Skip to main content

Posts

Showing posts from May, 2013

#Ethiopia: ከቃሊቲ ወደ ዝዋይ፤ ለምን?

ልክ የዛሬ 22 ዓመት (ማክሰኞ ዕለት)፣ በግንቦት 20 ኢሕአዴግ ቤተ መንግሥቱን ተቆጣጠረ፡፡ በዕለቱ በኢትዮጵያ ሬድዮ እየተደጋገመ ይተላለፍ የነበረው ‹‹ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን… ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ሲባል… ተቆጣጥሮታል›› የሚሉት ቃላት ያሉበት እወጃ ነበር፡፡ ከ22 ዓመት በኋላ ‹ደርግ ሲጠቀምበት የነበረው፣ ኢሕአዴግ እየተጠቀመበት ነው› ማለት ብቻ ይቻላል፡፡ የ‹‹ሰፊው ሕዝብ›› ጥቅምና ተሳትፎ ተመናምኖ፣ ተመናምኖ አሁን የደረሰበትን ትክክለኛ ቦታ መገመት ያስቸግራል፡፡ ስለሆነም የኢሕአዴግ መንግሥት ‹‹እየተጠቀመበት›› ያለውን ነገር እያስጠበቀ ያለው በአፈና ነው፡፡ በምርጫ አፈና፣ በሚዲያ አፈና፣ በፖለቲከኞች አፈና… ወዘተ፡፡ የዛሬ አራት ዓመት ገደማ በሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይ በመንግሥት ባለሥልጣናት ‹‹የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ›› ተብሎ የነበረውና በኋላ ደግሞ በፍርድ ቤት ‹‹ሕገ መንግሥቱን በኃይል የመናድ ሙከራ›› ተብሎ በቀረበው ክስ 23 ሰዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ አንዱ የሞት ፍርድ እና ቀሪዎቹ ደግሞ የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡ ስለነዚህ እስረኞች መዘንጋት እና የቤተሰቦቻቸው ሁኔታ ከአንድ ወር በፊት ዞን ዘጠኝ ላይ የወ/ሮ እማዋይሽን ልጅ በማነጋገር የተጻፈውን ማንበባችን ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ከነዚህ እስረኞች መካከል በእነብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ከተከሰሱት 23 ‹‹ታራሚዎች›› መካከል ከ4ቱ በስተቀር (19ኙ) ወደዝዋይ በቅርቡ ተዛውረዋል፡፡ ዝውውሩ እነርሱን ብቻ የተመለከተ ባይሆንም፣ ድንገተኛነቱ እና ምክንያት ያልተሰጠበት መሆኑ ጥያቄዎችን እንድናነሳ ያስገድደናል፡፡ ወደዝዋይ ከተዘዋወሩት መካከል ቃሊቲ እንዲቀሩ የተደረጉት አቶ መላኩ ተፈራ ጥላሁን (የሞት ፍርድ)፣ ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ (ዕድሜ ...