መጀመሪያ እንዲህ ነበር፤ “የኛ ሙሽራ ኩሪ ኩሪ፣ አገባሽ አስተማሪ፡፡” ከዚያ በኋላ፤ (በጓደኛ ዬ እርዳታ ርዕሱን ያስታወስኩት የዶ/ር በፍቃዱ ‹ሰሚ ያጡ ድምፆች› ላይ እንደሰፈረው) መምህራን በየክፍለሃገራቱ ተሰማርተው የነበረ ቢሆንም ደሞዛቸው 202 ብር (ቱኦቱ) ብቻ ነበር፡፡ መምህራኑ ይቺን ‹ቱኦቱ› ምን ከምን እንደምን እንደሚያደርጓት ይቸግራቸው ነበር፡፡ ስለዚህ እንደመፍትሔ ሌላ መምህርት በማግባት ወጪን በመጋራት ገቢን 404 ብር (ፎር-ኦ-ፎር) ለማደረስ ይጥሩ ነበር፡፡ (ትዳር ትርጉሙ ገቢን ማሳደግ ወይም ወጪን መጋራት እንጂ ፍቅር አልነበረም ማለት ነው፡፡) ይሄ ነገር እየተለመደ ሲመጣ የመምህር ሚስት መምህርት (ወይም የመምህርት ሚስት መምህር) ‹ፎሮፎር› የሚል ቅፅል ተሰጣቸው፡፡ “ፎሮፎሬን ተዋወቃት ” ማለት ልክ “ባለቤቴን ተዋወቃት” እንደማለት ሆነ፡፡ ትንሽ ከረምረም ሲል ደግሞ፤
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.