Skip to main content

Posts

Showing posts from January, 2019

ስድስቱ የኅትመት ብዙኃን መገናኛዎቻችን ፈተናዎች

በኢትዮጵያ የጋዜጦች እና መጽሔቶች አማራጭ አልባነት ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክሪያሲያዊ ስርዓት እንድትሸጋገር በማገዝ ረገድም ይሁን የነቁ እና መረጃ ያላቸው  ዜጎችን በመፍጠር ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዳይጫወቱ  አድርጓል። ጎረቤቶቻችን እነ ኬንያ ከኛ ግማሽ በታች የሕዝብ ብዛት ኖሯቸው ከእኛ እጥፍ ድርብ የበዙ ጋዜጦችና መጽሔቶች በየቀኑ ለስርጭት እና ለንባብ ይበቃሉ። እኛስ ምንድነ ነው ችግራችን? (የሚከተሉት ከልምድ የታዘብኳቸው ፈተናዎች ናቸው፤ አንባቢ ላለማሰልቸት ባጭር ባጭሩ ነው የምጠቅሳቸው።) ፩ኛ፣ የንባብ ባሕል ደካማነት ኢትዮጵያውያን የራሳችን ፊደል ያለን ሕዝቦች ነን እንበል እንጂ አንባቢ ሕዝቦች አይደለንም። የተማሩ ሰዎች ቁጥር ማነስ ብቻ ሳይሆን፣ ፊደል የቆጠሩትም የአንባቢነት ልምድ የላቸውም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ብዙ ጊዜ ጋዜጦቹ እና መጽሔቶቹ የሚነበብ ብዙም አዲስ ነገር የላቸውም ቢባልም፣ እውነቱ ግን የሚነበብ ነገር ይዘው የሚመጡትም ቢሆኑ በቅጡ እየተነበቡ አለመሆናቸው ነው። ጋዜጣና መጽሔት አንባቢዎች ጥቂት ጡረተኞችና የፖለቲካ ወይም የዝነኛ ሰዎች ወሬ ፈላጊዎች ብቻ ናቸው። ስለዚህ የንባብ ባሕል አለመኖሩ የኅትመት ብዙኃን መገናኛውን ከሚያዳክሙት ፈተናዎች ቀዳሚው ነው።  ፪ኛ፣ የሕግ እና አፈፃፀም አፋኝነት ከብሮድካስት ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ እስከ ብዙኃን መገናኛ ነጻነት እና የመረጃ ማግኘት መብት አዋጅ፣ እንዲሁም የሳይበር እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጆች በአንድም በሌላም መንገድ የኅትመት ብዙኃን መገናኛዎችን አዳክመዋል። እነዚህ አዋጆች የተፈጥሮ ነጻነትን እና ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን ከመገደባቸውም ባሻገር የፍርሐት ድባብ በመፍጠር ነጻ ውይይትን፣ ነጻ ሪፖርትን እና ነጻ ምርመራን የ...