ዝዋይ ሐይቅ፣ በተለምዶ ዝዋይ በምትባለው ባቱ ከተማ ዳርቻ ላይ፣ በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ፣ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 100 ማይሎች ርቆ የሚገኝ፣ 440 ስኵዌር ኪሎ ሜትር የሚሰፋ፣ ብዙም የማይወራለት፣ ብዙም ያልለማ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ፋይዳው የላቀ፣ ትልቅ ሐይቅ ነው። ሐይቁ 5 ደሴቶች አሉት። በደሴቶቹ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስር የሚተዳደሩ የተለያዩ ቤተ ክርስቲያኖች አሉ፤ የታቦታቱ ቁጥር 44 ነው ይባላል። በቱሉ ጉዶ ደሴት ላይ ባለችው የማርያም ቤተ ክርስትያን ጊቢ ውስጥ አንድ ሙዚዬም አለ። ሙዚዬሙ ውስጥ 'መጽሐፈ ሔኖክ' የሚባለው ዝነኛ መጽሐፍ አለ አሉ። ሔኖክ በመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች የኖህ ቅድመ አያት ነው ተብሎ ይታመናል። የአዳም ስድስተኛ የልጅ ልጁም ነው። ሔኖክ ከእግዜር ጋር በምድር ላይ ተንሸራሽሮ የጻፈው የጉዞ ማስታወሻ ነው 'መጽሐፈ ሔኖክ'። መጽሐፉ መጽሐፍ ቅዱስ ጥራዝ ውስጥ ባይካተትም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤት በጣም ይከበራል። በዓለም ዙሪያም ታሪካዊ ፋይዳው ትልቅ ነው። የመጽሐፈ ሔኖክ ምዕራፎች ከፊሎቹ 300 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ከፊሎቹ ደግሞ 100 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በኋላ የተዘጋጁ እንደሆነ በታሪክ ተመራማሪዎች ይታመናል። የመጽሐፈ ሔኖክ ታሪክ ሲወሳ መጀመሪያ (የኛ ከሆነው የግዕዙ መጽሐፍ በፊት) ፍልስጤም ውስጥ በእብራይስጥ እና በአርማይክ ቋንቋ ከተጻፈ በኋላ 800 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የገባበት ጠፍቶ ነበር። ከዛ ምንም እንኳ ከፊል የላቲን ትርጉሙ በአውሮጳ ቢኖርም፣ በ7ኛው ክፍለ ዘመን (ከ1,500 ዓመታት በኋላ) ኢትዮጵያ ውስጥ ሙሉው የግዕዝ ትርጉሙ መኖሩ ተሰማ። ከዛ በኋላ መጽሐፉን ለመስረቅ አውሮጳዎች ያልደከሙት የለም። ግን ሳይሳካ ቆይቷል። የፈረ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.