#EthioElection2020: What to Expect When You're Expecting Ethiopian Election! ወቅቱን የጠበቀ፣ ፉክክር ያለበት፣ ነጻ እና ርትዓዊ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ ጎጆ ውስጥ የመሐል ዋልታ ነው። ይሁን እንጂ ዴሞክራሲ ማለት በየአራት፣ አምስት ዓመቱ የሚመጣ ምርጫ ብቻ አይደለም፤ በኹለት ምርጫዎች መካከል ያለ የዜጎች ተሳትፎም የሚረጋገጥበት ስርዓት ነው። ለዚህ ነው ዴሞክራሲ መንገድ እንጂ መዳረሻ አይደለም የሚባለው። ነገር ግን በምርጫ መካከል የዜጎች ተሳትፎ (በተለይም በነጻ ሚዲያ እና ሲቪል ድርጅቶች አማካይነት የሚደረግ የዜጎች ተሳትፎ) የሌለው ዴሞክራሲ የይስሙላ ዴሞክራሲ ነው። ወቅቱን የጠበቀ (periodic) ምርጫ የሌለው ዴሞክራሲ ግን ከናካቴው የይስሙላ ዴሞክራሲ እንኳን ሊባል አይችልም። ለዚህ ነው ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ አዋጭ ስርዓት ነው ብለን የምናምን ሰዎች፥ በጥቅሉ ምርጫን፣ በተለይ ደግሞ የዘንድሮውን የኢትዮጵያን ምርጫ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና የወል ትብብር መከታተልና ማድረግ የሚኖርብን። ባለፉት ኹለት ዓመታት የዛሬ 15 ዓመት ገደማ ወዲህ የተዘጋውን የፖለቲካ ምኅዳር ለመክፈት ከበፊቱ የተሻለ ተነሳሽነት ታይቷል። የሲቪክ እና የፖለቲካ ምኅዳሩን ያጠበቡትን ሕጋዊ ማዕቀቦችን ለማሻሻል ጥሩ የሚባል ጥረት ተደርጓል። የመንግሥት ተቋማትን ተአማኒ እና "ነጻ" ለማድረግ ቃል ተገብቷል፣ ጥቂት የተቋማት ጥገናዊ ለውጥም ተደርጓል። ይኼ ሁሉ የተሐድሶ ሙከራ ግን በፉክክር በደመቀ፣ ነጻ እና ርትዓዊ ምርጫ ካልታጀበ "እቃቃው ፈረሰ፣ ዳቦው ተቆረሰ" መሆኑ ነው። First Things First ምርጫ ቦርድ ይታመናል? ይኼንን ጥያቄ ለመመለስ ነገሩን ከበርካታ አቅጣጫዎች መመ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.