Skip to main content

#16Days: የቃላት ጥቃት ጠባሳው አይሽርም!



ሰዎችን ለማድነቅ የምንጠቀምበት ቃል ‹ወንድ› ወይም ‹ወንዳታ› በሆነበት ማኅበረሰባዊ አስተሳሰብ የምትደነቅ ሴት ማብቀል ይከብዳል፡፡ የምትደነቅ ሴት ብትበቅል እንኳ የማኅበረሰቡ ውጤት ነው ማለት አይቻልም ባይ ነኝ፤ የግል ጥረቷ ውጤት ነው የምትሆነው!

ቋንቋ፣ አባባሎች እንዲሁም ተረትና ምሳሌዎች ማኅበረሰቡ አባላቱን የሚያሳድግበትን (nurture የሚያደርግበትን) መንገድ ያሳብቃሉ፡፡ ያልዘራነውን አናጭድም፤ ስለዚህ አጋጣሚውን ተጠቅመን ከቃላት አጠቃቀማችን ጀምሮ ራሳችንን መገምገም መጀመር ሊኖርብን ነው፡፡

ለመሆኑ የአማርኛ ተረትና ምሳሌዎቻችን ስለሴት ምን ይላሉ?
  1. ሴት ሲበዛ ጎመን ጠነዛ
  2. ሴትና ዶሮ ዱር ከሄዱ ቤታቸውን ይክዳሉ
  3. ሴት ከወንድ፣ እህል ከሆድ
  4. ሴት ለቤት፣ ወፍጮ ለዱቄት
  5. ሴትና መሬት የማይችሉት የለም
  6. ሴት ማገዶ ሲቸግራት ምሰሶ ትነቅላለች
  7. ሴት በማጀት፣ ወንድ በችሎት
  8. ሴት በጳጳስ፣ ኳደሬ በንጉስ
  9. ሴት ብታውቅ፣ በወንድ ያልቅ
  10. ሴት ሲያፏጩላት፣ ያረሱላት ይመስላታል
  11. ሴት አማት የመረዘው፣ ኮሶ ያነዘዘው
  12. ሴት አግብተው ሴት ቢወልዱ፣ የት አለ ንግዱ
  13. ሴት ከጠላች፣ በቅሎ ከበላች አመል አወጣች
  14. ሴት ካልወለደች ቋንጣ አትጠብስም
  15. ሴት ያመነ ጉም የዘገነ
  16. ሴት ያመጣው ጠብ አይበርድም
  17. ሴት ይወዷል ማጀት ያንጎዳጉዷል
  18. ሴትና ቄስ ቀስ
  19. ሴትና በቅሎ እንደገሪዋ ነው
  20. ሴትና አህያ ዱላ ይወዳል
  21. ሴትና ድመት ወደ ሞቀበት
  22. ሴትና ድስት ወደ ማጀት
  23. ሴትና ዶሮ ሳያብድ አይውልም
  24. ሴትና ፈረስ እንደኩሬ ውሀ እያደር ማነስ
  25. ሴትና ፈረስ የሰጡትን ይቀምስ
  26. ነፍስ በፈጣሪዋ፣ ሴት ባሳዳሪዋ
  27. ወጭትና ሴት ሲከናነቡ ይሻላል
  28. ወንድ ልጅ ለፈረስ ሴት ልጅ ለበርኖስ
  29. የመንገድ ዳር እሸት ባል የሌላት ሴት
  30. ዝናብ ካልጣለ ሁሉ ቤት፣ እንግዳ ካልመጣ ሁሉ ሴት

ተረትና ምሳሌ፤ የእምነት-እውነት

ተረትና ምሳሌዎች እንደባሕላዊ እሴት ወይም ብልሐት (wisdom) የተለመደ ነው፡፡ በሙግት ለመርታት ብዙ ተረት መቻል በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህ ተረትና ምሳሌዎች፣ ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ የተገነቡት በተጠራቀመ የማኅበረሰብ የእምነት-እውነታ ላይ ነው፡፡ አሁን፣ አሁን ከከተማ እየተመናመኑ ቢሆንም በብዙኃኑ ገጠሬ እና ጥቂት በማይባሉ ከተሜዎችም ውስጥ ስር የሰደደ እምነት የተጣለባቸው አፍራሽ ተረቶች ናቸው፡፡ ደግነቱ፣ ተረት በተጠራቀመ ዕውቀት ተረትም፣ በተረት ይተካል፡፡

ለተረትና ምሳሌዎቻችን ትንሽ ጥብቅና ለመቆም ያክል፣ እጅግ በጣም ጥቂት ቢሆኑም በሴቶች ዙሪያ ገንቢ የሆኑ ተረትና ምሳሌዎችም አሉን፡፡ እንደምሳሌ ‹‹ሴትና ጭስ መውጫ አያጣም›› የሚለውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይህንኑ ይዘው ይመስለኛል ብዙዎች ‹‹ሴት አይደለሽ እንዴ መላ አምጪ እንጂ!›› የሚሉት፡፡ ተረትና ምሳሌዎች በጊዜ ብዛት በሰዎች ልቦና ውስጥ የእምነት-እውነት የመፍጠር አቅም አላቸው፡፡

ማርክ ትዌይን ‹The Awful German Language› ባሰኘው ጽሑፉ ‹‹በስርዓተ ጾታ ጉዳይ እንደጀርመኖች አዳላጭ ቃል የለም›› ይልና እንደምሳሌ በጀርመን ቋንቋ ዛፍ ወንድ ይሆንና ቅርንጫፎቹ ግን በሴት ይጠራሉ ይላል (ገጽ 16)፡፡ ማርክ ትዌይን ይህንን ያለው እኛን ስለማያውቀን ነው እንጂ አማርኛን ቢያውቅ ኖሮ ቢያንስ ለጀርመኖች ተፎካካሪ ያደርገን ነበር፡፡ በአማርኛችን ግዙፍ፣ ጠንካራ ነገሮች ጾታቸው ‹ወንድ› ነው፤ ትንናሽና እና ደካማ ግዑዝ ነገሮች ግን ‹አንቺ› እያልን ነው የምንጠራቸው፤ ምናልባት ከጀርመኖቹ የምንለየው ጾታ-አልባ ስያሜ ስለሌለን ብቻ ነው፡፡ ‹‹የአበበ ቤት ትልቅ ነው፣›› ወይም ‹‹የአበበ ቤት ትንሽ ነች፣›› እንላለን እንጂ አናገላብጠውም፡፡ እዚህጋ በተገላቢጦሽ ይባል፣ አይባል የሚል መውጫ የሌለው ሙግት ውስጥ መግባት አልፈልግም፡፡ ነገር ግን አባባሉ የተፈጠረው ከምን ዓይነት ማኅበራዊ እሳቤ ነው የሚለውን አውቀን እንግባበት ነው የምለው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

The "Corridor Development" is a Façade of the Prosperity Party

Befekadu Hailu I have seen a news report claiming that 40% of central Addis Ababa will be demolished for the corridor development; I am not able to confirm the validity of the news but it sounds real to me given the size of massive operations in the demolition of old neighborhoods and construction of bike lanes, green areas, and glittering street lights. I like to see some beauty added to my city but cannot help mourning the slow death of it too. Addis Ababa was already in a huge crisis of housing and the demolition of houses is exacerbating it. Apparently, Prime Minister Abiy Ahmed is eager to showcase his vision of prosperity by demonstrating how fast his administration can do magic by beautifying the front sides of the streets with lights, new pavements, and painted fences ("to fake it until he makes it" in my friend's words). Therefore, he and his party do not care about the miserable human stories behind the scenes and they will harass you if you tell it (Azeb Woku...

የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ

በፍቃዱ ዘ . ኃይሉ “የአዲስ አበባ ብሔርተኝነት” ቢኖር ኖሮ መሪው ልጅ ሚካኤል ይሆን ነበር። አሁን አሁን እሱ ስለ አዲስ አበባ የዘፈናቸውን ዘፈኖች ቁጥር ራሱ በትክክል መቁጠር ይቸግረኛል። ለአዲስ አበባ ከተዘፈኑ ዘፈኖቹ ውጪም በየዘፈኑ ውስጥ የሚጨማምራቸው መልዕክቶች በራሳቸው መወድሰ አዲስ አበባ ናቸው። ለምሳሌ፣ በቅርቡ በለቀቀው ‘አዲስ አራዳ’ በተሰኘው አልበሙ ውስጥ ‘የድሬ ልጅ’ የሚል ዘፈን አለው። ዘፈኑ የተዘጋጀው ያው የአዲስ አበባ እህት ተደርጋ የምትቆጠረውን ድሬ ዳዋን ለማወደስ ነበር። ልጅ ሚካኤል ግን የአዲስ አበባ ፍቅሩ ያመልጠውና የሚከተለውን ያቀነቅናል፦ “መጣልሽ በሏት፣ ድሬ ድረስ፣  ከአዱ ገነት፣ ከሸገር፣ ከአዲስ ደረሰ፣... የሸገር ልጅ አራዳ ነው፣ ሰው አክባሪ፣ ሰው ወዳዱ፣ ቀላጅና ተረበኛ፣ ፍቅር ይዞ የሚተኛ፣ ‘አለው’ የለ፣ ‘የለው’ የለ፣ ከሁሉ ጋ፣ ግባ ጀባ...፤” ፤ ልጅ ሚካኤል በዚህ አልበሙ ብቻ አዲስ አበባን የሚያውድሰባቸው ሌሎችም ዘፈኖች አሉ፤ ‘ አዲስ አራዳ ’ የሚለው የአልበሙ መጠሪያ እና ‘ሸገር’ የሚሉት ዘፈኖቹ ዋነኞቹ ናቸው። ታዲያ እንዲህ በአዲስ አበባ ፍቅር የሚቃጠለው ልጅ ሚካኤል "ሊነግረን የሚፈልገው ምንድን ነው?" የሚለው ጥያቄ ደጋግሞ ይመጣብኛል። ይህ የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ ምንነትን ለመረዳት የሚጥር ፖለቲካዊ መጣጥፍ ነው። ‘አዲሱ አራዳ’ ማነው? በዚህ ዘፈኑ በብዙዎቻችን ዕድሜ የትዝታ ማኅደር ውስጥ የሚገኙ ነገር ግን በአዲስ አበባ ልማት ሥም የፈረሱ እና እየተረሱ ያሉ ሰፈሮችን ሥም ያነሳሳል። ዘፈኑ በግጥሙም በዜማውም፣ የሐዘን እንጉርጉሮ ያለበት ነው። ምሳሌ እንውሰድ፦ “ጨርሰሽ ስትወጪ ከቡፌ ዳ’ላጋ፣ ጠብቂኝ እንዳልል፣ ቆመሽ መሐሙድ’ጋ፣ አገር ...

መጽሐፍ የሚወጣው፣ የተዋነይ ዘ ጎንጅ 5 መሥመር ቅኔ

ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል። “የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።” (ተዋነይ ዘ ጎንጅ። ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ) ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን ...