Pages

Wednesday, February 5, 2014

ተቋማዊ አምባገነን




አምባገነን መንግሥታት ሁሉ አንድ አይደሉም:: አንዳንዶች ፍጹም አውቶክራቲክ የሆነ አስተዳደር ሲኖራቸው ሌሎቹ ደግሞዴሞክራቲክየሚመስሉ ተቋማትን በመመስረት አምባገነንነት በመንግሥታዊ አስተዳደሩ ብቻ ሳይወሰን ተቋማዊ (Institutionalized dictatorship) ይዘት እንዲኖረው ያደርጋሉ:: በእነዚህ ተቋማት ውስጥ አምባገነኖች በሥራ ላይ የሚያውሏቸው ሁለት ዋና ዋና መሣሪያዎች አሏቸው፦ ጥቅማጥቅሞችን (ኪራይ) ማካፈል እና የጥቅም ተጋሪዎች ለሆኑት ሰዎች ጊዜያዊ የፖሊሲ ማስተካከያ (Policy concession) እና የአሰራር ሂድት ለውጥ በማድረግ ጥቅማቸውን ማስከበር ናቸው::

እነዚህም በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በኢኮኖሚ እና በመሳሰሉት ተቋማት ሲንጸባረቁ ይታያሉ:: አምባገነኖች እነዚህን ተቋዋማዊ አደረጃጀቶች የሚጠቀሙት ታቃዋሚን እና ተቃውሞን በስልታዊ መንገድ ለማርገብ ሲሆን ሂደቱ እንደ ተቃዋሚው ጥንካሬ ይወሰናል:: ለምሳሌ ተቃዋሚው ድካማ ከሆነ አምባገነኑ ጥቅሞችን በስፋት የማጋራት ግዴታ ስለሌበት ፖሊሲዎችን እና የውስጥ አስራሮችን ብቻ በመጠቀም ሥርዓቱን ያጠናክራል:: በተቃራኒው ተቃዋሚው ጠንካራ ከሆነ ደግሞ ጥቅማጥቅሞችን በማብዛትና ፖሊሲዎች ላይ ጊዜያዊ ለውጥ በማድረግ ተቃዋሚው እንዳያምጽ በሩን ይዘጋል (assurance for non-rebellion opposition):: ተቃዋሚው ደግሞ በጣም ጠንካራ ከሆነና የአምባገነኑን መንግስት ለመጣል የሚያበቃ ኃይል እና እድል እንዳለው የሚያረጋግጥ መረጃ ካለ ስርዓቱ ከጥቅማጥቅሞችን እና ከጊዜያዊ የፖሊሲ ለውጦች በተጨማሪ ሌሎች የመፍትሄ አማራጮችን ያቀርባል::

አምባገነን መንግሥት ተቃውሟቸውን በይፋ የሚገልጡ እና ጠንካራ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚላቸው ላይ ትኩረት መስጠትና ጫና ማድረግ ይመርጣል:: ጫናውን በቀጥታም ሆነ በተዛዋዋሪ መንገድ ያድረገዋል :: ዋነኛው መንገድ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች በራሱ ቁጥጥር ውስጥ ካሉ ተቋማት በተለያየ መንገድ (systematically) ማስወገድ እና ከደረጃ ዝቅ ማድረግ ሲሆን ሌላው ደግሞ መወንጀል ማሰር ፣ማስፈራራት እና ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ ነው::

የስርዓቱ ተጠቃሚዎች የሚጠቀሙባቸው መንገዶች ለምሳሌ ያህል፦
በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ የሥራ እድል መስጠት በሥራ መደቡ ላይ ላሉ ደግሞ እድገት፣ የተሻለ ደሞዝ፣ የስልጠና እድል ማግኘት እንዲሁም የተጨማሪ ጥቅማጥቅሞች መስጠት:: የግል ሥራ ለሚሰሩ የተፋጠነ እና ለሌላው የማይሰጥ የብድር አገልግሎት የሥራ ፈቃድና በአጠቃላይ ለሥራው ሂድት የሚያስፈልጉ ነገሮችን በሟሟላት ሁኔታዎችን ማመቻቸት:: በትምህርት ዘርፍ ውስጥ የሚያልፉት፣ በሚፈልጉት የትምህርት ተቋም እንዲቀጥሉ፤ ከትምህርቱ ጋር የተያያዘ ክፍያ መሰረዝ (በከፊል እንዲከፍሉ ማድረግ) ለተጨማሪ የትምህርት የተመቻቸ እድል መስጠት:: ይህንን አንፈልግም ብለው እራቸው ከስራዓቱ ጥገኝነት ለመለየት ቢሞክሩም መኖርም መስራትም አስቸጋሪ ስለሚሆን በሁኔታዎች አስገዳጅነት ጥገኛ የመሆናቸው እድል ሰፊ ነው::

የሥርዓቱ የሙሉ ጊዜ ተጠቃሚዎች የዕለት ከዕለት ኑሯቸው በስርዓቱ ህልውና የሚወሰን ስለሚሆን በስርዓቱ ላይ ምንም አይነት ጥያቄ ለማንሳት አይፈልጉም:: ቢፈልጉም አይችሉም። ምክኒያቱም እነሱ አብዛኛው ነገር የተሟላላቸው ስለሆኑ የሚያሳስባቸው ነገር መጠነኛ ስለሆነ በአደባባይ ከመናገር በማልጎምጎም መጨረስን ይመርጣሉ:: ቅሬታ አለን ብለው ማሰማት የሚፈልጉም ቢኖሩ ችግሩ አሳስቧቸው ሳይሆን የአምባገነኑ ስርዓት ለተቃዋሚ ድምጽ እድል ይሰጣል ለማሰኘት ብሎም ለዚህ ተግባራቸው እንዲመሰገኑበት ብቻ ነው:: ሌላው እና ዋነኛው የስራቱ ተጠቃሚዎች መገለጫ ስርዓቱን እና ተቃዋሚን በአንድ ሚዛን በመመዘን ተቃዋሚውን ጥፋተኛ በማድረግ በተደጋጋሚ ጥላሽት በመቀባት ማጥላላት ነው::

በመጨረሻም ባገኙት አጋጣሚ ተዋስዖ ትኩረት በማስቀየር ሰዎችን ሰለአምባገነኡ ሥርዓት ትኩረት እንዳይሰጡ ማድረግ እና በተቻላቸው መጠን የሃሳብ አንድነት እንዳይፈጠር ማድረግ ነው::

No comments:

Post a Comment