት' ተላልፎ ለኢትዮጵያ ቢሰጥ ደግሞ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 507/1 መሰረት ከ15 አስከ 20 ዓመታት እስር ይጠብቀዋል ማለት ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

The "Corridor Development" is a Façade of the Prosperity Party

Befekadu Hailu I have seen a news report claiming that 40% of central Addis Ababa will be demolished for the corridor development; I am not able to confirm the validity of the news but it sounds real to me given the size of massive operations in the demolition of old neighborhoods and construction of bike lanes, green areas, and glittering street lights. I like to see some beauty added to my city but cannot help mourning the slow death of it too. Addis Ababa was already in a huge crisis of housing and the demolition of houses is exacerbating it. Apparently, Prime Minister Abiy Ahmed is eager to showcase his vision of prosperity by demonstrating how fast his administration can do magic by beautifying the front sides of the streets with lights, new pavements, and painted fences ("to fake it until he makes it" in my friend's words). Therefore, he and his party do not care about the miserable human stories behind the scenes and they will harass you if you tell it (Azeb Woku...

መጽሐፍ የሚወጣው፣ የተዋነይ ዘ ጎንጅ 5 መሥመር ቅኔ

ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል። “የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።” (ተዋነይ ዘ ጎንጅ። ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ) ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን ...

የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ

በፍቃዱ ዘ . ኃይሉ “የአዲስ አበባ ብሔርተኝነት” ቢኖር ኖሮ መሪው ልጅ ሚካኤል ይሆን ነበር። አሁን አሁን እሱ ስለ አዲስ አበባ የዘፈናቸውን ዘፈኖች ቁጥር ራሱ በትክክል መቁጠር ይቸግረኛል። ለአዲስ አበባ ከተዘፈኑ ዘፈኖቹ ውጪም በየዘፈኑ ውስጥ የሚጨማምራቸው መልዕክቶች በራሳቸው መወድሰ አዲስ አበባ ናቸው። ለምሳሌ፣ በቅርቡ በለቀቀው ‘አዲስ አራዳ’ በተሰኘው አልበሙ ውስጥ ‘የድሬ ልጅ’ የሚል ዘፈን አለው። ዘፈኑ የተዘጋጀው ያው የአዲስ አበባ እህት ተደርጋ የምትቆጠረውን ድሬ ዳዋን ለማወደስ ነበር። ልጅ ሚካኤል ግን የአዲስ አበባ ፍቅሩ ያመልጠውና የሚከተለውን ያቀነቅናል፦ “መጣልሽ በሏት፣ ድሬ ድረስ፣  ከአዱ ገነት፣ ከሸገር፣ ከአዲስ ደረሰ፣... የሸገር ልጅ አራዳ ነው፣ ሰው አክባሪ፣ ሰው ወዳዱ፣ ቀላጅና ተረበኛ፣ ፍቅር ይዞ የሚተኛ፣ ‘አለው’ የለ፣ ‘የለው’ የለ፣ ከሁሉ ጋ፣ ግባ ጀባ...፤” ፤ ልጅ ሚካኤል በዚህ አልበሙ ብቻ አዲስ አበባን የሚያውድሰባቸው ሌሎችም ዘፈኖች አሉ፤ ‘ አዲስ አራዳ ’ የሚለው የአልበሙ መጠሪያ እና ‘ሸገር’ የሚሉት ዘፈኖቹ ዋነኞቹ ናቸው። ታዲያ እንዲህ በአዲስ አበባ ፍቅር የሚቃጠለው ልጅ ሚካኤል "ሊነግረን የሚፈልገው ምንድን ነው?" የሚለው ጥያቄ ደጋግሞ ይመጣብኛል። ይህ የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ ምንነትን ለመረዳት የሚጥር ፖለቲካዊ መጣጥፍ ነው። ‘አዲሱ አራዳ’ ማነው? በዚህ ዘፈኑ በብዙዎቻችን ዕድሜ የትዝታ ማኅደር ውስጥ የሚገኙ ነገር ግን በአዲስ አበባ ልማት ሥም የፈረሱ እና እየተረሱ ያሉ ሰፈሮችን ሥም ያነሳሳል። ዘፈኑ በግጥሙም በዜማውም፣ የሐዘን እንጉርጉሮ ያለበት ነው። ምሳሌ እንውሰድ፦ “ጨርሰሽ ስትወጪ ከቡፌ ዳ’ላጋ፣ ጠብቂኝ እንዳልል፣ ቆመሽ መሐሙድ’ጋ፣ አገር ...