Skip to main content

Posts

Showing posts from June, 2020

What's Next for TPLF?

TPLF's decision to hold an election in time came a little too late. No one expects that the National Election Board of Ethiopia (NEBE), whose accountability is to the House of People's Representative (HPR), will help them run the election.  House of People's Federation (HoF) has already decided it is the HoPR that will blow the last whistle to decide when the next general and regional election should run (well, after the health institutions announced that COVID is no more a threat.)  Can Tigray Run its Own Election in Time? If TPLF is really committed to doing the election, the first thing to do is to establish an independent electoral commission. This needs a fair time. A law establishes the commission must be drafted and approved by the regional council, the institution needs to have space, people, and structure in due time. Then, it should register political parties that function in the region. Then, introduce the election schedule - which includes voters’ r...

የብሔር ጥያቄ እና የብሔር ሽቀላ

በኢትዮጵያ ውስጥ መልስ የሚሹ በርካታ የማንነት ጥያቄዎች አሉ፤ ከጥያቄዎቹ መካከል ግን ነጥሮ የወጣው ወይም እንዲወጣ የተደረገው “የብሔር ጥያቄ” ብቻ ነው። ይህ መሆኑ በነባሮቹ ታሪካዊና ማኅበራዊ ጥያቄዎች ላይ ተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ቁርሾዎች እና ቅራኔዎች እንዲደራረቡና ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች እየተባባሱ እንዲሔዱ አድርጓል። የብሔር ጥያቄ አቀንቃኞች ብሔርተኝነትን እንደ ብቸኛ መፍትሔ ያቀርባሉ። ይህ ዓይነቱ አቀራረብ ችግርን በችግር የመፍታት ዘዴ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት ዘለግ ያለ ዕድሜ ያላቸው የማንነት ጥያቄዎች መልሱ ብሔርተኝነት ሳይሆን ፍትሕ ነው። በዚህ መከራከሪያ ላይ በቅጡ ለመግባባት የኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄዎችን መሠረት፣ የብሔር ጥያቄ በማንነት ጥያቄዎች ውስጥ ያለውን ቦታ፣ እንዲሁም ችግሮቹን ከዚህ በፊት ለመፍታት የተሔደባቸው ዘዴዎች ለብልጣ ብልጦች የፈጠሩትን የማይገባቸው እርከን ላይ የመንጠላጠል ዕድል አፍታትቶ መነጋገር ያስፈልጋል። የማንነት ጥያቄ ነባራዊነት ረዥሙ የዐፄ ስርዓት በአንድ በኩል በአንድ ድንበር የታጠረ የፖለቲካ ማኅበረሰብ አበርክቶ ሲያልፍ፣ በሌላ በኩል ብዙ መልስ የሚያሻቸው ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን ለተከታታይ ትውልዶች ጥሎ አልፏል። የደርግ ወታደራዊ ጭቆና እና የትሕነግ (TPLF) የዘውግ ምደባ ዐፄያዊው ስርዓት ጥሎት በሔደው ሸክም ላይ ሲደመሩበት ጥያቄውን ከወትሮው የበለጠ ውስብስብ አድርገውታል። የኢትዮጵያ ዐፄዎች አገር ንብረቱን በሙሉ የግላቸው አድርገው ነበር የሚቆጥሩት። ይህ ግዙፍ የመደብ ልዩነት ፈጥሯል። የመደብ ልዩነቱ በገዢዎች እና ተገዢዎች ዘንድ ሰፊ የሀብት እና የማኅበራዊ ማዕረግ ክፍተት ጥሎ አልፏል። የመደብ ልዩነቱን ለማስፋት መሬት ትልቁን ሚና ተጫውቷል። የመሬት ባለ...

የትግራይ ክልል ምርጫ፤ ስለ ዴሞክራሲ ወይስ አልሞት ባይ ተጋዳይነት?

የትግራይ ክልል ብሔራዊ ምክር ቤት ምርጫውን ከጳጉሜ በፊት ለማካሔድ ዛሬ ሰኔ 5፣ 2012 ወሰነ። የዚህ ውሳኔ አዝማሚያ ወዴት ነው? ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከብልፅግና ጋር ያለው ፀብ የትግራይ ክልል ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ፀብ ተደርጎ መቆጠር ከተጀመረ ውሎ አድሯል። በሕወሓት ደጋፊነታቸው የሚታወቁ አክቲቪስቶች ኢትዮጵያን “ጎረቤት አገር” እያሉ የሚጠሩበት ጊዜ አለ። ሕወሓትም ክልሉን እንደ ነጻ አገር በመቁጠር የሚያደርጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ። በክልሉ መንግሥት እና በፌዴራሉ መንግሥት መካከል የነበረው ኩርፊያ ወደለየለት ፀብ የተሸጋገረው ብልፅግና ከተመሠረተ በኋላ ቢሆንም ቅሉ፥ ፀቡ እየተባባሰ መታየት የጀመረው ደግሞ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳው ከተሰረዘ በኋላ ነው። ሕወሓት በክልሌ ምርጫ በጊዜው አካሔዳለሁ ማለቱ ውዝግቡን እስካሁን ያልደረሰበት ቁንጮ ላይ ያደርሰዋል። በተለይም ደግሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ሁሉንም ክልሎች የሚመለከት ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ይህ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ውሳኔ መምጣቱ፣ ጉዳዩን ከድጡ ወደ ማጡ ይሰደዋል። ትግራይ በሌላ አነጋገር ራሷን እንደ ሉዓላዊ አገር እየተመለከት ያስመስላታል። ሕወሓት፤ የገዛ ‘ትሩፋቱ’ ሰለባ ሕወሓት በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መዋቅር ዝርጋታ ላይ ዐቢይ ተዋናይ ነው። ሕገ መንግሥቱ፣ የፌዴሬሽኑ አወቃቀር፣ የምክር ቤቶቹ አደረጃጀት እና ሥልጣን በዋነኝነት የተወጠኑት በሕወሓት ነው። ሕወሓትም እንከን አልባ መንግሥታዊ መዋቅር እንደሆነ ይናገር ነበር፤ ነገር ግን ድንገት ከፌዴራሉ መንግሥት ገዢ ፓርቲነት ተገልሎ የክልል ገዢ መንግሥት እና የፌዴራሉ መንግሥት ተቃዋሚ ሲሆን፥ በፊት እንከን አልባ መስለው ይታዩት የነበሩት ስርዓቶች እና አሠራሮች በሙሉ ተቃዋሚ ሆኗል። ይህ ነው ሕወሓትን የገዛ...