Pages

Saturday, January 25, 2014

የዶጋሊ ድል

    የውጭ ጸሐፊዎች ስለአድዋ ሲጽፉ የአድዋ ጦርነት እያሉ ነው የሚጽፉት፤ እኛ ግን የአድዋ ድል ነው የምንለው፡፡ ማስታወስ የምንፈልገው ድሉን እንጂ ጦርነቱን አይደለም፡፡ የዶጋሊ ድልንም በብዛት የጻፉት የውጭ ጸሐፍት ባብዛኛው ‹የዶጋሊ ጦርነት› እያሉ ነው የሚተርኩት፤ ልዩነቱ እኛም እነሱኑ ተቀብለን ታሪኩን የዱጋሊ ጦርነት እያልን ማስታወሳችን ነው፡፡ ነገር ግን ጦርነቱ በእኛ ድል አድራጊነት እስከተጠናቀቀ ድረስ ልክ እንደአድዋው ሁሉ ‹የዶጋሊ ድል› ብለን መተረክ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥም የዱጋሊ ድል ታሪካዊ ፋይዳ ከአድዋ ድል የሚተናነስ አይደለም፡፡  

ልክ የዛሬ 127 ዓመት ወደኋላ፣ ጥር 18/1879 በራስ አሉላ የሚመራው የኢትዮጵያ ጦር፣ አውሮጳውያን ብዙም ያልተዘጋጀ እያሉ የሚጽፉለትን ነገር ግን በ23 የጦር አመራሮችና በ477 ወታደሮች የተገነባውን ሠራዊት በ10,000 ጦርና ጋሻ እና ጥቂት ቆመህ ጠብቀኝ የታጠቁ አርበኞች ድል ነሳቸው፡፡ ይህ ጦርነት ነበር የአድዋውም፣ የማይጨዉም ጦርነት የቂም መንስኤ እና የድል ዕድል፡፡  

ዶጋሊ፣ በዛሬዋ የኤርትራ ምድር ላይ የምትገኝ መሬት ናት፡፡ ደርግ የዶጋሊ ድል በዓልን ሕዝባዊ በዓል ሆኖ እንዲከበርማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ በዶጋሊ የመታሰቢያ ኀውልት እንዲቆም አድርጎ ነበር፡፡ ጣሊያኖችም በጦርነቱ ለተሰዉ ወታደሮቻቸው ሮም ላይ የመታሰቢያ ኀውልት አቁመውላቸዋል፡፡ የዶጋሊው የድል ኀውልት ግን የሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሕግሓኤ) ደርግን አሸንፎ ኤርትራን ሲቆጣጠር ኀውልቱን አፍርሶታል፡፡  

No comments:

Post a Comment