‘አክቲቪዝም’ በአማርኛ ቁርጥ ትርጉም አልተገኘለትም። እንዲሁ በየዐውዱ "የለውጥ አራማጅነት"፣ "የመብቶች አቀንቃኝነት"፣ ወዘተ… ነው የሚባለው። የእንግሊዝኛ ቃሉን ግርድፍ ትርጉም ከወሰድን "ንቁ ተሳታፊ" ከሚለው የሰፋ ትርጉም የለውም። በኢትዮጵያ ቃሉ በተደጋጋሚ መደመጥ የጀመረውና ራሳቸውን ‘አክቲቪስት’ ብለው የሚጠሩ ሰዎች የተከሰቱት ከማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ማደግ ጋር ተያይዞ ነው። በተለምዶ፣ ቃሉ በጥቅሉ ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚያደርጉ እና የሚወክሉት ድርጅት የሌላቸውን ግለሰቦች በሙሉ ለመግለጽ እየዋለ ነው። እዚህ ጽሑፍ ላይ የምጠቀምበት ገላጭ ሆኖ ያገኘሁትን "አራማጅነት" የሚለውን ቃል ነው። አራማጅነት ምንድን ነው? አራማጅነት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና/ወይም አካባቢያዊ ለውጦችን ለማምጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። አራማጅነት የአጭር ግዜ ፕሮጀክት ወይም ዘላቂ ንቅናቄ ሊሆን ይችላል። አንድ ጉዳይ ላይ ብቻ ያተኮረ ወይም ብዙ ጉዳዮችን ያቀፈም ሊሆን ይችላል። አራማጅነት በብዙኃኑ ተቀባይነት ያለውን አንድ ጉዳይ በመንግሥት ተቀባይነት እንዲያገኝ፤ ወይም በመንግሥት ዕውቅና ያለውን ጉዳይ በብዙኃኑም ተቀባይነት እንዲያገኝ፤ ወይም በብዙኃኑም፣ በመንግሥትም ተቀባይነት እና ዕውቅና የሌለውን ጉዳይ በሁለቱም ተቀባይነት እና ዕውቅና እንዲያገኝ ለማድረግ ሊሆን ይችላል። አራማጅነት በብዛት ከተገለሉ ሕዳጣን ወይም ከተጨቆኑ ብዙኃን መሐል በወጡ አራማጆች የሚደረግ የመብት/የጥበቃ ንቅናቄ ነው። የአራማጅነት ስኬት እንደመነሻው ነው የሚለካው። አንዳንዴ የተነሳውን ሐሳብ የተደራጁ ሲቪል ማኅበረሰቦች ወይም የፖለቲካ ማኅበሮች አጀንዳዬ ብለው ሲይዙት ከአራማጆች እጅ ሊወጣ ይችላል። ሌላ ግዜ ደ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.