Skip to main content

Posts

Showing posts from November, 2017

What if We Were Raised with an ‘Authoritarian Personality’?

We less often discuss personalities that are fertile grounds either to be ruled by authoritarians or to be one of them. But, I think, it is important to look what is in them as it looks like we dont basically change from the way our parents have raised us. Our ancestors were either members of the oppressors or the majority (the oppressed) in the past, so are we. It happens to be we use that same privilege inherited from our parents to advance others; or, to remain underprivileged. History proves it is most probable that off springs follow their ancestors footsteps. Chances are big that children of the poor will remain poor; children of farmers remain farmer; children of democratic societies will remain democrat and etc. And, all this is until the quagmire breaks at some point. What's keeping us a conformist? And, how can we break it? I was reading a book titled "Between the World and Me" authored by Ta-Nehisi Coates and found some childhood experiences were shar...

ተቃዋሚዎች ከራሳቸው ይልቅ ኢሕአዴግን ያምኑ ይሆን?

ከዓመታት በፊት አንድነት ፓርቲ በሕይወት ሳለ፣ የቀድሞዎቹ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት አቶ ስዬ ኣብርሓ እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲውን ሊቀላቀሉ ሲሉ ትልቅ ፌሽታ ሆኖ ነበር። እንዲያውም ‘መርሕ ይከበር’ በሚል የተገነጠለው ቡድን፣ እነርሱን ለመቀበል የተዘጋጀውን ድግስ በአመፅ እስከማደናቀፍ ደርሷል(?)። ቅራኔው “እነርሱ የተለየ አቀባበል የሚደረግላቸው የገዢው ፓርቲ የቀድሞ አባል ስለሆኑ ነወይ?" የሚል ነበር። ተቃዋሚው የቀድሞ የኢሕአዴግ አባል ለቅቆ ሲወጣ ማግነን ያውቅበታል። በአንድ በኩል ሳስበው፣ መቃወማቸው ትክክል መሆኑን የገዢው አባላት መልቀቅ ለተቃዋሚዎቹ ስለሚያረጋግጥላቸው ይመስለኛል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ከጥቅም ባሕር ውስጥ መውጣት ስለሚከብድ ያንን እያሰቡ ይመስለኛል። የኋለኛውን እንዳላምን እንደ ዶ/ር ነጋሶ፣ ከጥቂቶቹ በቀር ብዙዎቹ ተገፍተው ነው ከገዢው የሚወጡት። የሆነ ሆኖ፣ አናንያ ሶሪ በስላቅ እንደተናገረው፣ ‘ብለን ብለን ኦሕዴድ እና ብአዴን ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ዛሚ እና ENN ነጻ ሚድያዎች የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል’። ለማንኛውም በምናገባኝ ነገሩን ከመታዘብ ይልቅ የኦሕዴድ (እንዲሁም የብአዴን) የሰሞኑ እምቢተኝነት እውነት ወይስ የሕወሓት ሴራ? ተቃዋሚው (በፓርቲ የታቀፈውም ያልታቀፈውም) ጉዳዩን እንዴት ነው ማስተናገድ ያለበት? የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሞክር። የጠላቴ ጠላት ለኔ ምኔ? በተቃዋሚዎች ዘንድ "የሕወሓት የበላይነት" መኖሩ እምብዛም አጠራጣሪ አይደለም። ማኅበራዊ ሚድያ አሁን (ከተዳራሽነቱ በላይ) በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሐሳብ አቅጣጫ አስማሪ እንደመሆኑ ይህንን እምነት የበለጠ በማስረፅም ሆነ በመታገል ረገድ የጉዞ ካርታ (road map) አስቀማጭ ነው። ይህንን ብዙዎች መረዳታቸው ሽሚያ ...

ማነው አሳሪ? ማነው ፈቺ?

አግባብ ያልሆኑ እስሮች፣ ያልተጠበቁ ፍቺዎች እና የማይታመኑ የፍቺ ክልከላዎች ደጋግመው ቢከሰቱም ሁሌ እንደ አዲስ የሚያወያዩን አጀንዳዎች ናቸው። ኦቦ በቀለ ገርባ የታሰሩት የኦሮሞ ሕዝብን ጥያቄ ያለ ፍርሐት ስላስተጋቡ ብቻ ነው። ይህን የምለው ለይስሙላ አይደለም፤ የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን ማስረጃ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ አራተኛ ወንጀል ችሎት ተገኝቼ አድምጬያለሁ። ችሎቱ ክሳቸውን ከሽብር ወደ 'በንግግር አመፅ ማነሳሳት' (የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 257/ሀ) ዝቅ ሲያደርገው ዋስትና እንደሚያሰጣቸው ግልጽ ነበር። ችሎቱ በዋስትና ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት ከአንድ ቀጠሮ በላይ ሲወስድ አይቼ አላውቅም። እርሳቸውን ግን ደጋግሞ ቀጠሮ ሲሰጣቸው፣ ዳኞች ዋስትናውን መከልከልም ሆነ መፍቀድ የፈሩ ይመስል ነበር። በመጨረሻ የሞት ሞታቸውን ከለከሏቸው እና አረፉ። ይግባኝ ተባለ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ30 ሺሕ ብር የስር ፍርድ ቤት የከለከለውን ፈቀደ። ቂሊንጦ እስረኛ ማቆያ ቤት እስረኛውን በመፍታት ፈንታ ደብዳቤው ላይ የተጻፈው ቁጥር አደናገረኝ በሚል ሰበብ ሁለት ቀን አሳደራቸው። በመሐል ፋና ሬዲዮ የኦቦ በቀለ ፍቺ በዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ባይነት፣ በሰበር ሰሚ ችሎት ታገደ የሚል ዜና ይዞ ወጣ። Déjà vu.  ሐምሌ ወር 2007፣ በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃም ሰለሞን ነጻ ከተባሉ በኋላ የተከሰተው ይሄንኑ ይመስል ነበር። ቤተሰቦቻቸው ሲፈቱ ለመቀበል ቂሊንጦ በር ላይ ሲመላለሱ፣ ማረሚያ ቤቱ ሰበብ ሲፈጥር አቆያቸው፤ በመሐል፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍቺያቸውን እንዳገደው ተሰማ። ከዚያ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በዞን ዘጠኝ ጉዳይ ከታሰሩት አምስቱ ድንገት ስማቸው ተጠርቶ...