Skip to main content

Posts

Showing posts from 2019

Abandonment of the Democratic Cause!

[A note from the brink of hopelessness] Ethiopia is in the verge of conflict due to power struggle between regional and federal government incumbents. The regional governments and their apparatus have fallen in the hands of ethnocentric forces who are threats to minority groups in their respective regions. The only sober voice is coming from Somali regional leaders who have maintained their regional autonomy as well as trying to get deserved representation in the federal government. The rest, specifically the powerful three - Oromia, Amhara and Tigray regional states' leaders are making life difficult for the silent majority. People have been mobilized based on ethnocentric narratives and co-existence with differences is almost impossible. Homogenization of regional states have become a new fashion against diversity.  Currently, Oromos are not in power; they are not privileged. But, Oromo-nationalism took power in the federal gov of Ethiopia. The most powerful men in Eth...

የእምነት ነጻነት ወይስ አስተዳደራዊ ጥያቄ?

በፍቃዱ ኃይሉ ሰሞኑን "የኦሮሚያ ቤተ ክሕነት አደራጅ ኮሚቴ" ያነሳው ጥያቄ የውዝግብ መንስዔ ሆኗል። ጉዳዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ስለሆነም፣ ምናልባት ደግሞ ለከፍተኛ ግጭት መንስዔ ሊሆን ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ይህንን መጣጥፍ የምጽፈውም፣ ከዚህ በፊት ስለማውቃቸው መሰል ውዝግቦች እና ድርድሮች የማውቀውን (የማስታውሰውን ያክል) ለማካፈል ነው። በስተመጨረሻ በወቅታዊው ውዝግብ ውስጥ የዴሞክራሲ እና የመብት ተሟጋቾች ጉዳዩን እንዴት መመልከት አለባቸው የሚለው ላይ የራሴን ነጥብ አስቀምጣለሁ። ይህንን የምጽፍበት ምክንያት የጥያቄውን ምንነት፣ የአቀራረቡን ሁኔታ፣ የቤተ ክርስቲያኗን አቋም እና የምዕመኑን ፍላጎት ከግምት ውስጥ ማስገባት ለመብት ተቆርቋሪዎች ወሳኝ ጉዳይ ስለሆነ ነው። በዚህ ጽሑፍ መሠረታዊ የሒደቱ መገምገሚያ መሥፈርቶቻችን 1ኛ፣ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ መግባት የለበትም፤ 2ኛ፣ ሃይማኖት በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለበትም፤ 3ኛ፣ በውዝግቡ ግጭት እንዳይነሳ እና ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መንግሥት የመከላከል ኀላፊነት እና ተወዛጋቢ አካላትም ይህንን የማስወገድ ግዴታ ያለባቸው መሆኑ ነው።  የራስ ገዝ አስተዳደር ጥያቄ ጉዳይ ያደግኩበት ሰፈር “ራስ ካሣ ሰፈር” ይባላል። የራስ ካሣ መኖሪያ ጊቢ ፊት ለፊት አንቀፀ ምኅረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አለ። ቤተ ክርስቲያኑ “ጭቁኑ ሚካኤል” በሚል ሥም ነው የሚታወቀው። ይህንን ሥያሜ ያገኘው ከቤተ ክሕነት ጋር በነበረው ውዝግብ ነው። በወቅቱ እዚያው እኛ ሰፈር የሚገኘው የገነተ እየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሥር ነበር ሚካኤል ቤተ ክርስትያንም የሚተዳደረው። እናም ባንድ ወቅት የሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች (ቀሳውስቱ እና ዲያቆናቱ) በገነተ ...

አዲሳባን እንደ የውክልና ጦር ሜዳ…

☞ የአዲስ አበባን የውሃ ፍላጎት ይቀርፋል የተባለ ፕሮጀክት በተዋወቀ ማግስት የኦሮሚያ መንግሥት አልተማከረም ነበር ተብሎ ተሰረዘ (ምክንያቱም ጃዋር ተቃውሞል) ☞ የኮንዶሚኒየም ዕጣ ወጥቶ በኅትመት እንዳይሰራጭ የመስተዳድሩ ጋዜጣ (አዲስ ልሳን) ላይ መታተም ከተጀመረ በኋላ እንዲቋረጥ ተደረገ (ምክንያቱም ጃዋር ተቃውሟል) *** ☞ ጃዋር "ኹለት መንግሥት አለ" ብሎ ነበር፤ "ኹለተኛው መንግሥት" የተባለው ሥራ በማጣት ምሬት በሕዝባዊ አመፅ ሕይወቱን አደጋ ላይ እስከመጣል ሊደርስ የተዘጋጀ ወጣት ነው። ☞ ጃዋር "አዲስ አበባን ቀለበት ውስጥ አስገብተን" ያሻንን ማድረግ እንችላለን ብሎ ነበር፤ ለዚህም "ኹለተኛው መንግሥት የጦር መሣሪያ ነው። ለመኾኑ ኦሮሚያን እያስተዳደረ ያለው ማነው? አዲስ አበባስ ምን ታድርግ? ኢትዮጵያ ውስጥ 'የማንነት ጥያቄ' አለ። ግን ብቸኛው ጥያቄ አይደለም፤ መፍትሔውም ብሔርተኝነት ወይም ደግሞ ብሔረ መንግሥት (nation state) መመሥረት አይደለም። እንደውም ከችግርቹ አንዱ ይኸው ብሔርተኝነት እና ብሔረ-መንግሥት ለመመሥረት ታስቦ የሚሠራው ሥራ ነው። ይኹን እንጂ ብሔርተኝነትን በማጦዝ አንዱ ፖለቲካዊ ተፈላጊነቱን (political relevance) ለመጨመር፣ ሌላው ፖለቲካዊ ታማኝነቱን ለማረጋገጥ፣ ቀሪው ደግሞ በአጋጣሚው ሥልጣን ለመንጠቅ ወይም ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ርብርብ ከሚበጀው ይልቅ የሚፈጀው እየበዛ ነው። እውነተኛ የሕዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማዕከል የኾነችውን አዲስ አበባ እና ነዋሪዎቿን እንደታጋች ቆጥሮ በላይዋ ላይ የውክልና (proxy) ጦርነት እየተካሔደባት ነው። በዚህ ሁሉ ትግል ውስጥ ለሥራ አጥ የኦሮሞ ወጣቶችም ይሁን ...

ለውጡ እና የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ

አሁን እየተካሔደ ያለው የፖለቲካ ለውጥ ፍኖተ ካርታ የለውም በሚል በተደጋጋሚ ተተችቷል። ይልቁንም፣ ሲሆን ሲሆን ለብዙኃን መገናኛዎች አጀንዳ በማበጀት፥ ሳይሆን ሳይሆን ደግሞ “ሚዲያዎች ምን አሉ?” የሚለውን እያሳደዱ መልስ በመስጠት የተጠመደ ለውጥ ነው የሚለው የአደባባይ ምሥጢር ሆኗል። ብዙኃን መገናኛዎች በለውጡ ላይ ይህንን የሚያክል ትልቅ ተፅዕኖ እንዳላቸው ከታወቀ ዘንዳ በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል። ለውጡ ፍኖተ ካርታ ባይኖረውም፥ ብዙኃን መገናኛዎቹ ግን ፍኖተ ካርታ ሊኖራቸው ይገባል፤ “ምን-ለምን-ለማን ነው የሚጽፉት ወይም ለተደራሲዎቻቸው የሚያቀርቡት?” የሚለውን በነሲብ ሳይሆን በነቢብ ቢያድርጉት መልካም ነው በሚል ዓላማ ይህ ጽሑፍ እንደ ምክረ ሐሳብ ቀርቧል። የብዙኃን መገናኛዎች ሚና በጥቅሉ በመሠረቱ የብዙኃን መገናኛዎች ሚና “ትርክት ማኖር” ነው። ዜና፣ ትንታኔ፣ ምርመራ፣ ማጋለጥ… ሁሉም አንድ ዓላማ አላቸው። በትርክት መብለጥ ነው። አንድ ጥሬ ሐቅ ከብዙ አንግሎች ‘ሪፖርት’ ሊደረግና ሊተነተን ይችላል። ሰዎች ያንን ጥሬ ሐቅ እንዴት መረዳት እንዳለባቸው የሚወስኑበት ደጋግመው ከሰሙት ወይም ደግሞ ይበልጥ ካሳመናቸው ትንታኔ አንፃር ነው። ስለዚህ ሁሉም ብዙኃን መገናኛዎች ዋነኛ ዓላማቸው ሐቁን ለዜጎች ማድረስ ነው ቢባልም ቅሉ፥ ዋናው ቁም ነገር ሐቁን የሚተነትኑበት መንገድ ነው። ለምሳሌ ያክል የአድዋ ጦርነትን ብናስታውስ፣ ለኢትዮጵያውያን የምሥራች ሲሆን፥ ለጣሊያኖች ደግሞ መርዶ ነው። የጣሊያን ብዙኃን መገናኛዎች መርዶውን ለዜጎቻቸው ያደረሱት በቁጭት ሲሆን፣ ‘የተነተኑትም ለሽንፈት የዳረገን ምንድን ነው? ለወደፊቱስ ምን ማድረግ አለብን?’ በሚል ነው። በወቅቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ቢኖራት ኖሮ ትንታኔው በተቃራኒው ታቀርብ ነበር። ስለሆነም...

ስድስቱ የኅትመት ብዙኃን መገናኛዎቻችን ፈተናዎች

በኢትዮጵያ የጋዜጦች እና መጽሔቶች አማራጭ አልባነት ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክሪያሲያዊ ስርዓት እንድትሸጋገር በማገዝ ረገድም ይሁን የነቁ እና መረጃ ያላቸው  ዜጎችን በመፍጠር ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዳይጫወቱ  አድርጓል። ጎረቤቶቻችን እነ ኬንያ ከኛ ግማሽ በታች የሕዝብ ብዛት ኖሯቸው ከእኛ እጥፍ ድርብ የበዙ ጋዜጦችና መጽሔቶች በየቀኑ ለስርጭት እና ለንባብ ይበቃሉ። እኛስ ምንድነ ነው ችግራችን? (የሚከተሉት ከልምድ የታዘብኳቸው ፈተናዎች ናቸው፤ አንባቢ ላለማሰልቸት ባጭር ባጭሩ ነው የምጠቅሳቸው።) ፩ኛ፣ የንባብ ባሕል ደካማነት ኢትዮጵያውያን የራሳችን ፊደል ያለን ሕዝቦች ነን እንበል እንጂ አንባቢ ሕዝቦች አይደለንም። የተማሩ ሰዎች ቁጥር ማነስ ብቻ ሳይሆን፣ ፊደል የቆጠሩትም የአንባቢነት ልምድ የላቸውም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ብዙ ጊዜ ጋዜጦቹ እና መጽሔቶቹ የሚነበብ ብዙም አዲስ ነገር የላቸውም ቢባልም፣ እውነቱ ግን የሚነበብ ነገር ይዘው የሚመጡትም ቢሆኑ በቅጡ እየተነበቡ አለመሆናቸው ነው። ጋዜጣና መጽሔት አንባቢዎች ጥቂት ጡረተኞችና የፖለቲካ ወይም የዝነኛ ሰዎች ወሬ ፈላጊዎች ብቻ ናቸው። ስለዚህ የንባብ ባሕል አለመኖሩ የኅትመት ብዙኃን መገናኛውን ከሚያዳክሙት ፈተናዎች ቀዳሚው ነው።  ፪ኛ፣ የሕግ እና አፈፃፀም አፋኝነት ከብሮድካስት ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ እስከ ብዙኃን መገናኛ ነጻነት እና የመረጃ ማግኘት መብት አዋጅ፣ እንዲሁም የሳይበር እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጆች በአንድም በሌላም መንገድ የኅትመት ብዙኃን መገናኛዎችን አዳክመዋል። እነዚህ አዋጆች የተፈጥሮ ነጻነትን እና ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን ከመገደባቸውም ባሻገር የፍርሐት ድባብ በመፍጠር ነጻ ውይይትን፣ ነጻ ሪፖርትን እና ነጻ ምርመራን የ...