ፎቶዎች ከቃላት በላይ ይናገራሉ እንዲሉ ባለፈው ዓመት ወዲያ ወዲህ ስል መንገዴ ላይ አጋጥመውኝ ካነሳኋቸው ፎቶዎች ላካፍላችሁ ወደድኩ:: እነሆ:-
አራት ኪሎ የፈረሱት ሰፈር አካባቢ ነው:: ጽሑፉ "ስለቀኑብን አፈረሱብን" ይላል:: ይህን ፎቶ ያነሳሁት አምና ነው:: አሁን በቀይ ቀለም ተሰርዟል:: |
ድርጅቱ በመስተንግዷቸው ከምናደንቃቸው አንዱ ቡና ሻጭ ካፌ ነው:: |
ከኢምፔሪያል ሆቴል ወደቦሌ ለመሄድ አንዳንዴ ከመኪና ይልቅ በጀልባ ይቀላል:: |
ፒያሳ - ራስ መኮንን ግርጌ |
የቴኒክ ብልሽት:- መጽሔቱ በአንድ እትሙ ሽፋን ገጹ
ላይ ኢትዮጵያ ከስንዴ ኢምፖርት አድራጊነት አልተላቀቀችም ይላል፡፡ የውስጥ ገጹን ጽሑፍ ደግሞ በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፡፡
|
የቴኒክ ብልሽት (ቀጣይ):- መጽሔቱ በውስጥ ገጹ ላይ ኢትዮጵያ ከስንዴ ኤክስፖርት አድራጊነት አልተላቀቀችም ይላል፡፡ (የሽፋን ገጹን ጽሑፍ ከላይ ይመልከቱ፡፡) |
Not Yet Arrived in 2014. In front of Bole Friendship Building |
ሁሉም ሰዎች አንድ ጋዜጣ (ልዕልና ከመታገዱ በፊት) - አሁን እነዚህ ካፌዎች በረንዳቸው ላይ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል:: |
ይህ ማስታውቂያ ተዘቅዝቆ ነው ወይስ ተልጦ ወይስ ግራ ቀኝ ተዛውሮ ወይስ ሁሉም? (ራስ መኮንን አለፍ ብሎ) |
የቤተልሔም ሕንፃ /መገናኛ/ (ጀርባ - ፊቱን ከታች ይመልከቱ) |
ቤተልሔም ሕንፃ ከፊቱ (በነገራችን ላይ ይህ ሕንፃ መስታወቱ አንፀባራቂ በመሆኑ እንዲቀየር ማስጠንቀቂያ ከተጻፈበት ወራት አልፈዋል::) |
Guess Where? You got it right; it is in front of Bole Medhanialem - የጄኔራሎቹ ሰፈር |
ለልማቱ ነው - ምናለበት? |
ቃሊቲ (የጠጠር ማምረቻውን ስም ሳየው ያስቀኛል:: አንድ ሰሞን
ሲቪል
ሰርቪስ ኮሌጅን ድንጋይ ማምረቻ ይሉት የነበረው ይመጣብኛል፡፡) |
Got it Wrong: የኮሌጁ የመጽሔት ማስታወቂያ ኮሌጅ የሚለውን ጠንቅቆ አልጻፈውም! |
"ኢ-ልማታዊ መጽሐፎች" (ግልጽ በሆነ ምክንያት የትምህርት ቤቱን ስም ከመጥቀስ እታቀባለሁ) |
"የልማት መስዋዕት" - ለገሃር ከለታት አንድ ቀን |
Legend making: ቦሌ ቴሌ |
ሶኒክ ስክሪን - ፒያሣ |
Legend Making: ቦሌ - ሰን በርድ ካፌ (አሁን ጀግና አይሞትም የሚለው ቅርጽ ተነስቷል) |
ሐዋሳ አውቶቡስ ተራ - "ከኤድስ ለማምለጥ በየሱስ ማመን ነው" Really?! |
ሻሸመኔ - "የረዳኝ እግዚአብሔር ነው መኝታ ቤት" (ይህን ሳየው "እህቴ የላክሽልኝን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ አዋልኩት ሬስቶራንት" ብሎ አብርሃም አስመላሽ የቀለደው ቀልድ ይታወሰኛል::) |
No comments:
Post a Comment