Skip to main content

#Ethiopia, #StopCensorship: ሐሳብን በነጻ መግለጽ በኢትዮጵያ - ሕገ መንግሥት ላይ እና በተግባር



በበፍቃዱ ኃይሉ

ሰሞኑ ‹‹የሕገ-መንግሥቱ›› ይከበር የበይነመረብ ዘመቻ 2ኛ ዙር በአንቀጽ 29 (ሐሳብንና አመለካከትን የመያዝና የመግለጽ መብት) ይከበር ዙሪያ በዞን ዘጠኝ አስተባባሪነት እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ለዘመቻው ግብአት እንዲሆኑ አንዳንድ እውነታዎችን ስለሕገመንግሥቱ እና ስለቀደሙት፣ ስለአተገባበሩም ጭምር እነሆ፡-

ሐምሌ 30/1966 በንጉሡ ነገሥት መንግሥት ረቂቅ ሕገ-መንግሥት፡-

አንቀጽ 25/1

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሐሳብ ነፃነት አለው፡፡ ማናቸውንም ሐሳብ በንግግር፣ በጽሑፍ ወይም በሌላ ዘዴ የመግለጽና የማሰራጨት እንዲሁም ሌሎች የገለጹትን የማወቅ መብት አለው፡፡

አንቀጽ 25/2

ማንኛውም ሰው በቴሌፎን፣ በቴሌግራፍ፣ በፖስታ ወይም በማናቸውም ሌላ የመገናኛ ዘዴ ሚስጢሩ እንደተጠበቀ የመነጋገርና የመላላክ መብት አለው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መስከረም 1/1980 ያወጣው ሕገ-መንግሥት፡-

አንቀጽ 47/1

የኢትዮጵያውያን የንግግር፣ የጽሑፍ፣ የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ የማድረግና በማኅበር የመደራጀት ነጻነት የተረጋገጠ ነው፡፡

አንቀጽ 47/2

መንግሥት ለነዚህ ነጻነቶች ተግባራዊ መሆን አስፈላጊውን ቁሳዊና ሞራላዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት (ሕዳር 29/1987)፡-

አንቀጽ 29

የአመለካከት እና ሐሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ መብት

1.       ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል፡፡

2.      ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፡፡ ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን የካትታል፡፡

3.      የኘሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን፣ እንዲሁም የሥነ ጥበብ ፈጠራ ነጻነት ተረጋግጧል፡፡ የኘሬስ ነጻነት በተለይ የሚከተሉትን መብቶች ያጠኝልላል፣

/ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን፣

/ የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን፡፡

በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ እንደተመለከተው ንጉሡም ሆኑ ደርግ ሙሉ ሐሳብን የመግለጽ መብት መውጫቸው/መውደቂያቸው ሰዓት ላይ ለመስጠት ሞክረዋል/ሰጥተዋል፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት የሽግግር መንግሥቱ ሕገ-መንግሥት ላይ የብሔሮች መብት እስከመገንጠልን ያሰፈረ ቢሆንም ስለሐሳብ ነጻነት የሚናገረው የለም፡፡ በ1987ቱ ሕገ-መንግሥት ግን የተሻለ የሚባል የሐሳብ ነጻነትን ፈቅዷል፡፡ ከሌሎቹ መንግሥታቶች እርምጃም የሚለየው የፕሬስ ሕጉ ወጥቶ በተግባር ላይ የሚውልበት መንገድ መመቻቸቱ ነው፡፡ ሆኖም ሁሉም ነገሮች ባሉበት አልቀጠለም፡፡ የተሻሻለው የፕሬስ አዋጅ፣ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅና ሌሎችም መልሰው የመብቱን ወሰን አጥብበውታል፡፡ ነገር ግን አሁን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ገደብ የሚከናወነው በአስተዳደራዊ አፈና ነው፡፡

ከ1983 ወዲህ ያሉ እውነታዎች፡-

1.   የመጀመሪያው ነጻ ጋዜጣ ‹‹ዕይታ›› ይባላል፤ የፕሬስ አዋጁ ከመውጣቱ በታኅሳስ ወር 1984 መታተም ጀምሯል፡፡ የቅጁ ብዛት ከ50,000 እስከ 70,000 ይደርስ ነበር፡፡ በወቅቱ በርካታ ‹‹የስም ማጥፋት›› ክሶችን በመንግሥት አስተናግዷል፡፡ በመጨረሻም የቅጂ ብዛቱ ወደ 5,000 ደርሶ በጥቅምት ወር 1986 ሕትመቱ ተቋርጧል፡፡ (ቅድመ ምርጫ 97 አካባቢ ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦች እትም እስከ 1050,000 ድረስ ከፍ ብሎ የነበረ ቢሆንም ከዚያ በኋላ እያሽቆለቆለ መጥቶ በ2004 መጨረሻ ላይ ሕትመቱ የተቋረጠው እና የወቅቱን እጅግ ከፍተኛ ቅጂ ያሳትም የነበረው ነጻ ጋዜጣ ፍትሕ ነበር፡፡ ፍትሕ የታገደበትን የመጨረሻ እትሙን በ30,000 ቅጂ ነበር ለብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ያዘዘው፡፡ በጥር ወር ስርጭት ላይ ከዋሉ ጋዜጦችን ያስመዘገበው የሪፖርተር እሁድ እትም ሲሆን እሱም 11,000 ነው /የብሮድካስት መረጃ/)

2.   እስከ ሐምሌ 1989 ብቻ 265 ጋዜጦች እና 120 መጽሔቶች ሕጋዊ ፈቃድ ወስደዋል፡፡ …… (በጥር ወር ለስርጭት የበቁት 12 የፖለቲካ ጋዜጦች፣ 6 የስፖርት እና 1 የጤናና ስነልቦና ጋዜጦች እና 21 መጽሔቶች ናቸው፡፡)

3.   በሕግ ባይከለከልም በኢትዮጵያ ለአንድም የግል ተቋም የቴሌቪዥን አገልግሎት አልተፈቀደም፡፡ ብቸኛው የግል አገር አቀፍ ሬዲዮ ስርጭት የፋና ሬዲዮ ሲሆን ሬዲዮ ፋና ንብረትነቱ የሕወሓት/ኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ነው፡፡ ሬዲዮ ፋና በተለያዩ ከተሞች ኤፍ ኤም ስርጭቶችን በማሰራጨት፣ የራሱን ሕንፃ በማስገንባት ወደኮርፖሬትነት ለማደግ የቻለ የመጀመሪያው እና ብቸኛው ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ሸገር እና ዛሚ ኤፍ ኤሞች ሌሎች ‹‹በገለልተኛ›› የተያዙ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ሲሆኑ፤ የሸገር ትኩረት ማኅበራዊ ጉዳዮች ሲሆኑ፣ የዛሚ ትኩረት ደግሞ የመንግሥትን ፖሊሲ ማበረታታት እና ማሞካሸት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በኢትዮጵያ መቀመጫውን ያደረገ (.et ኤክስቴንሽን ያለው/ዋና ቢሮው እዚህ የሆነ) በድረገጽ ላይ የሚሠራ አንድም የዜና አውታር የለም፡፡

Comments

Popular posts from this blog

The "Corridor Development" is a Façade of the Prosperity Party

Befekadu Hailu I have seen a news report claiming that 40% of central Addis Ababa will be demolished for the corridor development; I am not able to confirm the validity of the news but it sounds real to me given the size of massive operations in the demolition of old neighborhoods and construction of bike lanes, green areas, and glittering street lights. I like to see some beauty added to my city but cannot help mourning the slow death of it too. Addis Ababa was already in a huge crisis of housing and the demolition of houses is exacerbating it. Apparently, Prime Minister Abiy Ahmed is eager to showcase his vision of prosperity by demonstrating how fast his administration can do magic by beautifying the front sides of the streets with lights, new pavements, and painted fences ("to fake it until he makes it" in my friend's words). Therefore, he and his party do not care about the miserable human stories behind the scenes and they will harass you if you tell it (Azeb Woku...

መጽሐፍ የሚወጣው፣ የተዋነይ ዘ ጎንጅ 5 መሥመር ቅኔ

ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል። “የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።” (ተዋነይ ዘ ጎንጅ። ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ) ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን ...

የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ

በፍቃዱ ዘ . ኃይሉ “የአዲስ አበባ ብሔርተኝነት” ቢኖር ኖሮ መሪው ልጅ ሚካኤል ይሆን ነበር። አሁን አሁን እሱ ስለ አዲስ አበባ የዘፈናቸውን ዘፈኖች ቁጥር ራሱ በትክክል መቁጠር ይቸግረኛል። ለአዲስ አበባ ከተዘፈኑ ዘፈኖቹ ውጪም በየዘፈኑ ውስጥ የሚጨማምራቸው መልዕክቶች በራሳቸው መወድሰ አዲስ አበባ ናቸው። ለምሳሌ፣ በቅርቡ በለቀቀው ‘አዲስ አራዳ’ በተሰኘው አልበሙ ውስጥ ‘የድሬ ልጅ’ የሚል ዘፈን አለው። ዘፈኑ የተዘጋጀው ያው የአዲስ አበባ እህት ተደርጋ የምትቆጠረውን ድሬ ዳዋን ለማወደስ ነበር። ልጅ ሚካኤል ግን የአዲስ አበባ ፍቅሩ ያመልጠውና የሚከተለውን ያቀነቅናል፦ “መጣልሽ በሏት፣ ድሬ ድረስ፣  ከአዱ ገነት፣ ከሸገር፣ ከአዲስ ደረሰ፣... የሸገር ልጅ አራዳ ነው፣ ሰው አክባሪ፣ ሰው ወዳዱ፣ ቀላጅና ተረበኛ፣ ፍቅር ይዞ የሚተኛ፣ ‘አለው’ የለ፣ ‘የለው’ የለ፣ ከሁሉ ጋ፣ ግባ ጀባ...፤” ፤ ልጅ ሚካኤል በዚህ አልበሙ ብቻ አዲስ አበባን የሚያውድሰባቸው ሌሎችም ዘፈኖች አሉ፤ ‘ አዲስ አራዳ ’ የሚለው የአልበሙ መጠሪያ እና ‘ሸገር’ የሚሉት ዘፈኖቹ ዋነኞቹ ናቸው። ታዲያ እንዲህ በአዲስ አበባ ፍቅር የሚቃጠለው ልጅ ሚካኤል "ሊነግረን የሚፈልገው ምንድን ነው?" የሚለው ጥያቄ ደጋግሞ ይመጣብኛል። ይህ የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ ምንነትን ለመረዳት የሚጥር ፖለቲካዊ መጣጥፍ ነው። ‘አዲሱ አራዳ’ ማነው? በዚህ ዘፈኑ በብዙዎቻችን ዕድሜ የትዝታ ማኅደር ውስጥ የሚገኙ ነገር ግን በአዲስ አበባ ልማት ሥም የፈረሱ እና እየተረሱ ያሉ ሰፈሮችን ሥም ያነሳሳል። ዘፈኑ በግጥሙም በዜማውም፣ የሐዘን እንጉርጉሮ ያለበት ነው። ምሳሌ እንውሰድ፦ “ጨርሰሽ ስትወጪ ከቡፌ ዳ’ላጋ፣ ጠብቂኝ እንዳልል፣ ቆመሽ መሐሙድ’ጋ፣ አገር ...