Skip to main content

Posts

Showing posts from January, 2021

US and the Social Media, Lessons for Ethiopia

( Click here to read in Amharic.) Freedom of expression is a non-negotiable matter for the Americans. It is something they needed to do “the first amendment” of their constitution for. The first amendment states that "Congress shall make no law… abridging the freedom of speech, or of the press…". On January 6, 2021, Facebook and Twitter had suspended President Trump’s profiles for a day after his supporters forcefully raided Capitol Hill while Congress is at a meeting. While Americans are shocked by the incident, the social media corporations have been the ones that have denied a platform for the president who was accused by many of passing inciting messages.  The Americans have not seen such a scandal for more than two hundred years since 1814 when British troops attacked Capitol Hill. It would not be an exaggeration to say that the social media conspiracy theories and misinformation campaigns have resulted in this chaos. In this note, I will briefly explore the necessity...

አሜሪካ እና ማኅበራዊ ሚዲያ

ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ጉዳይ አሜሪካውያን የማይደራደሩበት ጉዳይ ነው። ሕገ መንግሥታቸውን መጀመሪያ ያሻሻሉትም በዚሁ ጉዳይ ነው። "ፈርስት አሜንድመንት" (አንደኛው ማሻሻያ) "ኮንግረስ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነትን የሚገድብ ሕግ ማውጣት አይችልም" ይላል። ዛሬ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በአሜሪካውያኑ ኩባንያዎች ፌስቡክ እና ትዊተር ታግደዋል። አሜሪካውያንም ደንግጠዋል።   ካፒቶል ሒል የሚሉት የፌዴራል መንግሥቱ ሕግ አውጪ (ኮንግረስ) በነውጠኞች የሰው መንጋ ተደፍሯል። አሜሪካውያኑ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እንዲህ ዓይነት ቅሌት አይተው አያውቁም። ለዚህ የዳረጋቸው ማኅበራዊ ሚዲያ ያገነነው የሴራ ትንተና እና የተዛባ መረጃ ልቅ ፍሰት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በዚህ ድንገቴ መጣጥፍ የሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ፋይዳ፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ጦስ እና የነውጥ መከላከል ጉዳይን በጨረፍታ እዳስሳለሁ።  የንግግር ነጻነት ለምን?  ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መከበር አለበት የምንለው ለአራት ወይም አምስት ዐቢይ ምክንያቶች ነው። 1ኛ) ተፈጥሯዊ ፍላጎት ስለሆነ፣ 2ኛ) እውነቱን በነጻነት ሳይነጋገሩ መረዳት ስለማይቻል፣ 3ኛ) የግለሰቦችን የውሳኔ ሰጪነት አቅም ለማሳደግ፣ 4ኛ) አፈና የሚያስከትለውን ነውጥ ለማስቀረት፣ እና በቀደሙት ውስጥ ሊካተት ቢችልም፣ 5ኛ) ለሌሎች መብቶች መከበር አስፈላጊ ስለሆነ ነው።  አመፅ ቀስቃሽ ንግግሮች እና የተዛቡ መረጃዎች ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መከበር አለበት የሚያስብሉ ምክንያቶችን ይቃረናሉ። ለዚህ ነው ዓለም ዐቀፍ ሥምምነቶች ሐሳብን የመግለጽ ነጻነቶች ስለሚገደቡባቸው ረገዶች (የጦርነት እና አመፅ ቅስቀሳ፣ የዘር ጥላቻ፣ ወዘተ…) እንዲሁም መርሖዎች (ሕጋዊነት፣ ቅቡልነት፣ አስፈላጊነት ላለው ዓላማ) ጥንቃቄ የ...