በበፍቃዱ ኃይሉ ሰሞኑ ‹‹የሕገ-መንግሥቱ›› ይከበር የበይነመረብ ዘመቻ 2ኛ ዙር በአንቀጽ 29 (ሐሳብንና አመለካከትን የመያዝና የመግለጽ መብት) ይከበር ዙሪያ በዞን ዘጠኝ አስተባባሪነት እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ለዘመቻው ግብአት እንዲሆኑ አንዳንድ እውነታዎችን ስለሕገመንግሥቱ እና ስለቀደሙት፣ ስለአተገባበሩም ጭምር እነሆ፡- ሐምሌ 30/1966 በንጉሡ ነገሥት መንግሥት ረቂቅ ሕገ-መንግሥት፡- አንቀጽ 25/1 ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሐሳብ ነፃነት አለው፡፡ ማናቸውንም ሐሳብ በንግግር፣ በጽሑፍ ወይም በሌላ ዘዴ የመግለጽና የማሰራጨት እንዲሁም ሌሎች የገለጹትን የማወቅ መብት አለው፡፡ አንቀጽ 25/2 ማንኛውም ሰው በቴሌፎን፣ በቴሌግራፍ፣ በፖስታ ወይም በማናቸውም ሌላ የመገናኛ ዘዴ ሚስጢሩ እንደተጠበቀ የመነጋገርና የመላላክ መብት አለው፡፡
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.