ከእኛ አገር የማያልቁ ችግሮች መካከል አንዱ የማንነት አረዳድ እና አበያየን ጉዳይ ነው። ማንነት እና ምንነት የፖለቲካ ጫወታችን አስኳል ሆኖ ሳለ፣ የማንነት አበያየናችን ግን ግለሰቦች የራሳቸውን ማንነት የሚበይኑበት ነጻ ዕድል የማይሰጥ ነው። የኦነጉ በያን አሶባ ባንድ ወቅት ከኢሳት ቴሌቪዥን "ኦሮሞ ማነው?" የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። "ኦሮሞ ነኝ ያለ" የሚል ምርጥ መልስ ሰጥተዋል። ነገር ግን ብዙዎች ማንነትን በዘር የሚወረስ እንጂ በማኅበራዊ-ሥሪት (social construction) የሚመጣ ነገር አድርገው አይመለከቱትም። እውነት መሆኑን ከራሷ ማረጋገጥ አልቻልኩም እንጂ ድምፃዊ ሴና ሰለሞን ከአማራ ተወላጆች የተወለደች ኦሮሞ ነች፤ "ኦሮሞ ነኝ" ስላለች። ራሷን የምትገልጸው እንደ ኦሮሞ ሲሆን፣ በዘፈኖቿ የታገለችውም ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት ነው። የወላጆቿ የማንነት ታሪክ የሐሰት ወሬ ቢሆን እንኳ ነባራዊ ምሳሌ እናጣለን እንጂ፣ ምሳሌው ማንነትን የመምረጥ ግለሰባዊ ነጻነቱን የተሳሳተ አያደርገውም። 'ኢትዮጵያዊ ማንነት አለ፣ የለም? ጎጃሜ ማንነት አለ፣ የለም? አዲሳበቤ ማንነት አለ፣ የለም?' የሚሉት ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ምንጫቸው የግለሰቦች ማንነት እኛ ራሳችንን እንዲሁም ሌሎችን ከምንረዳበት መንገድ ውጪ መወሰን የለበትም ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ነው። በቀላል ቋንቋ ለመግለጽ አባባሉ "እኔ ናችሁ ከምላችሁ ውጪ መሆን አትችሉም" ነው። በበኩሌ ሰዎች የራሳቸውን ማንነት ብለው የሚጠሩት ወይ 'የሚኮሩበትን' አሊያም 'የተበደለባቸውን' [ወይም የተበደለባቸው የሚመስላቸውን] ማንነታቸውን ነው ብዬ ነው የማምነው። ይሁን እንጂ ሁሉም ሰዎች ማኅበራዊ ሥሪታቸው ከብዙ ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.