Skip to main content

Posts

Showing posts from December, 2011

ጨርቆስና ቦሌ - ሕይወትን እኛ እንደኖርነው!

ጨርቆስና ቦሌን ምን አገናኛቸው? በርግጥ ለዚህ ጥያቄ መልሱ ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም ጨርቆስና ቦሌ ተለያይተው አያውቁም - በቀልድም በድንበርም፡፡ በኑሮ መቀለድ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የኑሮአችን አካል ነው፡፡ የጨርቆስ እና የቦሌ ጉርብትናም በኢትዮጵያ እየሰፋ ለመጣው የኑሮ ደረጃ ልዩነት በርካታ አዳዲስ ቀልዶችን አበርክቷል፡፡ ምንም እንኳን የጫወታዬ ዓላማ ቀልዶቹን ለአደባባይ ማብቃት ባይሆንም አንድ ስሜቴን የነካ ቀልድ ግን ሳላስታውስ ማለፍ አይቻለኝም፡፡ ቀልዱ የተነገረው ወንድማማቾቹ የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ጦርነት ላይ በነበሩበት ጊዜ ነበር፡፡ መንግስታችን በወቅቱ ‹‹ፈንጂ ማክሸፊያ›› ወጣቶች ያስፈልጉት ነበርና‹ወዶ ዘማች› የሚለው ቃል ወረት ሆኖ ነበር፡፡ እናም የሃገራቸው መወረር ያስቆጣቸው የቦሌ ልጆች ገንዘብ አዋጥተው ለጨርቆስ ሰፈር ‹ወዶ ዘማቾች› ደሞዝ እንዲከፈል አበረከቱ ተብሎ ተቀለደ፡፡ ከዚህ ቀልድ በኋላ ግን አንድ ጥያቄ በጭንቅላቴ ሲጉላላ ከረመ፡፡ ‹‹የሃብታምና የድሃ ሕይወት የዋጋ ልዩነት ስንት ነው?››

የዳዊት ከበደ እና የተመስገን ደሳለኝ ወጎች

“Every newspaper that's rented instead of being sold is a further challenge for those few trying to survive in the tough Ethiopian media environment,” ይህን የተናገረው የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ለሲኤንኤን ነበር፡፡ በአዲስ አበባ የጋዜጣ ኪራይን በተመለከተ ነበር፤ የጋዜጣ ኪራይ በአዲስ አበባ ቀድሞ ለታመመው የግሉ ሚዲያ ተጨማሪ ተግዳሮት መሆኑን ሲገልፅ፡፡ (የጋዜጣ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢዎችን›› ዳዊት እንዴት እንደማይወዳቸው ይታያችሁ! እኔ ግን አታስዋሹኝ እወዳቸዋለሁ፡፡ እስኪ አስቡት ሳምንት ሙሉ የሚታተሙትን ጋዜጦች እየገዛሁ ባነብ ደሞዜ ይበቃኛል? ጋዜጣ በልቼ፣ በጋዜጣ ተሳፍሬ፣ በጋዜጣ የቤት ኪራይ ከፍዬ፣ በጋዜጣ ሁሉን ነገር አድርጌ መኖር ይቻለኛል?) ዳዊት ከበደ አሁን ዋሽንግተን፣ አሜሪካ ነው ያለው፡፡ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ መንግስት ዕድሜ ልክ ተፈርዶበት ‹‹በይቅርታ›› መፈታቱ ይታወሳል፡፡ እንግዴህ ያ ‹‹ይቅርታ›› እንደሰኞ ሊሰረዝ እሱ ቅዳሜ ወደአሜሪካ በርሯል፡፡ ይመስለኛል፤ ዳዊት ይቅርታው እንደሚሰረዝ ከመስማቱ በፊት ገምቶ ነበር፡፡ ምክንያቱም የአሜሪካ ቪዛ የማግኘቱ ጉዳይ ቀላል ባለመሆኑ ቀድሞ መጀመርን ይጠይቃልና እሱም ይህንኑ ቀድሞ ማሳካት ችሎ ነበር ማለት ነው፡፡