‹‹ኢትዮጵያ አገሬ›› ከሚለው ሐረግ በቀር በዚህ ዘመን አንገት የሚያስቀና ነገር ማግኘት እየከበደ ነው፡፡ እሴቶቻችን እየተሸረሸሩ፣ ፍቅራችን እየጠወለገ፣ ተስፋችን እየመነመነ.. መጥቷል፡፡ መንስኤው እንደውጤቱ እልፍ ነው፡፡ እኔም እንደወትሮዬ አምስት አጀንዳዎችን አንስቼ አንድነታቸውን የማስደመድምበት ምክረ መጣጥፍ ይዤ ቀርቤያለሁ - እነሆ! 1ኛ ‹‹ገበታ ንጉሥ ነው›› ገበታ እንደንጉሥ የሚቆጠርባት ኢትዮጵያ ገበታን ለማግነን ምክንያት አላት፡፡ የዓለም ስልጣኔ እምብርት የሆነችው ግብጽ ጥንታዊና ዘመናዊ ከተሞቿ የተቆረቆሩት በአባይ ወንዝ ዳርቻ ነው፡፡ ግብጽ ምድሯ ውሃ ባያፈልቅም ከደጇ በሚያልፈው ውሃ ሕዝቦቿን ከረሃብ ለመታደግ ችላለች፡፡ ‹‹ከሞኝ ደጃፍ ምሳር ይቆረጣል›› ነውና ተረቱ ኢትዮጵያ ግን የረሃብ ምሳሌ ነች፡፡ ከሰማይ ዝናብ ዘነበ/አልዘነበ በሚል የምግብ ዋስትናዋን በሚትዮሮሎጂ ዕድል ላይ የጣለችው ኢትዮጵያ የረሃብን ነገር ታውቀዋለች እና ‹‹ገበታ ንጉሥ ነው›› እያለች ብትተርት አይፈረድባትም - ረሃብ አንደኛ ጠላቷ ነውና፡፡ 2ኛ ‹‹ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም›› ኢትዮጵያውያን አማኞች ናቸው፡፡ ክርስትና ከመፈጠሩ በፊት አክሱም ሃውልትን ያስቆማቸው እምነታቸው ነው፡፡ ነገሮች ሁሉ በፈጣሪ ፈቃድ እንጂ በሰው ጉልበት ይሆናል ብለው አያምኑም፡፡ ይህንን በርካታ ምሳሌና የኑሮ ዘይቤያቸው ይመሰክራል፡፡ እርግጥ በዘመናዊዋ እና በቀድሞዋ ኢትዮጵያ መካከል ልዩነት ይኖራል ብሎ መጠርጠር መልካም ነው፡፡ እንደምሳሌም ጥንታዊዎቹ የአክሱም ሐውልትን ያቆሙት በትግል እንጂ በዕድል አይደለም፤ ሌላ ምሳሌ፣ ቀደምት የላሊበላ ታሪክ ጸሃፊዎች ላሊበላ የታነፀው እነዚህ ታሪክ ጸሃፊዎች የኢትዮጵያውያንን የእጅ ሥራ ‹‹ታድለው›› እንጂ ‹‹ታግለው›› ያ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.