መጀመሪያ ጭብጨባ አንድነት ፓርቲ በቅርቡ ተቃዋሚዎች/የተቃዋሚ ደጋፊዎች በቂ የመረጃ ምንጭ የላቸውም በማለት በየሣምንቱ ማክሰኞ፣ በ5 ብር ገበያ ላይ የምትውል ‹‹ፍኖተ ነፃነት ›› የተሰኘች ጋዜጣ ማሳተም ጀምሯል፡፡ አንዱአለም አራጌ ሲናገር እንደሰማሁት ‹‹በጋዜጣዋ ላይ የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላትም ቢሆኑ መጻፍ ይፈቀድላቸዋል፤ አንድነት እንደ ኢሕአዴግ የመናገር ነፃነትን የማፈን ፍላጎት የለውም፡፡›› ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲው በየሣምንቱ እሁድ ማለዳ በተጋባዥ ምሁራን ጽሁፍ አቅራቢነትና በተሳታፊዎች መካከል የሚካሔድ የውይይት ፕሮግራም ጀምሮ ነበር፡፡ (የእነ አቶ አንዱአለም በ‹‹አሸባሪነት›› ተጠርጥሮ መታሰር ይህንን ጠቃሚ ልምድ እስከወዲያኛው ያስቀረው ይሆን?) በሌላ በኩል ( የኔ favorite ባይሆንም እንኳን) ኢዴፓ የዓለም ሊበራል ፓርቲዎችን ጉባኤ በ2004ዓ.ም. በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያካሒድ ጎንበስ ቀና እያለ መሆኑ የሚያስመሰግን ነው፡፡ እንዲህ ሰበብ እየፈለግን የምናቆለጳጵሳቸው ተቃዋሚዎች ግን በደመስማሳው ስንመለከታቸው መንግስት አንድ ውሳኔ ባሳለፈ ቁጥር የፕሮፓጋንዳ መግለጫ ከመስጠት ባሻገር (ያውም ከሰጡ) ባለፈው ምርጫ ካየናቸው በኋላ የት እንደገቡ ጠፍተዋል፡፡
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.