በፍቃዱ ኃይሉ * ሐምሌ 27/2007 ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና ቀናኢ - ፍትሕ ለሆኑ ሰዎች በሙሉ የመርዶ ቀን ነበር፡፡ ስለ ሠላማዊነታቸው የተመለከታቸው በሙሉ የፈረደላቸው፣ ባንድ ወቅት መንግሥትም በወኪሉ በኩል ሲደራደራቸው የነበሩ፣ ለሦስት ዓመታት ያክል በሕግ የበላይነት አምነው ችሎት ፊት የሠላማዊነታቸውን ማስረጃ ሲደረድሩ የቆዩት ( በተለምዶ በሚጠሩበት ሥማቸው ) የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ አፈላላጊ “ ኮሚቴዎች ” እስከ 22 ዓመት የሚድረስ የፅኑ እስራት ፍርድ ተጣለባቸው፡፡ ይህንን ዜና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( ኢብኮ ) ከ 7 ፡ 30 የቀን ዜና እወጃው ጀምሮ ሲለፍፈው ነበር፡፡ ከዜናው ጋር በማነፃፀሪያነት የቀረበው ሌላ ዜና ግን ግቡን ስላልመታ ይመስላል ማታ አልተደገመም፡፡ ያልተደገመው ዜና በተመሳሳይ አንቀፅ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለተፈረደባቸው ሰዎች ነው፡፡ እነዚህኞቹ መሣሪያ ታጥቀው የተወሰኑ ሰዎችን ገድለዋል፡፡ ሆኖም እንደ ኢ.ብ.ኮ. ዘገባ “ የቅጣት ማቅለያ በማስገባታቸው ” 14 ዓመት ተፈርዶባቸዋል፡፡ ዜናዎቹን ያዳመጡ ሰዎች ግን ማነፃፀር የቻሉት የሠላማዊነት ቅጣት መክበዱን ነበር፡፡ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ “Military and militarism in Africa: the case of Ethiopia” ባሰኙት ጥናታቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፡ - “በመካከለኛውዘመን እንዳየነው [ ጨዋ ] ማለት መሣሪያ ታጣቂ ማለት ነበር፡፡ ኋላ ላይ ግን ትርጉሙ ተለውጦ መልካም ፀባይ ያለው ማለት ሆነ፡፡ በተመሳሳይ፣ የቃሉ ተቃራ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.