ባሕር ማዶ ካሉ ሰዎችጋ ስናወራ አንዳንድ የማይገቡን ወሬዎችን እየሰማን ጭንቅላታችንን እየናጥን “ወቸ ጉድ!” ማለታችን አይቀሬ ነው፡፡ ለኛ ባዳ ከሆነው ከቀላሉ “GPS” ጀምሮ፣ credit card ቢሉ፣ ምን ቢሉ ሁሉም ለኛ እንቆቅልሾች ናቸው፡፡ ወጉ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ እንዲሉ “GPS” ቀርቶብኝ እበላው ባገኘሁ የሚለው እስኪታወሰን ድረስ እንደመማለን፡፡ እዚህ GPS የለም፣ credit card የለም፣ ባቡር (ወይም subway station ብሎ ቋንቋ) የለም፣ smart phone የለም፣ wi-fi የለም (አለ እንዴ?) ለነገሩ የዚህ ጫወታ ጉዳዮች እነዚህ ሁሉ ስላልሆኑ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ በርግጥ ግን ወደጫወታው አጀንዳ ለመድረስ አሁንም ዳር፣ ዳሩን መነካካት የግድ ነው፡፡ ‹አሜሪካኖች ለምን ወፋፍራም ሆኑ? ኢትዮጵያውያኖች ለምን ቀጫጭን ሆኑ?› ብለን ብንጀምርስ!
Friday, February 24, 2012
Friday, February 10, 2012
አማርኛ በመዝገብ ላይ
![]() |
| ዘፍጥረት 29÷11-16 (በግዕዝ) |
በሃገራችን አሁን ዘመን እየቀየረን መጣ÷ እንጂ ሴትን ለማማለል ገዳይነት ነበር የሚያስፈልገው፡፡ አንበሳ መግደል፣ ጠላትን በመግደል… ለዚህም ነው Romance ለሚለው ቃል ትርጉም (በአማርኛ) የማይገኝለት፡፡ ብቸኛው romanticነት ጀግንነት ነበርና፡፡ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ወራጅ ወንዞች እንጂ ውቅያኖሶች አይጎራበቱትም÷ ለዚህ ነው በአማርኛ waterbank፣ shore፣ beach ለመሳሰሉ ቃላት ትርጉም ማግኘት የሚቸግረን፡፡ ይህ ዓይነቱ ችግር የአማርኛ ቃላቶችን ወደእንግሊዝኛ ልንመልስ ስንሞክርም ይገጥመናል፤ ችግሩ እንግሊዝኛው ላይ እርግጠኛ መሆን ስለሚቸግረን ይሄ፣ ይሄ ማለት ያስፈራናል፤ እላይ የተዳፈርነው የራስ መቼም የራስ ነው በሚል ብሒል ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ‹ይሉኝታ› ለሚለው የአማርኛ ቃል የእንግሊዝኛ አቻ አንድ ቃል ፈልጌ አጥቻለሁ፡፡ ምናልባት አፈ-እንግሊዞቹ ይሉኝታ ስለማያውቁ ይሆን?
Thursday, February 2, 2012
የሐበሻ አምልኮ በኢትዮጵያ
(መግባቢያ፤ በዚህ ጽሁፍ ‘ሐበሻ’ ማለት ኢትዮጵያዊ፣ ‘አምልኮ’ ማለትም የተጋነነ አድንቆት የሚል ትርጉም ብቻ አላቸው፡፡) ‹የፈረረንጅ አምልኮበኢትዮጵያ› በሚል በጻፍኩት ጽሁፍ ተበሳጭተው÷ ጠንከር ያለ ነቀፌታቸውን ያደረሱኝ በርካቶች ናቸው፡፡ (በተለይም ethiopianreview.com ላይ!) የዚያን ቀጣይ ጽሁፍ በዚህ ርዕስ ለመጻፍ የተገደድኩት ያለፈው ጽሁፍ ስህተት መሆኑን አምኜ በተቃራኒው ለማረም ቢሆን ‹‹መልካም ነበር፡፡›› ግን አይደለም፤ ያም ሆነ ይህ ጽሁፍ ማሕበረሰባችንን መነቀፍ ባለበት ጉዳይ ለመንቀፍ የማይሳሱ ጽሁፎች ናቸው፡፡በመጀመሪያ የቀደመው ጽሁፍ ለምን ነቃፊ በዛበት የሚል ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ መስሎ ይሰማኛል፡፡ የሁሉንም አስተያየት ሰጪዎች መልዕክት ያለምንም ማንገራገር በአንድ ጨፍልቆ መረዳት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለባዕድ (ማለትም ለፈረንጅ) አምልኮ ወይም አድንቆ እጃቸውን የሰጡት ከመቼ ጀምሮ ነው በሚለው ጥያቄ ውስጥ እኔ መልስ ይሆናል ያልኩት ክርስትና ወደኢትዮጵያ መግባት ከጀመረ ወዲህ ነው የሚለውን ነው፡፡ ብዙዎች ክርስትና መነካቷን አይወዱምና የቁጣ ናዳ አወረዱብኝ ማለት ይቀላል፡፡ (ለጨዋታ ያህል ይሄ ጽሁፍ ‹‹ናዳን ለማቆም የተሮጠ ግለሰባዊ ሩጫ›› ነው ልንለው አንችላለን፡፡) እንዲያውም ክርስትና ለኢትዮጵያውያን የተሰፋ (ከባዕድ ያልወረስነው) እንደሆነ ሊያስረዱኝ የሞከሩ ሰዎችም አልጠፉም፡፡ ይሄ ሐሳብ ነው ወደዛሬው ጽሁፌ የሚያንደረድረኝ - የሐበሻ አምልኮ ብዬዋለሁ፡፡
Sunday, January 29, 2012
አፍንጫ ሲመታ ዓይን አያለቅስም ወይ?
አንድ የቆየ ቀልድ አስታውሳለሁ፡፡ ኒው ዮርክ ውስጥ አንዲትን ሕፃን ልጅ ውሻ ሲያባርራት ያየ አንድ ሰው ውሻዋን በያዘው አጠገቡ ባገኘው ዱላ መትቶ ይገድልና ልጅቷን ያድናታል፡፡ ይህንን ይመለከት የነበረ አንድ ጋዜጠኛ ወደሰውየው ይቀርብና ‹‹እሺ፤ ጀግናው አሜሪካዊ - እስኪ የልጅቷን ሕይወት እንዴት እንዳተረፍክ ንገረኝ?›› ሰውየው ‹‹ኧረ እኔ አሜሪካዊ አይደለሁም›› አለ፡፡ ‹‹እሺ፤ ጀግናው የኒው ዮርክ ሰው..›› ብሎ ጋዜጠኛው ሊቀጥል ሲል÷ ሰውየው ‹‹ኧረ የኒው ዮርክም ሰው አይደለሁ፤ ለጉብኝት ነው የመጣሁት›› ይለዋል፡፡ ጋዜጠኛው ፈገግ ብሎ ‹‹ታዲያ የምን አገር ሰው ነህ?›› ሲል ይጠይቃል፡፡ ሰውዬው ‹‹የሳውዲ አረቢያ›› ሲል ይመልሳል፡፡ በማግስቱ የኒው ዮርክ ጋዜጦች ‹‹አንድ አክራሪ ኢስላሚስት በኒውዮርክ ከተማ ውስጥ ውሻ ቀጥቅጦ ገደለ›› የሚል ዜና ይዘው ወጡ፡፡
ጆርጅ ቡሽ በዘመናቸው ከሰሯቸው ስህተቶች በሙሉ የከፋ ሊባል የሚችለው በሽብርተኞች ላይ ባወጁት ዘመቻ ‹‹ሽብርተኛ›› ማለት ‹‹ሙስሊም›› ማለት እንዲመስል ማድረጋቸው ነው፡፡ ይህንን ለማስተባበል መንግስታቸው ቢደክምም ተሳክቷል ማለት አይቻልም፡፡ ብዙዎች የተወናበደ አመለካከት አፍርተው ቀርተዋል፡፡ በዚህ ብስጭት ሃይማኖታዊ ሕልውናቸውን ለማዳን የፈለጉ የሚመስሉ ምስኪኖች አልቃይዳን ለመደገፍ ተገድደዋል፡፡
አሜሪካ የምታደርገው ማናቸውም ነገር በሌላው ዓለም ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ሉላዊነት (globalization) ባመዛኙ አሜሪካዊነት (americanization) መሆኑን ብዙዎች የሚስማሙበት ሐቅ ነው፡፡ የአሜሪካ ተጽዕኖ ለሁሉም የዓለም አገራት ይዳረሳል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ይሄ ተጽዕኖ ይንፀባረቅ ይሆናል የሚለው ስጋት ለብዙዎቻችን ልብ የሚያርድ ጉዳይ ነው፡፡
Friday, January 27, 2012
የኢትዮ ቴሌኮም ቁልቁለት
![]() |
| ፎቶ፤ www.stockphotopro.com |
ሐሙስ ዕለት አመሻሹ ላይ ስልኬ ካርዱን ጨርሶ የጀመርኩትን ወሬ አቋረጠኝ፡፡ ወዲያው ካርድ ገዛሁና ሞልቼ ወሬዬን ለመቀጠል ተጣደፍኩ፡፡ ምን ዋጋ አለው? አዲሱ *805* የካርድ መሙያም ሆነ የቀድሞው 904 ገንዘቤን ሊቀበሉኝ አልቻሉም፡፡ ብስጭቴ እየተጋጋለ ደጋግሜ ስሞክር አመሸሁ፤ አልተሳካም፡፡ በማግስቱ ካርዱን ለወሬው የማድረስ ሕልሜ አልቆ፣ ገንዘቤን ከኪሳራ ለማዳን ማለዳ ጀምሬ መቀጥቀጤን ቀጠልኩ÷ በቀላሉ የሚሆን አልነበረም፡፡ በመጨረሻ እኩለ ቀን ሲቃረብ 805 – “Sorry, the operation failed. Bye” የሚለውን የተለመደ ጽሁፍ ካስነበበኝ በኋላ÷ ካርዴ እንደተሞላ የሚነግር አጭር የጽሁፍ መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ደስ አለኝ ልበል?! ደስ ሊለኝ ግን አይገባም፤ ምክንያቱም ፍዳዬን ሳይ አድሬ ያረፈድኩት በኔ ጥፋት ሳይሆን በቴሌኮሙ የቴክኒክ ድክመት ነው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ከየት ወዴት?
የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን የስንት ዓመት ስሙን በጥላ ቢሱ ኢትዮ ቴሌኮም የቀየረው የለውጥ ርምጃ የሚጀምረው በስም ለውጥ ነው ከሚል መርኅ ይመስላል፡፡ የራሱን የሚመስል ስም ያጎናፀፈው ፍራንስ ቴሌኮም ቴሌን ማስተዳደር ሲጀምር÷ የተጣለበት ተስፋ (ትርፍ መጨመር ቢሆንም) የተዘበራረቀውንና ዘመናዊነት የጎደለውን አሠራር እንዲያፀዳ በማሰብም ጭምር መሆኑም ይታወቃል፡፡ ግን እየሆነ ያለው የተባለው ነገር ነውን?
ፈረንሳዊው አስተዳደር ሥራውን አሀዱ ያለው የሞቱና ድርጅቱን የለቀቁ ሠራተኞን በኃላፊነት ቦታዎች በመመደብ ነበር፡፡ በርግጥ ያንኛው ለዚህንኛው ሲያስረክብ የተፈጠረ ስህተት ነው ተብለን አምነን ነበር፤ እየቆየን እየተመለከትን ያለነው ግን የዛኔውን እምነታችንን ዛሬ ላይ ቆመን እንድንጠራጠረው የሚያስገድድ ነገር ነው፡፡
Tuesday, January 17, 2012
የፈረንጅ አምልኮ በኢትዮጵያ
ፈረንጅ የሚለው ቃል÷foreign ከሚለው እንግሊዝኛ ቃል የመጣ ይመስለኛል፡፡ ምናልባትም አባቶቻችን foreign የሚለውን እንግሊዝኛ ፈረንጅ ብለው ሳያነቡት አይቀርም፡፡ በዚህ ዓይነት ፈረንጅ ማለት ኢትዮጵያዊ ያልሆነን ሰው ይወክላል ማለት ነው፡፡ እኔ ግን በርዕሴ ፈረንጅ ብዬ የጠቀስኩት ነጮችን መሆኑን ተገንዘቡልኝ፡፡
የፈረንጅ አምልኮ በኢትዮጵያ መኖሩን ሳናውቅ ስር ሰዶ ከርሟል፡፡ ምንም እንኳን ጉዳዩ ቅርጫፉን የዘረጋው አሁን ቢሆንም÷ ከጥንት የተጀመረ አምልኮ ስለመሆኑ የታሪክ ድርሳናትን በመመርመር መረዳት ይቻላል፡፡
የፈረንጅ አምልኮ ድሮ
የፈረንጅ አምልኮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጣባን ክርስትና እና እስልምና ወደኢትዮጵያ በገቡበት ዘመን እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ይሄ ብዙዎችን የሚያናድድ አስተሳሰብ ቢሆንም÷ እኔን ግን ከማሳመን አላለፈም፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን ሀገር በቀል እምነቶችንና ስልጣኔዎችን ደምስሰው ባዕዳን ሃይማኖቶችንና ስልጣኔዎችን የተቀበሉት በነዚያ ጊዜያት ነው፡፡
Friday, January 13, 2012
ሰማንያ ሚሊዮን እስከምንደርስ እንታገላለን
አንድነታችንን የሚፈሩ ሰዎች ብቻ ናቸው የተለያየን እንደሆንን እና የተለያየ ፍላጎት እንዳለን የሚነግሩን፡፡ በፊት ኢትዮጵያውያን ነበርን አሁን ትግሬ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሞ…… አድርገውናል፡፡ አሁን ክርስቲያን፣ እስላም… አድርገውናል፡፡ አሁን አባል፣ ደጋፊ ወይም አሸባሪ ብለውናል፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ እኛ ኢትዮጵያውያን ከሰሜንም፣ ከደቡብም፣ ከምስራቅም፣ ከምዕራብም፣ ከመሃል አገርም ብንመጣ አንድነታችን በምቾታችን ብቻ ሳይሆን በችግራችንም ሳይቀር ይገለፃል፡፡ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ድሮም ሆነ ዛሬ ችግራችን እጦት ነው - የምግብ እጦት፣ የመረጃ ወይም የእውቀት እጦት፣ የነፃነት እጦት ነው፡፡
አንድነታችን እውነት ቢሆንም እኛን የመበታተኑ ትግል ግን አልተሳካም ማለት አይቻልም፡፡ ከአንድነታችን ይልቅ ልዩነታችን እንደጌጥ አንጠልጥለነው እንድንዞር እያደረገን ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ምንም እንኳን በየጓዳችን ሁላችንም በመንግስታችን ሥራ ስንብሰከሰክ ብንቆይም ከጎናችን የተቀመጠውን ሰው ማንነት በርግጠኝነት መናገር እየፈራን፣ እሱ/እሷም እንደኛ በውስጧ የተማረረች መሆኗን ከማሰብ ይልቅ ልዩነታችንን በመጠርጠር ብቻ በዝምታ ታፍነን እና በስጋት ተበታትነን፤ ኢሕአዴግ በጣት በሚቆጠሩ ታማኝ ደጋፊዎቹ ብቻ እየታገዘ አገሪቷን እና ዜጎቿን እንደልብ እንዲያሾራቸው ረድተነዋል፡፡
በምርጫ 97 ወቅት፣ የኢሕአዴግ ከፋፍለህ ግዛ ውጤትን ማስተዋል የታደለ አንድ ወዳጄ የቋጠራት ስንኝ ሁኔታውን ፍንትው አድርጋ ታሳያለች፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)
Transforming Ethiopia’s Exclusionary Constitution into an Inclusive One
Before introducing my proposal, I would like to explain my motivation for writing this now. One of the outcomes of the National Dialogue o...
-
“እኔ የምሞተው ዛሬ ማታ፣ እህሌ የሚደርሰው ለፍልሰታ” (በፍቃዱ ኃይሉ) For English, click here . የኮሪደር ልማቱ በተለይ የመሐል አዲስ አበባን ገጽታ እስከወዲያኛው እየቀየረው ነው። ለአቅመ ማስተዋል ከደረ...
-
(በበፍቃዱ ዘ. ኃይሉ) ዐቢይ አሕመድ ተቃዋሚ መስለው፣ ተቃዋሚ ለብሰው ሥልጣን ከተቆናጠጡ እነኾ ዛሬ ድፍን ስምንት ዓመታቸው። ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ወዲህ በየሁለት ዓመቱ አስተዳደራቸውን የሚገመግም መጣጥፍ ...
-
(በፍቃዱ ኃይሉ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዐቢይ አሕመድ እርካብና መንበር በአባዱላ ገመዳ የተቀየሰ ይመስለኝ ጀምሯል። ምክንያት አለኝ። አባዱላ በተቀናቃኞቹ ጃዋር መሐመድም፣ ዐቢይ አሕመድም አድናቆት የተቸራቸው ሰው ናቸው። ጃ...



