Skip to main content

Posts

Showing posts from February, 2012

የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሌሎችም ከኢትዮጵያ ፓርላማ መማር የሚገባቸው!

(የዓለማችንን ሕዳሴ ለማፋጠን የቀረበ ምክረ ሐሳብ) እስከዛሬ የጻፍኳቸው ሁሉ የግል አቋሜን የሚያንጸባርቁ አልነበሩም፡፡ ነገርዬዎቹ “ኪራይ ሰብሳቢ” የተባለ ሰይጣን ለክፎኝ የተናገርኳቸው ነበሩ፡፡ ሰይጣኑ የለከፋቸው ሰዎች በኢትዮጵያ የተገነቡት ፎቆችና መንገዶች፣ የሰፈነው መልካም አስተዳር፣ በ11.4% የሚመነደገው ኢኮኖሚ አይታያቸውም፡፡ ለነሱ የሚታያቸው ድንጋይ ሲወረውሩ÷ ፓሊሶች ራሳቸውን ለመከላከል በሚተኩሱት ጥይት የሚሞቱ አደገኛ ቦዘኔዎች፣ ከስንት አንዴ የሚገለበጡ የምርጫ ኮሮጆዎች፣ የመንግስትን ሕልውና በስክርቢቶና ወረቀት የሚያናጉ ጋዜጠኞች መታሰር፣ የኢኮኖሚውን ዕድገት ተከትሎ የተከሰተው የዋጋ ግሽበት ብቻ ነው፡፡ ቻይናዊው ዕውቅ ኮሚኒስትና የፖለቲካ ጠቢብ ኪል ሃንግ÷ ጥርነፋ ወከመ ለስልጣን በሚል ርዕስ በጻፉት መጽሃፋቸው ላይ በኪራይ ሰብሳቢ ሰይጣን የተለከፉ ዜጎች ነፃ ሊወጡ የሚችሉባቸውን መንገዶች ሦስቱ ‘መ’ዎች በማለት ሰይመዋቸዋል፤ እነሱም መጠመቅ ፣ መ ታረም ወይም መሰደድ ናቸው፡፡ መጠመቅ፡- በሚባለው መንገድ ኪራይ ሰብሳቢዎች በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ዶክትሪን ከተሰበኩና ካመኑ በኋላ “የልማታዊ ዜግነት” ጠበል ተረጭተው (ተጠምቀው) ካለፈው ሃጢያታቸው ተሰርየው÷ ምቹ ወንበርና ስልጣን፣ በቂ ደሞዝና ጥቅማጥቅም አግኝተው በሰላም የሚኖሩበት ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡ ያለፈው ሃጢያተቸውን ያነሳም “ው ሾ ይሁን ” ተብሎ ይረገማል፡፡ (በዚህ መንገድ እነ ሽመልስ ከማል፣ እነ ሬድዋን እና እኔ የዚህ ጠመቃ ተጠቃሚዎች ነን፡፡)

ኑሮ በአገርኛ÷ ጾም ይበዛበታል!

ባሕር ማዶ ካሉ ሰዎችጋ ስናወራ አንዳንድ የማይገቡን ወሬዎችን እየሰማን ጭንቅላታችንን እየናጥን “ወቸ ጉድ!” ማለታችን አይቀሬ ነው፡፡ ለኛ ባዳ ከሆነው ከቀላሉ “GPS” ጀምሮ፣ credit card ቢሉ፣ ምን ቢሉ ሁሉም ለኛ እንቆቅልሾች ናቸው፡፡ ወጉ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ እንዲሉ “GPS” ቀርቶብኝ እበላው ባገኘሁ የሚለው እስኪታወሰን ድረስ እንደመማለን፡፡ እዚህ GPS የለም፣ credit card የለም፣ ባቡር (ወይም subway station ብሎ ቋንቋ) የለም፣ smart phone የለም፣ wi-fi የለም (አለ እንዴ?) ለነገሩ የዚህ ጫወታ ጉዳዮች እነዚህ ሁሉ ስላልሆኑ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ በርግጥ ግን ወደጫወታው አጀንዳ ለመድረስ አሁንም ዳር፣ ዳሩን መነካካት የግድ ነው፡፡ ‹አሜሪካኖች ለምን ወፋፍራም ሆኑ? ኢትዮጵያውያኖች ለምን ቀጫጭን ሆኑ?› ብለን ብንጀምርስ!

አማርኛ በመዝገብ ላይ

ዘፍጥረት 29÷11-16 (በግዕዝ) በሚያውቁት ቋንቋ መናገር አንጀትን ያርሳል፡፡ ለዚህም ነው አንዳንዶቻችን በውጭ ቋንቋ፣ ከውጭ አገር ሰዎች አውርተን ስናበቃ ነፃ የመውጣት ስሜት የሚሰማን፡፡ ‘ሶሲዮሎጂስቶች’ ቋንቋን ከባሕል ገንቢ ወይም ገላጭ ቅንጣቶች መካከል ዋነኛ ሲሉ ያኖሩታል፡፡ የአንድ ማሕበረሰብ ባሕል እና ዕውቀት በቋንቋው ውስጥ ይገለጣል፡፡ ምንም እንኳን ቋንቋዎች ሁሉ ሙሉ ናቸው ብንልም÷ ባሕሉ የማያውቃቸው ብዙ ቃላቶች ግን እንደሚኖሩት መካድ አይቻልም፡፡ ለምሳሌ በአማርኛችን snow (‘ስኖው’) ለሚለው ቃል አንድም አቻ ትርጉም የለውም፡፡ በሰሜን አሜሪካ እና ሩሲያ መካከል፣ አላስካ አካባቢ የሚኖሩ የዚያው አካባቢ ጥንታዊ ሕዝቦች (እስኪሞዎች ይበላሉ) ስኖውን የሚወክሉ በርካታ ቃላቶች አሉዋቸው፡፡ ለምሳሌ አፑት ~ መሬት ላይ የተከመረ ስኖው ፣ ጋና ~ እየዘነበ ያለ ስኖው ፣ ፒቅሲርፖቅ ~ አየርላይ እየተንሳፈፈ ያለ ስኖው ፣ ቂሙቅሱቅ ~ የ ስኖው ሰፈፍ፡፡ በሃገራችን አሁን ዘመን እየቀየረን መጣ÷ እንጂ ሴትን ለማማለል ገዳይነት ነበር የሚያስፈልገው፡፡ አንበሳ መግደል፣ ጠላትን በመግደል… ለዚህም ነው Romance ለሚለው ቃል ትርጉም (በአማርኛ) የማይገኝለት፡፡ ብቸኛው romanticነት ጀግንነት ነበርና፡፡ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ወራጅ ወንዞች እንጂ ውቅያኖሶች አይጎራበቱትም÷ ለዚህ ነው በአማርኛ waterbank፣ shore፣ beach ለመሳሰሉ ቃላት ትርጉም ማግኘት የሚቸግረን፡፡ ይህ ዓይነቱ ችግር የአማርኛ ቃላቶችን ወደእንግሊዝኛ ልንመልስ ስንሞክርም ይገጥመናል፤ ችግሩ እንግሊዝኛው ላይ እርግጠኛ መሆን ስለሚቸግረን ይሄ፣ ይሄ ማለት ያስፈራናል፤ እላይ የተዳፈርነው የራስ መቼም የራስ ነው በሚል ብሒል ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ‹ይሉኝታ› ለሚለው የአማርኛ ...

የሐበሻ አምልኮ በኢትዮጵያ

(መግባቢያ፤ በዚህ ጽሁፍ ‘ሐበሻ’ ማለት ኢትዮጵያዊ፣ ‘አምልኮ’ ማለትም የተጋነነ አድንቆት የሚል ትርጉም ብቻ አላቸው፡፡) ‹ የፈረረንጅ አምልኮበኢትዮጵያ › በሚል በጻፍኩት ጽሁፍ ተበሳጭተው÷ ጠንከር ያለ ነቀፌታቸውን ያደረሱኝ በርካቶች ናቸው፡፡ (በተለይም ethiopianreview.com ላይ!) የዚያን ቀጣይ ጽሁፍ በዚህ ርዕስ ለመጻፍ የተገደድኩት ያለፈው ጽሁፍ ስህተት መሆኑን አምኜ በተቃራኒው ለማረም ቢሆን ‹‹መልካም ነበር፡፡›› ግን አይደለም፤ ያም ሆነ ይህ ጽሁፍ ማሕበረሰባችንን መነቀፍ ባለበት ጉዳይ ለመንቀፍ የማይሳሱ ጽሁፎች ናቸው፡፡ በመጀመሪያ የቀደመው ጽሁፍ ለምን ነቃፊ በዛበት የሚል ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ መስሎ ይሰማኛል፡፡ የሁሉንም አስተያየት ሰጪዎች መልዕክት ያለምንም ማንገራገር በአንድ ጨፍልቆ መረዳት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለባዕድ (ማለትም ለፈረንጅ) አምልኮ ወይም አድንቆ እጃቸውን የሰጡት ከመቼ ጀምሮ ነው በሚለው ጥያቄ ውስጥ እኔ መልስ ይሆናል ያልኩት ክርስትና ወደኢትዮጵያ መግባት ከጀመረ ወዲህ ነው የሚለውን ነው፡፡ ብዙዎች ክርስትና መነካቷን አይወዱምና የቁጣ ናዳ አወረዱብኝ ማለት ይቀላል፡፡ (ለጨዋታ ያህል ይሄ ጽሁፍ ‹‹ናዳን ለማቆም የተሮጠ ግለሰባዊ ሩጫ›› ነው ልንለው አንችላለን፡፡) እንዲያውም ክርስትና ለኢትዮጵያውያን የተሰፋ (ከባዕድ ያልወረስነው) እንደሆነ ሊያስረዱኝ የሞከሩ ሰዎችም አልጠፉም፡፡ ይሄ ሐሳብ ነው ወደዛሬው ጽሁፌ የሚያንደረድረኝ - የሐበሻ አምልኮ ብዬዋለሁ፡፡