ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በአንድ ወቅት በፈፀሙት ድርጊት ተፀፅተው ይቅርታ ይጠይቁ እንደሁ በገነት ‹ማስታወሻ› ላይ ሲጠየቁ ‹‹ማንን ነው ይቅርታ የምጠይቀው? ወያኔን? ወያኔ እኔን ይቅርታ ጠይቆኛል?...ይህ የታገልንለትን ጉዳይ አለማወቅ ነው›› በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል፡፡ መንግስቱ በአስተዳደራቸው ማክተሚያ ሰሞንም፣ በመንግስት መገናኛ ብዙሐን እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ‹‹ለአገሬና ለወገኔ ይበጃል ብዬ ባደረግኩትና በተሳተፍኩባቸው ተግባሮች ሁሉ በግሌ ሕሊናዬን የሚወቅሰኝ ነገር የለም›› ብለዋል፡፡ ‹‹መ›› ንግስቱ እና ‹‹መ›› ለስ መለስ በመንግስቱ ቆብ ውስጥ ገብተው ይሆን? በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ዲሞክራት መስለውን ነበር:: እኛን ብቻ ሳይሆን ምዕራባውያንንም በዚህ ሸውደዋቸዋል:: ምዕራብውያን ታዛዥነታቸውን ስለሚወዱላቸው ብቻ ተቀብለዋቸዋል:: የመለስ ታዛዥነት ለውጭ ኃይሎች ብቻ እንጂ ለአገራቸው ሕዝብ አይደለም:: መለስ በውጭ ዲፕሎማሲ ጎበዝ የሚመስሉዋችሁ ከሆነ - አይደሉም:: ሊደራደሩበት የሄዱትን ጉዳይ አሳልፈው በመስጠት መስማማትን ይመርጣሉ:: ውጪያዊ ተቃውሞ የማይደመጥባቸውም ለዚያ ነው:: በዴሞክራሲ ጉዳይ "ሙጋቤ የሚለው አፍሪካውያን የምዕራባውያን ዓይነት ዴሞክራሲ አያስፈልጋቸውም::" ብሎ ነው ብለው መለስ ከጋዜጠኛ ጋር ከተሟገቱ በኋላ የዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ተስፋው ተመናምኗል:: ሙጋቤ መንግስቱን አስጠልለዋል - አሁን ደግሞ መለስም የርሳቸውን የዴሞክራሲ ቲዎሪ እየዘመሩ ነው:: መንግስቱና መለስ እያደር የሚያመሳስላቸው ነገር ተበራክቷል፡፡ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹የነጋሶ መንገድ›› በተሰኘው ግለታሪካቸው እንደነገሩን የሕወሓት ተገን...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.