እንዲያው ለመንደርደር ያህል ‹‹ከለማኝና ከቀማኛ የቱ ይሻላል?›› ተብላችሁ ብትጠየቁ መልሳችሁ ምን ይሆናል? ነገሩ ከሁለት መጥፎ ነገሮች የተሻለ መጥፎ መምረጥ ነው፡፡ (የተሻለ መጥፎ ስንል ጉዳቱ ያልከፋ እንደማለት ነው፡፡) ስገምት፥ ብዙዎቻችሁ ለማኝ የምትመርጡ ይመስለኛል፤ ግን ለማኝ ከቀማኛ በምን ይሻላል? ሁለቱም የሰው ገንዘብ ፈላጊዎች አይደሉም? ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል እንዲሉ፣ አንዴ የታዘብኩትን ላውጋችሁ፡፡ ከእለታት አንድ ቀን፣ ከአንድ ካፍሬተሪያ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ማኪያቶ እየጠጣሁ እቆዝም ነበር፡፡ ከፊት ለፊቴ ታክሲ ተራ አለ፡፡ ታክሲው ተራ አካባቢ፥ ከባለታክሲዎቹ ውጪ የዕለት እንጀራቸውን ለማግኘት የሚራወጡ ሦስት ተዋናዮች ነበሩ - ተራ አስከባሪው፣ ለማኝ እና ማስቲካ ቸርቻሪ፡፡
Passionate about the ideas of liberty and dignity, and of course prosperity too.