መንግሥት ድህነትን ለመቅረፍ የሚያስችል መንገድ ካልዘረጋ ሰብኣዊ መብት እንደጣሰ መቆጠር አለበት፡፡
ዓለምአቀፉ የሰብኣዊ መብቶች ድንጋጌ (Universal Declaration of Human Rights) የመጀመሪያው አንቀጽ የመጀመሪያው ዓረፍተነገር ‹‹All human beings are born free and equal in dignity and rights (ሁሉም ሰዎች ነጻ እና በክብርና መብት ዕኩል ሆነው ይወለዳሉ)›› ይላል፡፡ በግል ሕይወቴ የድህነትን ያህል የሰውን ልጅ ክብር የሚያዋርድ ነገር አይቼ አላውቅም፡፡ አሁንም ድረስ፣ በዚህ 21ኛ በምንለው ክፍለዘመን ሰዎች በዘራቸው፣ በጾታቸው፣ በሃይማኖታዊ አመለካከታቸው እና ሌሎችም ክብራቸው ይዋረዳሉ፡፡ ነገር ግን የትኛውም ጉዳይ ሰዎች በድህነታቸው የሚዋረዱትን ያክል በግልጽ እየታየ አይደለም፡፡ በዛሬ ጊዜ ሆቴል በር ላይ በዘሩ፣ ሃይማኖቱ ወይም ጾታው ‹አትገባም› የሚባል ሰው የለም፤ በድህነቱ ግን ከበር የሚመለስ አለ፡፡ ሰዎች ምንም ይሁኑ ምን፣ ምንም ይመኑ ምን ድሃ ከሆኑ የሰው ንዑስ ተደርገው የመቆጠር ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡
ብዙ ምሁራን ‹ድህነት የሰብኣዊ መብት ጉዳይ አይደለም፤ ድህነትን መቅረፍም እንደየመንግሥታቱ አቅም የሚወሰን እንጂ ሊጠየቁበት የሚገባ ግዴታቸው አይደለም› ይላሉ፡፡ ምናልባትም ከዓለምአቀፍ ተቋማት መካከል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ብቻ ነው ‹ድህነት የሰብኣዊ መብት ጉዳይ ነው› እያለ በመከራከር ላይ ያለው፡፡ በሁለትዮሽ ክርክሮቹ መሐል ጥቂት ለመዋኘት ብሞክርም ድህነትን ከሰብኣዊ መብት ጉዳይ አሳንሼ እንዳየው ያሳመነኝ የለም፡፡
አዎ፣ ድህነት የማኅበራዊ ፍትሕ ጉዳይ ነው፤ የኢኮኖሚያዊ መብት ጉዳይ ነው፡፡ ግን የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰብኣዊ መብቶችም ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንዶች የድህነት መቀረፍ ለሰብኣዊ መብት መከበር መንገድ ይጠርጋል ብለው ያስባሉ፤ እኔ ግን ድህነትን መቅረፍ በራሱ አንድ ሰብኣዊ መብት ማክበር ነው ባይ ነኝ፡፡
ተፈጥሮ ለሰው ልጅ የሚበቃ ሀብት አላት፤ ይህንን ማብቃቃት የሚሳናቸውና ሰዎች በድህነት አረንቋ ውስጥ እንዲማቅቁ የሚያደርጉት ስርዓት አልበኞቹ ‹‹ስርዓት ለማስያዝ›› የሚሾሙ መንግሥታት ናቸው፡፡ ሕዝብን ከድህነት አረንቋ ውስጥ ማውጣት ግዴታቸው እንጂ ውለታቸው አይደለም፤ ምክንያቱም ከድህነት መውጣት (በፀጋ መኖር) የዜጎች ሰብኣዊ መብት ነው፡፡

Comments
Post a Comment