Skip to main content

Posts

Showing posts from September, 2016

Sharing the Burden…

How many prisoners of conscience do you think are held in Qilinto, Kality, Shoa Robit and Zeway Federal prisons for having different political thoughts to the regime in Ethiopia? In Qilinto alone, there are estimated of 500 of them who are not convicted yet. How many of these are recognized by the public to whom they are sacrificing? My arrest and 18 months of stay in prison has helped me meet a lot of prisoners. I met a guy who has never heard the name of a rebel group (Amhara Democratic Forces Movement) of which he was accused being a member; I met a guy who is accused for affiliation of Oromo Liberation Front whose leaders he can't name; I met the ex-president of regional state of Gambella, Air Force Capitans, and many others who has no one to visit, hire a lawyer, or even to remember to… By the time I was held in Qilinto, many Ethiopians who raised religious freedom from State interference, Gondere Amharas, Oromo University students, youths from Gambella and Benishangul Gumuz...

EthiopiaProtests: ‘የበሰለው ፍሬ’

ሐምሌ 2006 ከማዕከላዊ ወደ ቂሊንጦ ስዛወር፣ ዞን ሁለት ነበር የተመደብኩት። በወቅቱ በሽብር የተከሰሱ ብዙ ጎንደሬዎች ነበሩ። አልጋው ሥር "ደቦቃ" በማስተኛት ያስተናገደኝም ቢራራ የተባለ ጎንደሬ ነበር። ከዚያ በፊት ከሥሙ በስተቀር የማላውቀውን ፋሲል ደሞዝን አንድ ዘፈን ያስተዋወቀኝ እሱ ነው። ዘፈኑን እስከዛሬ ባልሰማውም ሁለቱን ስንኞች ግን በቃሌ ይዣቸዋለሁ። "አረሱትን አልሰማኸውም?" አለኝ ድጋሚ 'አልሰማሁትም' አልኩት ባለማወቄ ሲገረም አይቼ እያፈርኩ፤ ስንኞቹን ነገረኝ። "አረሱት ይሉኛል የመተማን መሬት፣ ያውም የኛን ዕጣ እነሱ ምን ያርጉ ከኛ ሰው ሲታጣ።" ሰሞኑን 17 ያህል አርቲስቶች ለአዲስ ዓመት ዋዜማ አቅደውት የነበረውን የሙዚቃ ድግስ በሐዘናችን ምክንያት መሰረዛቸውን ሰማሁ። አርቲስቶቻችን ሰው እየወጣቸው ነው ማለት ነው የሚል ስሜት ተሰማኝ። እኛው ያከበርናቸው አርቲስቶች የሕዝባችንን ሐዘን ማክበር ከጀመሩ ትግላችንንም የሚቀላቀሉበት ግዜ ሩቅ አይሆንም፣ እኛም 'አርቲስት' የሚለውን ቃል ስድብ ከማድረግ እንቆጠባለን እያልኩ ሳስብ ሳልሰማቸው ያመለጡኝ ብዙ የትግል ዘፈኖች እንዳሉ ተረዳሁ። የኦሮምኛ ዘፋኞች ዘፈንን የትግል መሣሪያ ማድረግ ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። ሁሉም ዕኩል መደመጥ አልቻሉም እንጂ ባለፈው አንድ ዓመት በአማካይ በቀን አንድ የትግል ዘፈን እየለቀቁ ነበር። ከሁሉም ግን በጣም ተወዳጅ የሆነውና ቋንቋውን የማታውቁትን ሳይቀር የሚወዘውዘው የሀጫሉ 'ማለን ጅራ' ነበር፤ ስለዚህ ዘፈንም መጀመሪያ የሰማሁት እዚያው ቂሊንጦ በመጣ ወሬ ነው። ኪነ ጥበብ ትግሉን ሲቀላቀል የትግሉን መብሰል የሚያሳይ ምልክት አድርጌ ነው የማየው። በአዲስ አበባ ...