Skip to main content

Posts

Showing posts from January, 2016

Will #OromoProtests ever Spread to #EthiopiaProtests?

More than 100 towns (with population more than 5,000) in Oromia have witnessed protests; more than 140 people were killed; and, more than 5000 people were arrested following the ongoing Oromo protests. Yet, it seems the protests are limited in Oromia region and didn't show any sign of spreading to other regions. It is a serious issue but no political analyst seemed to be seriously concerned about it. Will the protest grow to be Ethiopia-wide? Is there even a need for it to be? If so, how? I will try to raise similar questions with my own answers. My hope is you will proceed in elaborating it. Will Oromo Protests Continue? Oromo protests are not only about the Addis Ababa expansion plan. As many Oromo civil rights activists are explaining, the protests are about anonymous self-administartion of Oromia, proprotional representation of its people in Federal administration, upraisal of Afaan Oromo to Federal working language status and etcetra. Therefore, lone-cancellation o...

Bewketu Seyoum፤ የኔ ትውልድ Eyeኮነ!

በውቀቱ ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት ሰው መኮርኮር ይችላል። የተማረው ሳይኮሎጂ ነው። ሳይኮሎጂ የሳቅ ስስ ብልት የት እንደሆነ አስተምሮት ይሆን እላለሁ። ነገር ግን ማሳቅ የጀመረው ትምህርቱን ከመጨረሱ በፊት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሳይኮሎጂስቶች ሲያስቁ ስላልገጠመኝ በዚህ ረገድ ግንኙነት (co-relation) መፈለጌን አቋርጫለሁ። በውቀቱን እንደ ኮሜድያን አልቆጥረውም [ነበር]። እንደዛ እንድቆጥር የተገደድኩበት አንድ ጊዜ ቢኖር ሀብቴ ከሞተ በኋላ ሀብቴን ተክቶ ሲመጣ ነው፤ ደረጄና በውቄ ነገር ሁኖ። እዚያ ላይ በውቄ ሀብቴን ተክቶ መምጣቱ ከቀልዶቹ የተሻለ ያስቅ ነበር፤ የተሻለ። በውቀቱ ያንን ሚና ደግሞ ላይመለስበት ባደባባይ ቃል ገብቷል። በውቀቱ ፈላስፋ ነው፤ ኮሜድያን አይደለም። በነገራችን ላይ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋም በውቀቱን ፈላስፋ ነው ይላል። "ስንት ፕሮፌሰሮች ሁለት ክላስ የሚያሰተምሩበትን ሐሳብ እሱ በሁለት መሥመር ቁጭ ያረገዋል፣" በማለት፦ ሉላዊነት "የጋራችን ዓለም፣ የጋራችን ሰማይ የብቻችን ሕመም፣ የብቻችን ስቃይ።" *** "አገር ድንኳን ትሁን ፣ ጠቅልዬ የማዝላት ስገፋ እንድነቅላት፣ ስረጋ እንድተክላት።" *** "ከተመኙ ላይቀር ወንዝነት መመኘት፣ አገርን ሳይለቁ ሰው አገር መገኘት።" በራሪ ቅጠሎች ላይ የመጀመሪያዋ ጽሑፍ ትመስለኛለች በሕይወት ላይ የሚስቅባት ገፀ–ባሕሪይ አለ። ሕይወት ግን ዝም ብላ የምታስቅ እንዳልሆነች የልቦለዱ መጨረሻ ይተርካል። በመጨረሻው መጽሐፉ (መውጣትና መግባት) መግቢያ ላይ ደግሞ፣ ግጥም ተርጉሞ እንደመግቢያ አስቀምጧል። ታዲያ ዘነበ ወላ አዲስ አድማስ ላይ መጽሐፉን ሲተቸው (መጽሐፉ እንደበፊቶቹ ሲሪዬስ ...

ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት እስከ ማበሳጨት

“ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ምንድን ነው? ማበሳጨትን ካላካተተ፣ ሕልውና የለውም፡፡” ~ ሰልማን ሩሽዲ ፩ - ማበሳጨት ‹‹በመስከረም ወር 1997፣ ዢላንድስ ፖስተን የተባለ የዴንማርክ ጋዜጣ ነብዩ መሐመድ ላይ የሚሳለቁ ካርቱኖችን ይዞ ወጣ፡፡ የዚህ ሕትመት ዜና በመላው ዓለም እንደተሰማ በየቦታው ያሉ ሙስሊሞች ቁጣቸውን በአደባባይ መግለጽ ጀመሩ፡፡ የተቃዋሚዎቹ ምክንያቶቻቸው ሁለት ናቸው፤ አንደኛ፣ ነብዩ መሐመድን በምስል መግለጽ በእስልምና ሃይማኖት አይፈቀድም የሚልና፤ ሁለተኛ፣ ካርቱኖቹ በጥቅሉ እስልምናን እና ሙስሊሞችን ከሽብር ጋር አቆራኝተው ይገልጻሉ የሚል ናቸው፡፡  ሠላማዊ ሰልፎችና ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በጋዜጣው አዘጋጆች እና በዴንማርክ መንግሥት ላይ ተቀሰቀሰ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሕይወት እስከመቅጠፍ የዘለቀ አመጽ የተቀላቀለባቸው የተቃውሞ ሰልፎች ነበሩ፡፡ ካርቱኖቹ ግን በመላው ዓለም በሚገኙ በሌሎች ጋዜጦች ላይ ለ ዢላንድስ ፖስተን ጋዜጠኞች የሞራል አጋርነት ለማሳየት በሚል ሰበብ ድጋሚ ታትመው ይበልጥ ተሰራጩ፡፡›› (Paul Sturges, 2006) ሌላ ምሳሌ እንውሰድ፡፡ አንድ ወንድ “‹ሴቶችን ማስተማር የአገርን ሀብት ማባከን ነው፤ ስለዚህ ሴቶችን ማስተማር ካለብን የቤት አያያዝ፣ ምግብ ማብሰል እና ልጅ አስተዳደግ እናስተምር እንጂ ሌላ ‹የነጭ ኮሌታ› ሥራ የሚያስይዝ ትምህርት ማስተማር የለብንም› የሚል አስተያየት ሲሰጥ በቴሌቪዥን ተላለፈ፡፡ ይህን ተከትሎ የከተማው ሴቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ፡፡ ወንድ አሽከርካሪዎች የሚነዷቸውን መኪኖች ሰባበሩ፡፡ ወንዶችን እያሳደዱ ደበደቡ፡፡” በዚህ የፈጠራ ታሪክ ውስጥ የአስተያየት ሰጪው ሐሳብ ሴቶቹን አበሳጭቷቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለአመጹ እነርሱን አነሳስቷቸዋል ብሎ መደምደ...