በፍቃዱ ኃይሉ ሰሞኑን "የኦሮሚያ ቤተ ክሕነት አደራጅ ኮሚቴ" ያነሳው ጥያቄ የውዝግብ መንስዔ ሆኗል። ጉዳዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ስለሆነም፣ ምናልባት ደግሞ ለከፍተኛ ግጭት መንስዔ ሊሆን ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ይህንን መጣጥፍ የምጽፈውም፣ ከዚህ በፊት ስለማውቃቸው መሰል ውዝግቦች እና ድርድሮች የማውቀውን (የማስታውሰውን ያክል) ለማካፈል ነው። በስተመጨረሻ በወቅታዊው ውዝግብ ውስጥ የዴሞክራሲ እና የመብት ተሟጋቾች ጉዳዩን እንዴት መመልከት አለባቸው የሚለው ላይ የራሴን ነጥብ አስቀምጣለሁ። ይህንን የምጽፍበት ምክንያት የጥያቄውን ምንነት፣ የአቀራረቡን ሁኔታ፣ የቤተ ክርስቲያኗን አቋም እና የምዕመኑን ፍላጎት ከግምት ውስጥ ማስገባት ለመብት ተቆርቋሪዎች ወሳኝ ጉዳይ ስለሆነ ነው። በዚህ ጽሑፍ መሠረታዊ የሒደቱ መገምገሚያ መሥፈርቶቻችን 1ኛ፣ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ መግባት የለበትም፤ 2ኛ፣ ሃይማኖት በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለበትም፤ 3ኛ፣ በውዝግቡ ግጭት እንዳይነሳ እና ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መንግሥት የመከላከል ኀላፊነት እና ተወዛጋቢ አካላትም ይህንን የማስወገድ ግዴታ ያለባቸው መሆኑ ነው። የራስ ገዝ አስተዳደር ጥያቄ ጉዳይ ያደግኩበት ሰፈር “ራስ ካሣ ሰፈር” ይባላል። የራስ ካሣ መኖሪያ ጊቢ ፊት ለፊት አንቀፀ ምኅረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አለ። ቤተ ክርስቲያኑ “ጭቁኑ ሚካኤል” በሚል ሥም ነው የሚታወቀው። ይህንን ሥያሜ ያገኘው ከቤተ ክሕነት ጋር በነበረው ውዝግብ ነው። በወቅቱ እዚያው እኛ ሰፈር የሚገኘው የገነተ እየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሥር ነበር ሚካኤል ቤተ ክርስትያንም የሚተዳደረው። እናም ባንድ ወቅት የሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች (ቀሳውስቱ እና ዲያቆናቱ) በገነተ ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.