Skip to main content

Posts

Showing posts from 2018

Understanding Privileges

[This piece is posted on ' Ekool Ethiopia ' in Amharic.] Some of my Facebook friends make fun of other Facebook users for not being stylish enough like them, for not knowing Amharic/English the way the formers do, for not being ‘Arada’ enough and for being comparatively ‘Fara’. They ridicule the way the formers pose for a photo and also the captions they use when they post their photographs on social media. The terms ‘Arada’ and ‘Fara’ are both coined by the city dwellers in Ethiopia and ‘Arada’ is a title given to the “cool”, “cheer leading”, “stylish” people while ‘Fara’ is a label against those who are oppositely perceived. However, the term ‘Fara’ is mostly applied to refer to those people who were raised in rural areas and those who are desperately struggling to urbanize themselves (or trying to look like one). The division and categorization gets on Facebook from the ground. ‘The Aradas’ consider themselves as superior to ‘the Faras’ and think they deserve better tr...

ምርጫ፦ ቄሮ ‘መንግሥት’ ይሁን ‘ፅንፈኛ’?

በቄሮ ምንነት እና "ድርጊቶች" ላይ በርካታ ውዝግቦች እየተነሱ ነው። ውዝግቦቹ የሚነሱት በሁለት ፅንፎች ነው፦ ፩ኛው ፅንፍ ያሉት ሰዎች "ቄሮ ቅዱስ ነው" ሲሉ፣ ፪ኛው ፅንፍ ያሉት  ሰዎች ደግሞ "ቄሮ እርኩስ ነው" ይላሉ። እኔ ደግሞ ቄሮ እኛ ነህ የምንለውን ይሆናል ባይ ነኝ። እንደኔ እንደኔ የውዝግቡ ሁሉ መንስዔ የቄሮን ምንነት እና የንቅናቄውን ዓይነት፣ እንዲሁም "የትግሉን" ወይም ደግሞ "የድሉን" ባለቤት ካለመረዳት የመጣ ነገር ይሆን ይሆናል በማለት ነው ይህንን ጽሑፍ ለአማራጭ አስረጅነት ያዘጋጀሁት። እግረመንገዴንም ለውዝግቡም ይሁን ለውዝግቡ መንስዔ የሆኑ ተቃርኖዎችን እዳስሳለሁ። ዓላማዬ ከፅንፉ እና ከፅንፉ ወዲህ ዓለም እንዳለ ለማሳየት እንጂ መሞከር ብቻ ሳይሆን ፍረጃችን ተፅዕኖ እንዳለው ማስታወስም ጭምር ነው። ቄሮ - ሥያሜው ምን ይነግረናል? 'ቄሮ' ቃሉ 'ያላገባ፣ ያልወለደ' ወጣትን ይወክላል። ነገር ግን ወጣት የሚለውን ቃል የሚተኩ ሌሎች የኦሮምኛ ቃላት አሉ። እነዚህም 'ደርደሩማ'፣ 'ደርገጌሳ' እና 'ጎሮምሳ' የሚሉት ቃላት ምሳሌ ይሆናሉ። ቄሮ የሚለው ቃል ምንጩ 'ቄረንሳ' ከሚለው እና ነብር የሚል ትርጉም ካለው ቃል የተቀዳ እንደሆነ ይነገራል። ስለዚህ ቄሮ ማለት እንደነብር ያለ ብርቱ ወጣት ማለት ነው፣ ማለት እንችላለን። ይሁን እንጂ አሁን በተለይ በኦሮሞ ፖለቲከኞች ዘንድ 'ቄሮ የሚለው ቃል ፍቺ 'አብዮተኛ ወጣት' የሚል ትርጉም አለው። "የቄሮ ንቅናቄ" ውልደት እና ዕድገት ቄሮ የሚለው ቃል የፖለቲካ መድረኩ ውስጥ የገባው እ.ኤ.አ. በ2011 የአረቡ አብዮ...

በዴሞክራሲ ተስፋ መቁረጥ? (አይታሰብም!)

ትላንት አንድ የስዊድን ጋዜጠኛ "ሐሳብን ከመግለጽ ነፃነት ይልቅ ደኅንነቴን እመርጣለሁ" የሚል አስተያየት አዲስ አበባ ላይ እንደገጠማት ነገረችኝ። ዛሬ ደግሞ በጥዋቱ አንዲት አሜሪካዊ ጓደኛዬ በዋትሳፕ "ብጥብጥ ካለበት ዴሞክራሲ ይልቅ ሠላማዊ አምባገነንነት ይሻላል" የሚል ክርክር እንደገጠማት ነገረችኝ። በጣም ነው ያዘንኩት፤ ምክንያቱም እዚህ ድምዳሜ ላይ እንድንደርስ የሚፈልጉ የፖለቲካ ቡድኖች እንዳሉ አውቃለሁ። በመሠረቱ ዛሬ በጉዳዩ ላይ በአጭሩ መሞነጫጨር የፈልግኩት በነዚህ ሰዎች ብቻ አስተያየት ተነሳስቼ አይደለም። "ጭቆና ለምደን ነፃነት መሸከም አቃተን" የሚሉ አስተያየቶችን ደጋግሜ እሰማለሁ። ስህተቱ የሚጀምረው ዴሞክራሲም ይሁን ነፃነት ላይ "ደርሰናል" ከሚለው ድምዳሜ ነው። አሁን ያለንበት ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ ነፃነት ለማዋለድ በምጥ ላይ ነው ቢባል ይሻላል። እንደ አዋላጆቹ ብቃት ፅንሱ (ዴሞክራሲው) ይወለዳል ወይም ይጨናገፋል። አዋላጆቹ ካላወቁበት ደግሞ ፅንሱ እናትየውን ጨምሮ ይዞ ሊሔድ ይችላል። ስለዚህ ድምዳሜያችን ጥንቃቄ የሚያሻውን ጉዳይ ችላ እንድንለው ሊያደርገን ይችላል። ግን ዋነኛው የአረዳድ ችግር የዚህ ጉዳይ ብቻ አይደለም። ሠላም በአምባገነንነት እና በዴሞክራሲ ውስጥ አምባገነንነት ሕዝቡ "በቃኝ" ብሎ ቀና እስከሚል ድረስ ረግጦ የመግዛት ስልተ መንግሥት ነው። አምባገነኖች የበቃኝ ነጥብ ከመድረሷ በፊት ሁሉንም ነገር ስለሚያፍኑ ሠላም ያለ ያስመስላሉ። በአምባገነናዊ ስርዓት ውስጥ ፀጥታ ስላለ ሠላም ያለ ይመስላል። ነገር ግን የታፈነ አመፅ አለ፤ የታፈነ ደም መፋሰስ አለ። ስለ አመፁም ይሁን ስለ ደም መፋሰሱ መነጋገር አይፈቀድም። የመረጃ ምንጮችም ይታፈናሉ። በአምባገነናዊ...

የትግራይ ፖለቲካ እንደምን ወደዳር አገር ፖለቲካ ተገፋ?

የኢትዮጵያ ሥርወ መንግሥት መነሻ ማዕከሉ (core state የሚሉት) ሰሜን ላይ ነበር - አክሱም። ቀስ በቀስ ወደ ደቡብ እያፈገፈገ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማገባደጃ ላይ ሸዋ ላይ ከትሞ እስከ ዛሬ ዘልቋል። 'የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ' በአሁኑ ቅርፅዋ የተሠራችው በ19ኛው ክፍለዘመን ማገባደጃ ነው። ከዛሬዪቱ ኢትዮጵያ በፊት የነበረችው 'ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ' ነች። ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ እንደሌሎቹ የዓለማችን ጥንታዊ አገራት ሁሉ፣ ድንበር አልነበራትም - የተፅዕኖ አድማስ እንጂ።  የተፅዕኖ አድማሷ ደግሞ እንደ ጊዜው እና እንደ ነጋሹ አቅም ሲሰፋና ሲጠብ ነው የከረመው። ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ የአማርኛ ተናጋሪዎች እና የትግርኛ ተናጋሪዎች በዋነኝነት የሚዘውሯት ነበረች። በተለይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ወዲህ ያለችው ኢትዮጵያ በሁለቱ ፉክክር እና ማመቻመች (compromise) ነበር የቆመችው። ዳግማዊ ምኒልክ ደቡቡን እና ምሥራቁን የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ አካል ባደረጉበት ወቅት ግን በቁጥር ከትግርኛ ተናጋሪዎቹ እና ከአማርኛ ተናጋሪዎቹ የሚበልጡ ኦሮሞዎች የአገረ መንግሥቱ አካል በመሆናቸው፥ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች በፊት ከነበራቸው ተቀናቃኝነት የበለጠ ኃይል አግኝተዋል። ይህ ክስተት ኢትዮጵያን ሦስተኛ የሥልጣን ተፎካካሪ እንድታገኝ አድርጓታል። (ይህ ማለት ግን ከዚያ በፊት ኦሮሞዎች የአገረ መንግሥቱ አካል አልነበሩም ማለት አይደለም፤ ሸዋ ቀድሞውንም ቅይጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ በ16ኛው ክፍለ ዘመን 'ታላቁ የኦሮሞ ፍልሰት' የኦሮምኛ ተናጋሪዎች ሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል ተቀላቅለዋል። ይህም የወሎና የጁ ኦሮሞ ፖለቲከኞችን አፍርቷል። በዘመን ወደኋላ በነጎድን ቁጥር ታሪኩ ይለዋወጣል፤ ስለዚህ ርቀን ባንሔድ ጥሩ ነው። የዚህ ጽሑፍ ዓላማም ዛሬን...

ብሔርተኝነት፤ ቅዱስ ወይስ እርኩስ?

በዚህ ርዕስ ረዥም መጣጥፍ መጻፍ ከጀመርኩ ረዥም ግዜ ሆነኝ፡፡ እስካሁን አላለቀም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፤ ጉዳዩ ስሜት የሚነካ እና በስሜት የሚነዳ ስለሆነ ፈርቼው ነው፡፡ የፖለቲካ ተዋስኦዋችንን በተከታተልኩት ቁጥር የተረዳሁት አንድ ነገር ቢኖር "ብሔርተኛ ነኝ" በሚሉ እና "ብሔርተኛ አይደለሁም" በሚሉት ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ብሔርተኝነትን የማመን እና የመሸሸግ ችሎታ ልዩነት ነው፡፡ ወይም ደግሞ አንዳንዴ ልዩነቱ ግለሰቦቹ የሚያራምዱት ብሔርተኝነት የሚያቅፋቸው ሰዎች ቁጥር የበዛ መሆኑ ‹ብሔርተኝነቱን› የመሸሸግ ዕድል ያገኛል፡፡ በጣም በተሳሳተ መደምደሚያ ላለመጀመር ያክል "ብሔርተኝነት" ደረጃው እና ልኩ ይለያይ ይሆናል እንጂ ሙሉ ለሙሉ ከውስጡ የወጣለት ሰው የማግኘት ዕድላችን ጠባብ ነው ብለን እንስማማ፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ‹ብዙኃን ብሔርተኛ ናቸው› የሚል መደምደሚያ ይዤ ነው ይህንን የምር አጭር ያልሆነ መጣጥፍ፣ ረዘመብኝ ካልኳችሁ መጣጥፌ ጨልፌ እና ጨምቄ የማስነብባችሁ፡፡ የመጀመሪያው አንቀፄ እንደሚያመለክተው ‹ብዙኃን ብሔርተኞች ናቸው›፡፡ ‹ብሔርተኝነት ቅዱስ ነው ወይስ እርኩስ?› የሚል ጥያቄ ማንሳት ‹ብዙኃን ቅዱስ ናቸው ወይስ እርኩስ?› የሚል ጥያቄ እንደማንሳት ያስፈራል፡፡ ቢሆንም እንጋፈጠዋለን። ብሔርተኝነት ሲበየን ብዙዎቹ ዓለም ዐቀፍ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ያሉ ምሁራን ለብሔርተኝነት ያላቸው ንቀት የትየለሌ ነው፡፡ ንቀቱ አንድም ብሔርተኝነት ‹ማኅበራዊ ፈጠራ› (social fabrication) ነው ከሚል የመነጨ ሲሆን፣ በሌላ በኩል የሰው ልጅን ያክል ባለ ብሩሕ አእምሮ በአጋጣሚ በበቀለበት ማኅበረሰብ ብቻ መበየን ከእውነታው የራቀ ስለሚሆን ነው፡፡ የሆነ ሆኖ የብሔርተኝነት የመዝገበ...

የማንን ግዛት ማን ያስተዳድር?

ነገሮችን አቃልሎ እና ሸንሽኖ ለመረዳት መሞከር ጠቃሚ የሚሆንበት አጋጣሚ ቢኖርም፥ ሁሌም ትክክለኛ ውጤት አያስገኝም። አገርን የሚያክል ትልቅ ፅንሰ-ሐሳብ በግለሰብ ርስት ዓይን  ለመረዳት መሞከርም ከዚህ ዓይነቱ አደገኛ ስህተቶች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ 'እከሌ የተባለው ግዛት የማን ነው?' እና 'እከሌ የተባለውን ግዛት ማን ያስተዳድር?' የሚሉት ጥያቄዎች ዐውድ በጣም አሳፋሪ እና 'ገና በዚህ ጉዳይ እንኳ መግባባት አልቻልንም እንዴ?' በሚል ራሳችንን እንድንታዘብ የሚያደርግ የዘወትር ገጠመኝ ነው።  'አዲስ አበባ የማነች?' የሚለውን ጥያቄ ደጋግሞ መስማት አስደናቂ አይደለም። የቡድን ሥም እየጠሩ፣ ታሪክ እየደረደሩ የባለቤትነት ማስረጃ ለማምጣት የሚሞክሩትን ሰዎች መከራከሪያ ማድመጥም የከተማዋን ኅልውና ያክል አዲስ ነገር አይደለም። የዚህ ጽሑፍ መነሻም የምክትል ከንቲባዋን ሹመት ተከትሎ የዚህ ክርክር እንዳዲስ ማገርሸት ነው። አዲስ አበባ የማን ነች? እነማን ናቸው ሊያስተዳድሯት የሚገባቸው? መጀመሪያ ግን ኢትዮጵያ ራሷስ የማነች? ኢትዮጵያ የማነች? ቢያንስ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ኢትዮጵያ የምንላት ሕዝቧን፣ ግዛቷን፣ መንግሥቷን እና ሌሎች የዓለም መንግሥታት የሚቀበሉትን ሉዓላዊነቷን ነው። ሉዓላዊነት የአገር ፅንሰ-ሐሳብነት መገለጫ ነው። በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ላይ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች "የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች" ናቸው (አንቀፅ 8)። ይህ ማለት 'ኢትዮጵያ የኦሮሞ፣ አማራ፣ ሶማሌ፣ ትግራዋይ፣ ወዘተ የጋራ ንብረት ናት' የሚል ትርጉም ይሰጣል። ከላይ ሲታይ 'ኢትዮጵያ የሁሉም ናት' የሚል ጭብጥ ያለው ይመስላል። ነገር ግን ...

ለውጥ እና ውዥንብር

አሁን ያለንበት ሁኔታ "ታስሮ የተፈታ ጥጃ" ሁኔታ ነው። መዝለል እና መቦረቅ - የነፃነታችንን ልክ መፈተን የምንፈልግበት ወቅት ነው። ምክንያቱም ነፃነታችን ከእስር የተፈታው ገና አሁን ነው፣ የዴሞክራሲ ባሕል አልነበረንም፣ በዚያ ላይ ያልተመለሱ እልፍ ጥያቄዎች አሉን። ይሁን እንጂ ሲደክመን እንሰክናለን። መዝለል ስለምንችል ብቻ አንዘልም። መርገጥ ስለምንችል ብቻ አንራገጥም። ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በተደራጀ፣ በሕጋዊ እና ሠላማዊ መንገድ ታግለን ማስመለስ እንጀምራለን። ከዚያ በፊት ግን ዝላያችን እና እርግጫችን ለገዢዎቻችን የለውጡን ተስፋ ለመቀልበሻ፣ እኛን መልሶ ለመርገጫ ምክንያት እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። አንዲት ኤርትሪያዊት የትዊተር ተጠቃሚ፣ 'ሰውያችሁ ባለ ግርማ ሞገስ እና ጥሩ ተናጋሪ በመሆኑ እንዳትሸወዱ፣ የእኛም መሪ እንደዛ በመሆኑ የለውጡን ተቋማዊነትን ሳናረጋግጥ ነው ለዚህ የተዳረግነው' የሚል መልዕክት ለኢትዮጵያውያን አቻዎቿ አስተላልፋለች። አዎ፣ የዛሬው ታላቁ አምባገነን ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የዛሬ 27 ዓመት ገደማ በኤርትራውያን ዘንድ ታላቅ ሕዝባዊ ይሁንታ ያለው መሪ ነበር። " ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከራሳቸው መጠበቅ " በሚለው ጽሑፌ 'ብዙዎቹ ነጻ አውጪዎች ኋላ አምባገነን ይሆናሉ' ማለቴን እንደ ጅምላ ድምዳሜ የወሰዱብኝ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። እኔ ለማመልከት የፈለግኩት በአንድ ወቅት 'ነጻ አውጪ' የነበረ፣ ሌላ ግዜ 'አምባገነን' እንደማይሆን አያረጋግጥም ነው። ይህ እንዳይሆን ብቸኛው ዋስትና 'ቁጥጥርና ሚዛን' (check and balance) ነው። ትላንት ጓደኞቼ ስለ ኢዲ አሚን ዳዳ አንድ ጽሑፍ እያስነበቡኝ ነበር። ከዓለማችን የ...

የማንነት ብያኔ አፈና…

ከእኛ አገር የማያልቁ ችግሮች መካከል አንዱ የማንነት አረዳድ እና አበያየን ጉዳይ ነው። ማንነት እና ምንነት የፖለቲካ ጫወታችን አስኳል ሆኖ ሳለ፣ የማንነት አበያየናችን ግን ግለሰቦች የራሳቸውን ማንነት የሚበይኑበት ነጻ ዕድል የማይሰጥ ነው።  የኦነጉ በያን አሶባ ባንድ ወቅት ከኢሳት ቴሌቪዥን "ኦሮሞ ማነው?" የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። "ኦሮሞ ነኝ ያለ" የሚል ምርጥ መልስ ሰጥተዋል። ነገር ግን ብዙዎች ማንነትን በዘር የሚወረስ እንጂ በማኅበራዊ-ሥሪት (social construction) የሚመጣ ነገር አድርገው አይመለከቱትም። እውነት መሆኑን ከራሷ ማረጋገጥ አልቻልኩም እንጂ ድምፃዊ ሴና ሰለሞን ከአማራ ተወላጆች የተወለደች ኦሮሞ ነች፤ "ኦሮሞ ነኝ" ስላለች። ራሷን የምትገልጸው እንደ ኦሮሞ ሲሆን፣ በዘፈኖቿ የታገለችውም ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት ነው። የወላጆቿ የማንነት ታሪክ የሐሰት ወሬ ቢሆን እንኳ ነባራዊ ምሳሌ እናጣለን እንጂ፣ ምሳሌው ማንነትን የመምረጥ ግለሰባዊ ነጻነቱን የተሳሳተ አያደርገውም።  'ኢትዮጵያዊ ማንነት አለ፣ የለም? ጎጃሜ ማንነት አለ፣ የለም? አዲሳበቤ ማንነት አለ፣ የለም?' የሚሉት ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ምንጫቸው የግለሰቦች ማንነት እኛ ራሳችንን እንዲሁም ሌሎችን ከምንረዳበት መንገድ ውጪ መወሰን የለበትም ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ነው። በቀላል ቋንቋ ለመግለጽ አባባሉ "እኔ ናችሁ ከምላችሁ ውጪ መሆን አትችሉም" ነው።  በበኩሌ ሰዎች የራሳቸውን ማንነት ብለው የሚጠሩት ወይ 'የሚኮሩበትን' አሊያም 'የተበደለባቸውን' [ወይም የተበደለባቸው የሚመስላቸውን] ማንነታቸውን ነው ብዬ ነው የማምነው። ይሁን እንጂ ሁሉም ሰዎች ማኅበራዊ ሥሪታቸው ከብዙ ...

የተዘነጋው የኮንሶ እስረኞች ጉዳይ ("እኛስ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወይ?")

ፎቶው ላይ ከግራ ወደቀኝ የሚታዩት፤ የኮንሶ መሪ ካላ ገዛኸኝ እና ወንድማቸው በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ሕዝባዊ አመፆች በተቀጣጠሉበት ወቅት፣ በሕዝብ ብዛት ትንሿ ኮንሶም ከዐሥር ወራት ላላነሰ ጊዜ ሕዝባዊ ተቃውሞ ታደርግ ነበር። በወቅቱ የመብት ተሟጋቾች አመፁ አገር ዐቀፍ እንደሆነ ለማስረዳት እንደምሳሌ የኮንሶን ጉዳይ ደጋግመው ይጠቅሱት ነበር። በወቅቱ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሠላማዊ ተቃውሞዎችን በኃይል በመበተን፣ ብዙዎችን ወደ እስር ቤት አጉረዋል። ከነዚህ እስረኞች ውስጥ የኮንሶ የጎሳ መሪ የሆኑት ካላ ገዛኸኝ ወልደዳዊት ካዮቴ ይገኙበታል። ('ካላ' በጎሳ መሪነት የሚገኝ የጎሳ ሐረግ ማዕረግ ነው።) ካላ ገዛኸኝ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በሲቪል ምሕንድስና ተመርቀዋል። የጎሳ መሪነቱን ከአባታቸው የወረሱት በጥቅምት 2006 በባሕላዊው ወግ መሠረት ከአባታቸው ነበር። የጎሳ መሪው በኮንሶ ማኅበረሰብ ልማድ መሠረት ልማዳዊ ዳኝነት፣ ግልግል እና ሌሎችም ማኅበራዊ አስተዳደር ይሰጣል። ይሁን እንጂ የአሁኑ የጎሳ መሪ ካላ ገዛኸኝ ሠላማዊ ሕዝባዊ ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት ከሌሎች የኮንሶ ብሔረሰብ አባላት ጋር ለእስር ከተዳረጉ እና ከማኅበራዊ ኃላፊነታቸው ከተገለሉ አንድ ዓመት ከ10 ወራት አለፏቸው። ካላ ገዛኸኝ በተከሰሱበት መዝገብ ብቻ 43 ሰዎች ተከስሰዋል። ያነጋገርኳቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እንደነገሩኝ ግን የጠቅላላ እስረኞቹ ቁጥር 467 ነው። እነዚህ ሕዝባዊ ጥያቄ ያነሱ የኮንሶ ብሔረሰብ አባላት በጊዶሌ ማረሚያ ቤት፣ ኮንሶ ፖሊስ ጣቢያ እና አርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት ታስረው ይገኛሉ። ካላ ገዛኸኝ እና ሌሎችም 180 ገደማ ሰዎች የታሰሩት በአርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት ነው።  ከእስር ውጪ ከመንግሥት የሥራ ገበታቸው ተ...

በማንነት ማፈናቀልን እንዴት መቀነስ ይቻላል? (የግል ጥቆማ)

(ከታች ያስቀመጥኳቸው ጥቆማዎች በጥናት ላይ የተመሠረቱ የመፍትሔ ሐሳቦች ሳይሆኑ በግል ትዝብት የተጠቆሙ ናቸው። በምስሉ ላይ የሚታየው (ፎቶ: ቴዎድሮስ አያሌው) በ1977 ድርቅ ወቅት ደርግ ቄለም ወለጋ አስፍሯቸው የነበሩ እና አሁን ተፈናቅለው አላማጣ የሚገኙ ናቸው። በምስሉ እንደሚታየው አብዛኛዎቹ የተወለዱት እዚያው አካባቢ ሲሆን፣ ወላጆቻቸው እና አያቶቻቸው ናቸው ከአላማጣ ነበር ቄለም ወለጋ እንዲሰፍሩ የተደረጉት።) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ 'የማንነት' እና 'የብሔር' ፖለቲካ ወይም ጥያቄ ተምታተዋል። ብዙ ግዜ ሁሉም ነገር 'የብሔር ጥያቄ' ነው፤ መልሱም የሚገኘው 'በብሔርተኝነት' ነው የሚባለው ጉዳይ ከማንነት ጋር የተያያዘውን ጥያቄ ያድበሰብሰዋል። እንዲያውም አንዳንዴ ብሔርተኝነት ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል። የማንነት ወይም የብሔር ትርጉሙም እንዲሁ የተምታታ ነው። ምክንያቱም ማንነትም ይሁን ብሔር በተለምዶ የሚበየነው በቋንቋ ላይ ተመሥርቶ ነው። ስለዚህም በተምታታ ትርጉም ላይ የተመሠረተ ብሔርተኝነትም ለተሳሳተ ጥያቄ የተሳሳተ መልስ ለመስጠት ይዳርጋል። ማንነት በቋንቋ ሊመሠረት ይችላል፤ ነገር ግን አንድ ቋንቋ እየተናገሩ የተለያየ ማንነት ያላቸው ግለሰቦች ወይም ሕዝቦች አሉ። ማንነት በፆታ ብቻ ሊወሰን ይችላል። ወይም ደግሞ በፆታዊ ግንኙነት ምርጫ ሊወሰን ይችላል። በመልክ ወይም በቆዳ ቀለም። ወዘተ… ለምሳሌ ያክል ቱትሲዎች እና ሁቱዎች አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሆነው፣ ልዩነታቸው የመልክ (እና የታሪክ ድርሻ) ነው።  ፌዴራሊዝሞች የአወቃቀር ስርዓታቸው ምንም ቢመስል፣ ዋነኛ ዓላማቸው በብሔርተኝነቶች መካከል ውጥረቶችን ሥልጣን በማከፋፈል እና በማጋራት ማርገብ ነው። የእኛው ግን ውጥረቱን ምናልባትም አባብሶታል አልያ...

የተቃውሞው ጎራ ለምን ደነገጠ? (What to do next?)

ኦሕዴድ እና ብአዴን በሕወሓት የበላይነት ይመራ የነበረውን የኢሕአዴግ ፖለቲካ ከውስጥ መነቅነቅ ሲጀምሩ ተቃዋሚዎች ተደስተው ነበር። ኦሕዴድ በክልሉ አንፃራዊ የተቃውሞ-ነጻነት ሲፈቅድም እንዲሁ ተደስተዋል። ነገር ግን የዐብይ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እና የተቃዋሚውን ቋንቋ መነጋገራቸው ድንጋጤ ፈጥሯል። ባጭሩ ተቃዋሚዎች ከኢሕአዴግ ጋር "መደራደር ይገባናል" ሲሏቸው የነበሩት ጉዳዮች - የፖለቲካ እስረኛ ማስፈታት እና አንዳንድ አዋጆችን ማሻሻል፣ በጥቅሉ የፖለቲካ ምኅዳሩን የማስፋት ጥያቄ እና ተቋማትን ከፖለቲካ ጥገኝነት ማላቀቅ - የመሳሰሉትን ነገሮች በራሳቸው በኢሕአዲጉ ሊቀ መንበር ሲቀነቀን፣ ተቃዋሚዎች አጀንዳ አጥተዋል። የድንጋጤያቸው ምንጭም ይኸው ይመስላል። በርግጥ የፖለቲካ ድርጅቶቹ ሲያልፉበት ከነበረው ፈታኝ ሁኔታ አንፃር በመዳከማቸው የፖለቲካ ለውጦችን እያዩ ከወቅቱ ጋር የሚሔድ ፖለቲካ መጫወት ቢያቅታቸው የሚገርም አይደለም።  የፖለቲካ ድርጅቶቹ "የአኩራፊዎች እና የጡረተኞች መሰብሰበቢያ" እየተባሉ ሲተቹ ከርመዋል። ምንም እንኳን ከላይ ያሉ ቢመስልም ውስጣቸው በብዛት ባዶ ነው። ለኢትዮጵያ (100 ሚሊዮን ሕዝብ) የሚመጥን የመምራት አቅም ያላቸው ሰዎች ስብስብ የላቸውም። በመገናኛ ብዙኃን በሚራገቡ አጀንዳዎች ላይ የመንግሥትን አቋም ካወቁ በኋላ ተቃራኒውን ይዘው ከመሟገት በላይ ርዕዮተ ዓለማዊ አቅጣጫ የሌላቸው ድርጅቶች ቀላል አይደሉም። አንዳንዶቹ ከላይ ያሉትን ታዋቂ ሊቀ መንበሮቻቸውን የሚተኩ አባላት እንኳን አላፈለቁም። ኢትዮጵያን መምራት የሚችሉ በርካቶች ድግሞ ወይ የፖለቲካውን ትኩሳት እየፈሩ አንገታቸውን ደፍተው 'ዝምተኛ-ብዙኃን' መሐል ተቀብረዋል፤ አልያም ተሰድደዋል። በዚህም ምክንያት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶቹ...

ሰው መሆን…

የሰው ልጆች ሰው ለመሆን ማለቂያ የሌለው አብዮታዊ ጉዞ ውስጥ ናቸው፡፡ እንደመታደል ሆኖ፣ የሰው ልጆች የላቀ እና እየላቀ የመጣ አእምሮ ባለቤት በመሆናቸው ምድርን እንደግል ንብረታቸው፣ ራሳቸውንም ተለይቶ እንደተመረጠ ፍጡር እየቆጠሩ፣ ምድርን ለራሳቸው ምቾት እያሾሩ ዛሬ ላይ ደርሰዋል። የሰው ልጆች በሠለጠኑ ቁጥር ርሕራሔያቸው እየጨመረ፣ አውሬነታቸው እየቀነሰ መጥቷል። የራሳቸውን ነጻነት የሚያከብሩትን ያክል የሌሎችንም ለማክበር እየተጉ መጥተዋል። የሰው ልጆች ዛሬ ከራሳቸው አልፈው ስለአካባቢያቸው ብዝኃ ሕይወት እስከመጨነቅ ደርሰዋል። የሰው ልጆች ረዥም ጉዞ ገና አላለቀም። የሰው ልጆች ሰው የመሆን ጉዞ የት ተጀመረ? በየት በኩል አለፈ? ዛሬ የት ደረሰ? ነገስ ወዴት ይጓዝ ይሆን? የዚህ መጣጥፍ ዓላማ የሰው መሆንን ጉዞ በወፍ በረር በመቃኘት የሰውነትን ዓላማ መገመት ነው። ቶማስ ፍሬድማን ሉላዊነት 3ኛው ደረጃ ላይ እንደደረሰ ጽፏል። የመጀመሪያው ደረጃ የአገረ-መንግሥታት እርስበርስ መተሳሰር ነው። ሁለተኛው ደረጃ የንግድ ኩባንያዎች ብዙ አገራት ላይ መሥራት መቻልና እርስ በርስ ግንኙነት ነው። የመጨረሻውና ሦስተኛው ደረጃ የሰዎች ድንበር ዘለል የአንድ ለአንድ ግንኙነት፣ የትብብር እና የውድድር ዕድል መጨመሩ እና መጠናከሩ ነው። እውነትም ዛሬ ሉላዊ ዜጋ (global citizen) መሆን ከመቼውም ግዜ በላይ ቀሏል። ይህ ክስተት የሰው መሆን ጉዞ አቅጣጫ ድንበር የለሽ የዓለም ዜጋ መሆን መሆኑን ይጠቁመን ይሆን? በዓለማችን አሁን ላይ በአንድ ወቅት 7 ሺሕ ገደማ ቋንቋዎች ነበሩ። በአጥኚዎች ትንበያ መሠረት ከነዚህ ውስጥ በመጪዎቹ መቶ ዓመታት ውስጥ የሚቀሩት መቶዎቹ ብቻ ቢሆኑ ነው። በተረፈ ቀሪዎቹ ወይ ተናጋሪ በማጣት፣ ወይ ከሌላ ጋር ተዳቅለው አዲ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከራሳቸው ማዳን!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተስፋን-በጥንቃቄ (cautious optimism) ካነገቡት ሰዎች አንዱ ነኝ። የተስፋዬ መሠረቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን የመጡበት መንገድ፣ የገቧቸው ቃልኪዳኖች እና አሁን የታየው መረጋጋት ናቸው። አሁን የታየው መረጋጋት ስል የቄሮዎች የአደባባይ ተቃውሞ መቆሙን ማለቴ አይደለም። ተቃዋሚዎችን እያሳደዱ መከታተል፣ ማዋከብ እና ማሰር ርቀን ሳንሔድ አምና ከነበረው አንፃር እንኳ ልዩነቱ የትየለሌ ነው። ለዚህ የራሴን ስሜት እና ተሞክሮ ነው በምሳሌነት የማቀርበው። በፊትም አሁንም ሐሳቤን በነጻነት እገልጻለሁ። ነገር ግን አምና እና ካቻምና ከያንዳንዱ ጽሑፎቼ/ንግግሮቼ ቀጥሎ እስር ይመጣል እያልኩ እየሰጋሁ ነበር የማደርገው። አሁን ምን ያክል ይዘልቃል የሚለው ቢያሰጋኝም እታሰራለሁ እያልኩ በየደቂቃው አልባትትም። በፊት ሲያስሩ፣ ሲያዋክቡ እና ሲከስሱ ከነበሩት አንዳንድ ኃላፊዎችም ጋር ባጋጣሚዎች አውርቻለሁ። ከላይ ለውጥ ያለ ሲመስል እነርሱም ከታች ይለወጣሉ። አንድ ከፍተኛ የፌዴራል ፖሊስ ኃላፊ የኛን እንቅስቃሴ "የበፊቱ አመራር እንደ ወንጀል ያየው ስለነበር ወንጀል ነበር። አሁን ግን እንደወንጀል አይታይም" ብለውኛል። ይህ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰዎች ላይ የተፈጠረው የ"ለውጥ መጥቷል" ስሜት እና የፍርሐት ማጣት ከተጠቀሙበት ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ትልቅ ዕድል ነው። ሌላው ሌላው ሁሉ ለዘለቄታው ለመቅረፍ ረዥም የፖለቲካ እና የሥራ ባሕል አብዮት የሚፈልግ ፈርጀ ብዙ የሁላችንም ችግር ነው።

From OPDO Sensation to Abiy Mania

In an inaugural speech, Prime Minister Abiy Ahmed Ali turned almost all pessimists in to EPRDF enthusiasts. It is like he has all traits of a leader 'naturally'. His charisma coupled with his fluency in three local languages of "the competing nationalities" made him look like the right person to fix the mess Ethiopian state is in. But, is he really the person to fix Ethiopia? Or, should we hope something else? Overlaping Interests: Source of Support It has been a bit long since OPDO officials pretend a dissenter within EPRDF. Their dissent was about their regional autonomy at first. This overlapped the interests of opposition groups and has gotten OPDOs unprecedented support from the protestors and general population. The overwhelming support OPDO received regionally encouraged them to have a deserved representation in the Federal Government. Besides, the regional autonomy was interfered by federal authorities who didn't like to accept OPDO's diss...

Resignation of the Prime Minister: Beginning of Collapse to EPRDF or of Reform?

(Recap the Past Decades of EPRDF's Rule) It all started when the Ethiopian national election ended in crisis 13 years ago. But, it became very interesting when the beginning of an end of an era gives a hint with the resignation of a Prime Minister for the first time in Ethiopia's experience.  On the 15th of February 2017, expected yet surprising breaking news hit Ethiopian media. The Prime Minister wrote a letter of resignation from both his premiership of the country and chairmanship of the ruling coalition of Ethiopian People's Democratic Revolutionary Party, EPRDF. Prime Minister Hailemariam Desalegn's resignation was expected because it was rumored; and, it was also surprising because the news came earlier than the long-awaited EPRDF conference which is a feast of reshuffle. The resignation is a combination of both lack of his competency and manifestation of internal dispute within the coalition.  Thirteen years ago, the contested national election ...

የኢትዮጵያ ስርዓተ ናሙና እውን (ከሕግ አንፃር) ፌዴራላዊ ሊባል ይችላል?

(ይህ ጽሑፍ በ1992 ከታተመው "Ethnic Federalism in a Dominant Party State: The Ethiopian Experience 1991-2000" ከሚለው የሎቪስ አለን ጥናት ውስጥ ካለ ንዑስ ርዕስ ተቀንጭቦ የተተረጎመ ነው።) በሽግግር መንግሥቱ ግዜ የታተሙት ዐዋጆች ሁሉ ክልሎች እና ንዑስ ክፍሎቻቸው የማዕከላዊ መንግሥቱ ምንዝሮች እንደሆኑ ተመልክቷል። የሽግግር ምክርቤቱ ለብሔሮች ‹የራስን ዕድል በራስ መወሰን› የሚል ቃል በስተቀር የክልሎች ሥልጣን የተገደበ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተማከለ፣ አሀዳዊ፣ ወይም ፌዴራላዊ ስለመሆኑ ምንም አይታወቅም ነበር። የ1987ቱ ሕገ መንግሥት ግን ይህንን ግራ መጋባት ቀርፎታል። አሀዳዊውን ስርዓት በመተው ፌዴራላዊውን እንደሚከተል በግልጽ ያስቀምጣል (አንቀፅ1)። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የፌዴራል አወቃቀር ላይ በርካታ እንግዳ እና አሻሚ ነገሮች አሉ። ይህም ከነባር ፌዴሬሽኖች የፌዴራል ኅልዮት እና አተገባበር አንፃር ይገጥማሉ ወይም ይጋጫሉ የሚለውን የመደምደሙን ነገር  ከባድ ያደርገዋል። የመገንጠል መብት፣ ለፌዴሬሽኑ አባል አገረ-መንግሥታት ፈንታ ሉዓላዊነት "ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች"  መሰጠቱ፣ ገለልተኛ የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት አለመኖር፣ እና ጠንካራው የሥራ አስፈጻሚ አካል ለዚህ ውስብስብ ባሕሪው ተጨማሪ ምክንያቶች ናቸው። የክልሎች ሥልጣን ተቃርኖ በኢትዮጵያ ፌዴራል አወቃቀር ግልጽ የሆነ አያዎ እንዳለ ብዙ ጸሐፊዎች አስፍረዋል። በአንድ በኩል ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የተወሰኑ ሁኔታዎችን አሟልተው የመገንጠል መብት ተሰጥቷቸዋል። ይህ ከሌሎች የፌዴራል ስርዓታት በተለየ የፌዴራሉ አካላትን ነጻነት የተለጠጠ ያደርገዋል። በሌላ በኩል፣ የ...

የኃይሌ ገ/ሥላሴ ችግሩ፣ በሀብት መክበሩ!

ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ የዛሬ 8 ዓመት ገደማ፣ በመስከረም ወር 2003ቱ የኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ ተገኝቶ ንግግር አድርጎ ነበር። እናም "እናንተ ፖለቲካውን ሥሩ፣ ንግዱን ለኛ ተዉልን" የሚል ንግግር አድርጓል። ንግዱን አልተዉለትም። ሆኖም ምንጩ በሚታወቀው ሀብቱ እየተፎካከራቸው ነው። እነርሱ በወቅቱ የፈለጉት በሕዝቡ የሚወደደውን ሰው ወደ መድረካቸው በማምጣት ከሕዝባዊ መውደዱ መሻማት/መፎካከር ነበር። ከዚያ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ግዜ ክብረወሰን ሲሰብር የለበሰውን ቲሸርት ለወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሥጦታ አበረከተላቸው። መብቱ ነው ግን ይህም አልበቃው፣ በአትሌቲክስ ሜዳ ክብረወሰን ሲሰብር ከተሰማው ደስታ ይልቅ እዚያ መድረክ ላይ በመገኘቱ የተሰማው ደስታ እንደሚበልጥ ተናገረ። ይሁን። ዞሮ ዞሮ ግን ኃይሌ ለዚህ ሙገሳው በምላሹ የጠየቀው 'ውለታ' "ንግዱን ተዉልን" የሚል ብቻ ነበር። በርግጥ ከዚያ በፊት "የአገር መሪነት ማን ይጠላል?" የሚል ቃል ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፤ የግንባሩ አባል ቢሆን የሆነ የአመራር ቦታ የሚከለክሉት አይመስለኝም። ሆኖም ከዚያ በፊት የነበረው የፖለቲካ ልምድ ግን የቅንጅት አመራሮችን በሽምግልና ሥም ይቅርታ ያስፈረመው የአገር ሽማግሌዎች አባልነት ብቻ ነበር።  ኃይሌ ገብረሥላሴን በመተቸት ለመጻፍ ስንጀምር "ኃይሌ ለአገር ውለታ የዋለ፣ ከአትሌቲክስ ጡረታ ቢወጣም በኢኮኖሚው መስክ ብዙ ሰው ለመቅጠር የበቁ ኢንቨስትመንቶች ላይ የተሠማራ" የሚሉ ማባበያዎችን ማስቀመጥ እንደ ደንብ ተቆጥሯል። እኔ ይህን አላደርግም። ለትችት የሚቀርቡት ሰዎች ስለአገር ምንም ውለታ ያልዋሉ ሰዎች ናቸው ማለት አይደለም። ሁሉም የአቅሙን አዋጥቷል። ኃይሌም ቢሆን በፍትሕ ዓይን ከማንም አይበልጥም። አሁ...

An African Portrayal of Adwa!

A few years ago, there was a movement by African media leaders to create an African narration of itself. The proposal aimed at reversing the racist or colonial perspective of Africa and telling African stories in African way. To understand this, I usually think of ways of things are done at home, Ethiopia. Let me give you an example from home. Foreign media or any reference of an Ethiopian is so strange until that Ethiopian learns about it. In my little experience of travel and even in reference of foreign media, I found myself usually referred as someone whom I am not. The wikipedia page that has my profile, for example, reads my story as Hailu's, my father. Jokes aside, foreigners usually referred to me by my father's name mostly, and by my grandfather's name seldom. They call it Sur Name or Family Name while we have no such thing. I want to be called in my own way, the cultural way I have lived. But no one cares because the standard is set in the European way.  ...

No Diplomacy, No Dependency!

I believe all changes must come from within Ethiopia. It is the people of Ethiopia who should have the chance to have the ultimate say to make decisions on its fate. However, realities on ground give foreign powers disproportionate opportunity to interfere in internal affairs; and often times they use it to consolidate powers of authoritarians. World conventions, pacts, partnership values and etc. are lip services to let the hopeless mass hope for a promise that will never be fulfilled, letting citizens settle down while diplomats continue empowering authoritarians to consolidate power through their support. In post election 2005, foreign powers supported EPRDF financially to rise up after a wave of public protests. Similarly, today too, foreign powers and most of their diplomats in Ethiopia are in favor of the status quo with EPRDF (which is dominated by TPLF) because of mainly the following reasons: 1. Fear of the Unknown Horn of Africa is capital of crises. Somalia is...