የብሔር ፖለቲካ በጣም ስስ (sensitive) ነው፡፡ በቀላሉ ተቆስቁሶ ብዙ ሊጓዝ ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ በኢሕአዴግ ዘመን፣ በብሔር ፌዴራሊዝም ከተከፋፈለች ወዲህ እንኳን የብሔር ፍላጎቶችና ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ አላገኙም፡፡ የኦሮሞ ብሔረሰብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ከ34 በመቶ በላይ ድርሻ አለው፡፡ (2007 National Census) ሆኖም የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት የሚገባውን ትኩረት የመነፈጉ ጉዳይ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ሲያነታርክ ቆይቷል፡፡ የብሔር (በተለይም የኦሮሞ ተወላጆች) ፖለቲካ ጉዳይ የታገሉለትን ያሕል ብዙ መሻሽል ባያስመዘግብም፣ በርካታ አማራጮችን ለፖለቲካው የሚመግቡ ኢትዮጵያውያንን አፍርቷል፤ እነ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ እነ ቡልቻ ደመቅሳ እና እነ ዶ/ር መረራ ጉዲና የዚህ ትሩፋቶች ናቸው፡፡ ለነገሩ የዚህ ወጌ ቁምነገር የብሔር ፖለቲካ በጥቅሉ አይደለም፤ ነገር ግን ከብሔር ፖለቲካ ዘውግ ውስጥ አንዱን መዝዤ መሟገት ቃጥቶኛል፡፡ ጉዳዩ የተቀበረ ቢመስልም ለኔ ግን ገና አልሞተም፤ ልክ በኤርትራ መገንጠል ጉዳይ ላይ መቁረጥ እንዳልቻልኩት ሁሉ - በዚህም ገና አልቆረጥኩም፡፡ በነገራችን ላይ ኢሕአዴግ ‹‹በመቃብሩ ላይ›› ካልሆነ በቀር የማይቀይራቸው በርካታ ጉዳዮች መካከል ይመደባል የዛሬ ጉዳዬ፡፡ ለዚያ ነው ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊ ምኞቶቼ እውን እንዲሆኑ ቶሎ የኢሕአዴግ መቃብር እንዲማስ ሌት ተቀን የምመኘው፡፡ አላግባብ ልብ ማንጠልጠሌን ልተወውና
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.