ሁሉም ሰዎች ይናገራሉ፤ ሁሉም ሰዎች ብሶት አላቸው። ነገር ግን የሁሉም ንግግር እና ሐሳብ የሁሉንም ሁኔታ ያገናዘበ አይደለም። በዚህም ምክንያት ተናጋሪ እንጂ አዳማጭ የለም፤ ብሶት እንጂ አዘኔታ የለም። ምክንያቱም ‘ አገናዛቢነት ’ የለም፤ አንዳቸው የሌላኛቸውን ሁኔታ እና እውነታ ለማገናዘብ ሲሞክሩ አይታይም። አገናዛቢነት የሚናገሩት ነገር ያለበትን ጥቅል ሁኔታ ከግምት ውስጥ ለማስገባት መሞከር ነው። ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ቀውስ ውስጥ የሚያነጋግሩን ክስተቶች ድንገታዊ መነሻ ይኑራቸው እንጂ ታሪካዊ፣ ባሕላዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ወይም አካባቢያዊ አንድምታ ይኖራቸዋል። እነዚህን ማገናዘብ ያስፈልጋል፤ የፖለቲካ ተዋስዖዎቹ የአንድን ወገን በደል፣ የአንድን ክስተትን አደገኝነት፣ ወዘተርፈ አተኩረው ሊናገሩ ይችላሉ። ጉዳዮቹ ግን ከአንድ ወገንም፣ ከአንድ ክስተትም የሰፉ እና ውስብስብ ናቸው። ውስብስብነታቸውን ያላገናዘበ ንግግር ችግሩን የመፍታት አቅም ከማጣቱም ባሻገር፣ ምናልባትም ችግሩ ላይ ተጨማሪ ችግር ሊቆልል ይችላል። ግጭት አገናዛቢነት የነውጥ አዘል ግጭቶች ቦታዎችና ክስተቶች ዳታ (ACLED) የተባለ እ.አ.አ. በ2019 ኢትዮጵያ ውስጥ 300 ገደማ የፖለቲካ ነውጦች፣ 680 ያህል ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት አድርጎ ነበር። የ2020ውን ገና ቆጥረው የጨረሱት አይመስለኝም፤ ሆኖም ከዚህ ጽሑፍ ጋር ሕዳር ወር ላይ ያወጡትን ግጭቶች ያሉባቸውን ቦታዎች የሚያመለክት ካርታ አስቀምጥላችኋለሁ። ግጭቶች የኢትዮጵያ ፖለቲካ እውነታዎች ናቸው። ግጭቶች እዚህም እዚያም አሉ። ነገር ግን የፖለቲካ ተዋስዖዎቹ ግጭት አገናዛቢ አይደሉም። መጀመሪያ ግጭት አገናዛቢነት ...
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.