Showing posts with label Media. Show all posts
Showing posts with label Media. Show all posts

Monday, February 11, 2019

ለውጡ እና የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ


አሁን እየተካሔደ ያለው የፖለቲካ ለውጥ ፍኖተ ካርታ የለውም በሚል በተደጋጋሚ ተተችቷል። ይልቁንም፣ ሲሆን ሲሆን ለብዙኃን መገናኛዎች አጀንዳ በማበጀት፥ ሳይሆን ሳይሆን ደግሞ “ሚዲያዎች ምን አሉ?” የሚለውን እያሳደዱ መልስ በመስጠት የተጠመደ ለውጥ ነው የሚለው የአደባባይ ምሥጢር ሆኗል። ብዙኃን መገናኛዎች በለውጡ ላይ ይህንን የሚያክል ትልቅ ተፅዕኖ እንዳላቸው ከታወቀ ዘንዳ በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል። ለውጡ ፍኖተ ካርታ ባይኖረውም፥ ብዙኃን መገናኛዎቹ ግን ፍኖተ ካርታ ሊኖራቸው ይገባል፤ “ምን-ለምን-ለማን ነው የሚጽፉት ወይም ለተደራሲዎቻቸው የሚያቀርቡት?” የሚለውን በነሲብ ሳይሆን በነቢብ ቢያድርጉት መልካም ነው በሚል ዓላማ ይህ ጽሑፍ እንደ ምክረ ሐሳብ ቀርቧል።

የብዙኃን መገናኛዎች ሚና በጥቅሉ

በመሠረቱ የብዙኃን መገናኛዎች ሚና “ትርክት ማኖር” ነው። ዜና፣ ትንታኔ፣ ምርመራ፣ ማጋለጥ… ሁሉም አንድ ዓላማ አላቸው። በትርክት መብለጥ ነው። አንድ ጥሬ ሐቅ ከብዙ አንግሎች ‘ሪፖርት’ ሊደረግና ሊተነተን ይችላል። ሰዎች ያንን ጥሬ ሐቅ እንዴት መረዳት እንዳለባቸው የሚወስኑበት ደጋግመው ከሰሙት ወይም ደግሞ ይበልጥ ካሳመናቸው ትንታኔ አንፃር ነው። ስለዚህ ሁሉም ብዙኃን መገናኛዎች ዋነኛ ዓላማቸው ሐቁን ለዜጎች ማድረስ ነው ቢባልም ቅሉ፥ ዋናው ቁም ነገር ሐቁን የሚተነትኑበት መንገድ ነው።

ለምሳሌ ያክል የአድዋ ጦርነትን ብናስታውስ፣ ለኢትዮጵያውያን የምሥራች ሲሆን፥ ለጣሊያኖች ደግሞ መርዶ ነው። የጣሊያን ብዙኃን መገናኛዎች መርዶውን ለዜጎቻቸው ያደረሱት በቁጭት ሲሆን፣ ‘የተነተኑትም ለሽንፈት የዳረገን ምንድን ነው? ለወደፊቱስ ምን ማድረግ አለብን?’ በሚል ነው። በወቅቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ቢኖራት ኖሮ ትንታኔው በተቃራኒው ታቀርብ ነበር። ስለሆነም የብዙኃን መገናኛዎች የመጨረሻ ግብ ለቆሙለት ወገን ወይም ግብ ተሥማሚውን ‘ትርክት መፍጠር’ እና ያንን ትርክት ገዢ (mainstream) ማድረግ ነው።

Monday, August 8, 2016

ቋንቋችንን እንታዘበው

በፍቃዱ ኃይሉ

፩. Independence, Freedom, Liberty (ነጻነት የቱ ነው? የቱስ አይደለም?)

"ነጻነት ውስብስብ ነው" ብዬ ልጀምር።ነጻነትየሚለውን የአማርኛ ቃል በተለምዶ ከላይ የዘረዘርኳቸውን ሦስቱንም የእንግሊዝኛ ቃላት ለመተርጎም እንጠቀምበታለን። ትርጉሙ ግን ሁሌም አጥጋቢ አይሆንም።

ቃላት ባብዛኛው ደረቅ አይደሉም ፅንሰ-ሐሳብ (concept) ያዝላሉ። የሆነ ፅንሰ-ሐሳብን የሚወክሉ ቃላቶች በሆነ ቋንቋ ውስጥ የሉም ማለት የዚያ ፅንሰ-ሐሳብ በቋንቋው ተናጋሪው ማኅበረሰብ ዘንድ እምብዛም አይታወቅም እንደ ማለት ነው። ፅንሰ-ሐሳቡን በቃላት ቀንብቦ ማስቀመጥ መቻልና ብዙኃን በየለት ንግራቸው እንዲጠቀሙበት ማድረግ መቻል ቃሉን ከነፅንሰ-ሐሳቡ በማኅበረሰቡ ውስጥ ማስረፅ ማለት ነው። ይህንን ለማስረዳት ቀላሉ መንገድ የአየር ሁኔታን መግለጽ ነው። በረዶ (Ice) እና snow (የበረዶ ብናኝ እንበለው) ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፤ በአማርኛ ግን የሚጠሩት በአንድ ሥም - በረዶ - ተብለው ነው። Frost (snow ወይም የበረዶ ብናኝ የለበሰ ተራራ) አመዳይ ይባላል። በአገራችን የሌለ በመሆኑ ሥሙ የውሰት እና እምብዛም የማይታወቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ (መዝ 147: 16) ከመገኘቱ በቀር ቃሉም፣ ሐሳቡም በማኅበረሰቦቻችን ዘንድ የሌለ ነገር ነው። Tornado የሚለው ቃል የአማርኛ አቻ የለውም፤ ምክንያቱም በሐሳብ ደረጃም እምብዛም አይታወቅም። ሩቅ ምሥራቃውያን በየጊዜው ለሚያጠቃቸው የነፋስ እና የማዕበል ዓይነት (ነፋስን ከነፋስ፣ ማዕበልን ከማዕበል) የሚለዩባቸው እልፍ ቃላት አሏቸው። የቃላት እና ሐሳብ ቁርኝት እንዲህ ይገለጻል።

ኢትዮጵያ ውስጥነጻነትየሚለው ቃል እና ፅንሰ-ሐሳብ በአማርኛ ተናጋሪው ዘንድ እንዴት ነው እየታየ ያለው? መነባንቡ (rhetoric) ብቻ ነው ወይስ ግንዛቤውም አብሮት አለ? አብረን እንፈትሽ።

ምሳሌ ፩፦

A) Ethiopia is an independent country.
B) Zone 9 is an independent blogosphere.
C) She is an independent woman.

በሚሉት ሦስት /ነገሮች ውስጥ ‘independent’ የሚለው ቃል ሦስት ተለምዷዊ ትርጉሞች አሉት፣

) ኢትዮጵያ "ነጻ" አገር ናት።
) ዞን ነጻየጡመራ መድረክ ነው።
) እሷነጻሴት ናት።

ሦስቱ ቃላቶች በዐውድ (context) የተለያዩ ቢመስሉም በመሠረታቸው አንድ ናቸው። ሁሉም፣ማንም ላይ ጥገኛ ያልሆነ/ወይምራሱ/ሷን የቻለ/የሚለውን ሐሳብ ያዘሉ ናቸው። ነገርዬው በራስ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ወይም በሌሎች ጉዳይ ላይ አቋም ለመያዝ የማንም ተፅዕኖ የሌለበት እንደማለት ነው። መቶ በመቶ ራስን መቻል ወይም ከሌሎች ተፅዕኖ መላቀቅ የሚባል ነገር አለ ብዬ ባላምንም የሌሎችን በራስ ጉዳይ ጣልቃ ገብነት በእጅጉ መቀነስ መቻልንራስን መቻልብለን ብንጠራው አይከፋኝም። በላይኞቹ ምሳሌዎች ላይ ‘independence’ ራስን መቻል ወይም ገለልተኛ የሚሉት ቃላቶች ሊተኩት ይችላሉ።

Saturday, January 2, 2016

ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት እስከ ማበሳጨት

“ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ምንድን ነው? ማበሳጨትን ካላካተተ፣ ሕልውና የለውም፡፡” ~ ሰልማን ሩሽዲ

፩ - ማበሳጨት

‹‹በመስከረም ወር 1997፣ ዢላንድስ ፖስተን የተባለ የዴንማርክ ጋዜጣ ነብዩ መሐመድ ላይ የሚሳለቁ ካርቱኖችን ይዞ ወጣ፡፡ የዚህ ሕትመት ዜና በመላው ዓለም እንደተሰማ በየቦታው ያሉ ሙስሊሞች ቁጣቸውን በአደባባይ መግለጽ ጀመሩ፡፡ የተቃዋሚዎቹ ምክንያቶቻቸው ሁለት ናቸው፤ አንደኛ፣ ነብዩ መሐመድን በምስል መግለጽ በእስልምና ሃይማኖት አይፈቀድም የሚልና፤ ሁለተኛ፣ ካርቱኖቹ በጥቅሉ እስልምናን እና ሙስሊሞችን ከሽብር ጋር አቆራኝተው ይገልጻሉ የሚል ናቸው፡፡  ሠላማዊ ሰልፎችና ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በጋዜጣው አዘጋጆች እና በዴንማርክ መንግሥት ላይ ተቀሰቀሰ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሕይወት እስከመቅጠፍ የዘለቀ አመጽ የተቀላቀለባቸው የተቃውሞ ሰልፎች ነበሩ፡፡ ካርቱኖቹ ግን በመላው ዓለም በሚገኙ በሌሎች ጋዜጦች ላይ ለዢላንድስ ፖስተን ጋዜጠኞች የሞራል አጋርነት ለማሳየት በሚል ሰበብ ድጋሚ ታትመው ይበልጥ ተሰራጩ፡፡›› (Paul Sturges, 2006)

ሌላ ምሳሌ እንውሰድ፡፡ አንድ ወንድ “‹ሴቶችን ማስተማር የአገርን ሀብት ማባከን ነው፤ ስለዚህ ሴቶችን ማስተማር ካለብን የቤት አያያዝ፣ ምግብ ማብሰል እና ልጅ አስተዳደግ እናስተምር እንጂ ሌላ ‹የነጭ ኮሌታ› ሥራ የሚያስይዝ ትምህርት ማስተማር የለብንም› የሚል አስተያየት ሲሰጥ በቴሌቪዥን ተላለፈ፡፡ ይህን ተከትሎ የከተማው ሴቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ፡፡ ወንድ አሽከርካሪዎች የሚነዷቸውን መኪኖች ሰባበሩ፡፡ ወንዶችን እያሳደዱ ደበደቡ፡፡” በዚህ የፈጠራ ታሪክ ውስጥ የአስተያየት ሰጪው ሐሳብ ሴቶቹን አበሳጭቷቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለአመጹ እነርሱን አነሳስቷቸዋል ብሎ መደምደም ከባድ ይሆናል፡፡ አማጺዎቹ ሴቶች ስሜታቸውን መቆጣጠርና ሐሳቡን በሐሳብ መመከት ካልቻሉ ድክመቱ የነርሱ የራሳቸው ይሆናል፡፡

የዴንማርክ ፍርድቤት የፈረደውም፣ እኔ በላይኛው አንቀጽ አመጸኞቹ ሴቶች ላይ የሰጠሁትን ዓይነት ብይን ነው፡፡ “እርግጥ ነው ስዕሎቹ የተወሰኑ ሙስሊሞችን ማበሳጨታቸው አይካድም፤ነገር ግን የካርቱኖቹ ዓላማ ሙስሊሞችን ማንኳሰስ አልነበረም›› ብሏል ፍ/ቤቱ፡፡ ሲያብራራውም፣ “ስዕሎቹን አመጽ ወይም ቦንብ የመወርወር ድርጊት በእስልምና ሥም እየተደረገ ነው፤” በሚል መረዳት የካርቱኖቹ ተመልካቾች ድርሻ ነበር ብሏል፡፡ የዴንማርክ ፍርድ ቤት ብይን ለካርቱኒስቶቹ ያደላ ቢመስልም ካርቱኒስቶች ራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ክስተቱ አስገድዷቸዋል፡፡ ነገር ግን የአንድ ሐሳብ (expression) አንባቢ፣ ተመልካች ወይም አድማጭ የራሱን ስሜት መቆጣጠር ድርሻ የራሱ መሆን ካልቻለ ቢያንስ የሆነ ሰውን የማያበሳጭ ሐሳብ ማፍለቅ በጣም አስቸጋሪ ስለሚሆን፣ ‹በነጻ› ቀርቶ ሐሳብን መግለጽ የሚባለው ጉዳይ ራሱ አይኖርም፡፡

Saturday, December 19, 2015

“…ማን አለ እንዳንተ፣ ታማኝ?”



የሆነ ጊዜ የሰማኋት ቀልድ ትዝ አለችኝ፤ አንዳንድ የተቃዋሚ ተወካዮች ፓርላማ ውስጥ በነበሩበት በዚያ በደጉ ጊዜ ነው አሉ፡፡ አንድ ተወካይ የሻዕቢያ መንግሥት ላይ ሊደረግ ስለሚገባው እርምጃ ሲናገሩ እንዲህ አሉ፤ “አሁኑኑ ገብተን ድምጥማጣቸውን ማጥፋት አለብን፡፡ አለበለዚያ ካደሩ አይቆረጠሙም፤ እነዚያ ወያኔዎችም ያኔ ሲመሠረቱ ሳንጨፈልቃቸው ዝም ብለናቸው ነው ዛሬ አናታችን ላይ…” አሉና ያሉበት ቦታ ትዝ ሲላቸው ድንግጥ ብለው ወደአቶ መለስ መቀመጫ አማተሩ፡፡ አቶ መለስ በጥሞና ያዳምጣሉ፤ ተወካዩ እንደደነገጡ “…ልጨርሰው ወይስ ትጨርሰኛለህ?” አሉ ይባላል፡፡

የሕወሓት/ኢሕአዴግ ወታደሮች አዲስ አበባ ደርሰው “ሲቪል” መንግሥት ከመመሥረታቸው አስቀድሞ “እኩይ” ናቸው በሚል ሲቃወማቸው የነበረ እና እስካሁንም ስክነቱ ያልተለየው አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው፡፡ የታማኝ የአክቲቪስትነት ሪከርድ ከኮሜዲያንነቱ የሚመዘዝ ነው፡፡ በቀልዶቹ ቢጀምርም አሁን ግን በጣም ‹ሲሪዬስ› ነው፡፡ አሁን እነቪኦኤ፣ ዶቸ ቬሊ፣ ኢሳት በየቤቱ እንደሚደመጡት ከደርግ ማክተሚያ ቀደም ብሎ ብዙ ሰው በየቤቱ ‹ድምፂ ወያነ›ን በድብቅ ያደምጥ ነበር፡፡ የፕሮፓጋንዳ ሚዲያዎች አመል ነውና ያው ውሸታቸው አይጣል ነው፡፡ ታዲያ ታማኝ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቀርቦ የምሩን ሲቀልድ ‹እዚህ ቦታ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር፣ እዚያ ቦታ ደግሞ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር ደመሰስን ይላሉ፡፡ ሲደመር ግን ይሄን ያክላል፡፡ ቆይ እኔ የምለው ወያኔዎቹ የሚደመስሱት ጦር ከጠቅላላ ጦሩ በለጠ እኮ፤ ከየት እያመጡ ነው የሚደመስሱት?› ዓይነት ቀልድ ተናግሮ አላገጠባቸው፡፡ ከዚያ በድምፂ ወያነ መልስ ተሰጠው፤ “ቁጥሩን አዲስ አበባ ስንደርስ እናወራርዳለን” የሚል፡፡ ዛቻ የሽፍትነት ዘመንም አመል ነበረች፡፡

ግንቦት 20/1983 - ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲረግጥ፣ ሲ ኤን ኤን ካነጋገራቸው ሰዎች አንዱ ታማኝ በየነ ነበር፡፡ “በመሣሪያ ተከበናል፣ ምንም ሠላም የለም…” የሚል ነገር ለጋዜጠኛው ሲነግረው ይታያል፡፡ ታዲያ ታማኝ ሁኔታውን በቀልድ ሲያስታውስ “ጓደኞቼ ከውጪ ደውለው ‹ሲ ኤን ኤን› ላይ አየንህ ሲሉኝ፣ ወዲያውኑ እንግሊዝኛዬ እንዴት ነበር?” አልኳቸው ይላል፡፡

ታማኝ ከአዲሱ ስርዓት ጋር አብሮ መኖር በማይችልበት ሁኔታ የተቀያየመው፣ ካልተሳሳትኩ የወቅቱ ባለሥልጣናት፣ እነታምራት ላይኔ በተገኙበት ስታዲዬም ውስጥ በቀለደው ቀልድ ነው፡፡ እንደማስታውሰው ቀልዱ በማንነት ላይ የተመሠረተ እና ለኢሕአዴግ የማንነት ብያኔ የማይበገር ዓይነት ቀልድ ነው፡፡

Monday, March 24, 2014

‘Blame the Victim’: The Quest for Freedom vs. Professionalism of Media in Ethiopia?



16th of March 2014 marks the 1000th day since Reeyot Alemu, a newspaper columnist and teacher, was arrested for working to ethiopianreview.com news website which the Ethiopian State/court called ‘supporting terrorism’. On the same day, a twitter discussion focused on what happened to weaken the Ethiopian Press. Soleyana Shimeles, an activist for human rights and constitutional order, commented that the State ‘blames the victim after deliberately weakened the Press’. However, a twitter discussion following her tweet revealed that it is not only the State that blames the victim. Many ‘activists’ do. 


A Short Story of the Press

It is the same regime, the current regime, which created the Free Press and then tried to kill it. It is not dead yet; but it is also hardly possible to say it is alive. Researchers (Terje and Hallelujah, 2009) put the history of the Free Press in the past two decades in three overlapping periods:  

“…Tafari and others draw three periods of the private press in Ethiopia. The first period was the chaotic period from 1991 to 1997 with a blooming of new newspapers and anarchy journalism. The second period, 1997-2005 saw the establishment of professionally and ethically integrated newspapers like Reporter, Addis Admas, Fortune and Capital. The last period goes from 2005 when press freedom again came under threat after editors and journalists were imprisoned and persecuted after alleged transgressions following the May 2005 elections…” 

If the paper, from which the above excerpt was taken, was written now there would be a fourth period too – we may call it a counter-attack period! The current Press, however is mostly led by different people from the media leaders who existed pre-2005, it is now trying to counter attack (in becoming too critical of the State in its own way) past the self-defense time that followed its threat after the contested election in 2005.


Elections have become nightmares of the independent media. Even though the Press tried to recover from its wound of post 2005 election, the Ethiopian State planned to narrow the sphere to clear way for the 2010 election: the penal code was revised in relation to Free Press issues; the anti-terrorism bill, which clearly puts Freedom of Expression in danger, passed; the highly emerging Addis Neger newspaper journalists were intimidated to have eventually exiled; other journalists and bloggers were prosecuted in relation to terrorism; a few media houses such as Addis Admass took measures to toned down choosing existence over professional integrity. 

Saturday, January 18, 2014

የአዲስ ዘመን “አዝማሚያ ጥናት” አዝማሚያ


አዲስ ዘመን ጋዜጣ (በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በሕግ ይፍረስ ተብሎ ያልፈረሰው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር ተሰርቷል ያለውን) ጥናት፣ በፊት ገፁ ላይ፣ ባለፈው ረቡዕ ይዞ ወጥቶነበር፡፡ ጥናቱ፣ እንደአዲስ ዘመን አገላለጽ ‹‹የአዝማሚያ ጥናት›› ነው፡፡ ከዚህ በፊት የአዝማሚያ ጥናት የሚባል ነገር ሰምቼ አላውቅም፡፡ በእንግሊዝኛም ፈልጌ ስላጣሁት አገር በቀል የጥናት ዓይነት ሊሆን ይችላል ብዬ በደንብ አነበብኩት፡፡ ከአነበብኩት የተረዳሁት ነገር ቢኖር ‹የመጽሔቶቹ ጽሑፍ አዝማሚያ ምንድን ነው?› የሚለውን ለማጣራት የተደረገ ሙከራ እንደሆነ ነው፤ እናም እኔም በበኩሌ የጥናቱን (ጥናት ከሆነ) አዝማሚያ ምን እንደሚሆን ለመመርመር ደግሜ አነበብኩት፡፡

የዜናው የመጀመሪያው አንቀጽ እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹በኢትዮጵያ ከሚታተሙት መጽሔቶች መካከል ሰባቱ ‹በብዙ ባሕሪያቸው የጽንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሳን መሆናቸው፣ በተሳሳቱ መረጃዎች ይዘት ሕዝቡ በሥርዓቱ ላይ እምነት አጥቶ ለአመጽ እንዲነሳሳ የሚያደርጉ ዘገባዎች ይቀርባሉ› ሲል አንድ የአዝማሚያ ጥናት አመለከተ፡፡…››

‹‹ጽንፈኛ›› ተብለው የተመረጡት ሰባቱ ከነማን ጋር ተወዳድረው እንደሆነ አይገልጽም፤ ሰባቱ ግን አዲስ ጉዳይ፣ ፋክት፣ ሎሚ፣ ቆንጆ፣ ጃኖ፣ ዕንቁና ሊያ ናቸው፡፡ ‹‹ጥናቱ›› ከመስከረም 1/2006 እስከ ኅዳር 30/2006 ለሦስት ወር ዘልቋል ይላል፡፡ ‹‹የአዝማሚያ ትንታኔ›› እያለ የሚጠራው ትንታኔ ግን ጋዜጣው መጽሔቶቹን በገዢው ፓርቲ መነጽሩ ዓይቶ ከመዳኘቱ በስተቀር በቅጡ ለሦስት ቀን ታስቦበት የተጻፈ አይመስልም፡፡

Thursday, January 2, 2014

የኢትዮጵያ የጋዜጠኛ ማኅበራት = የመንግሥት ገደል ማሚቶዎች?



“ሲፒጄ የሃገራችንን ስም ለማጥፋት ስለሚፈልግ ነው እንጂ፣ በጻፈው ጽሑፍ የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ የለም፡፡ 3 ጋዜጠኞች የታሠሩት አሸባሪ ተብለው ነው” ~ አቶ አንተነህ አብርሃም (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት /ኢብጋኅ/ ፕሬዚደንት)

“[ሲፒጄ] ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛ ናት ብሏል፡፡ ይሄ ከዚህ በፊትም ሆኖ የማያውቅ ግነት ነው፡፡ የታሰረ የለም።” ~ አቶ ወንደወሰን መኮንን (የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማኅበር /ኢነጋማ/ ሊቀመንበር)

“በጻፈው ተፈርዶበት የታሰረ አለ ከተባለ ዶክመንቶችን ማገላበጥ ያስፈልጋል፡፡ ማንም ደግሞ አልታሰረም። ይህ አልሆነም፡፡ ከምላሴ ላይ ፀጉር ይነቀላል፡፡” ~ አቶ ሽመልስ ከማል (የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ)

ከላይ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ከወጣ ቃላቸው ቀንጭቤ ያስነበብኳችሁ አስተያየቶች ውስጥ ምንም ዓይነት መሠረታዊ ልዩነት የለም፡፡ ነገር ግን አንዱ በመንግሥት ባለሥልጣን እና የቀደሙት ሁለቱ ደግሞ የጋዜጠኞችን ጥቅም ለማስጠበቅ በጋዜጠኞች ስም ከተመሠረቱ ማኅበራት ኃላፊዎች የተደመጡ ንግግሮች ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ስምንት የጋዜጠኞች ማኅበራት ሲኖሩ ሦስቱ እንደአካባቢና ጤና ባሉ የተለዩ ጉዳዮች ላይ ብቻ አተኩረው የሚሠሩ ሲሆን ቀሪዎቹ የተለያዩ ጋዜጠኞችን እንወክላለን በሚል የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ሆኖም በአብዛኛው ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር ጋብቻ በመፈፀም የመንግሥትን (የገዢውን ፓርቲ) ጥቅም በማስጠበቅ ሥራ ላይ ተሰማርተው እናገኛቸዋለን፡፡ በመሀከላቸው ፉክክር ቢኖር እንኳን ለማኅበራቱ መሪዎች ጥቅም እንጂ በጋዜጠኞች ጥቅም ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ማኅበራቱ አንዳንዶቹ የአሳታሚ ድርጅቶች ባለቤቶች በመሆናቸው መንግሥት ድርጅታቸውን እንዳይጣላባቸው ሲሉ ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን በደል በሙሉ አፍ ማጋለጥ አይደፍሩም፡፡ ሌሎቹ አሉን የሚሏቸው አባላት ቢኖሯቸው እንኳን የማኅበሩ አባላት የሚያገኙት ጥቅም የላቸውም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ጭራሹኑ እራሳቸው ለጋዜጠኞቹ ደኅንነት አደጋ ናቸው፡፡

Thursday, December 12, 2013

A New Journalists Association is Under-formation in Ethiopia



There are about eight journalists and media related associations in Ethiopia. None of them, however, have been heard speaking out for either jailed or exiled journalists. Ethiopia is one of the highest jailor of journalists (CPJ, names it 2nd where as Addis Standard, a local media, named it 3rd in its December issue). According to Article 19, twelve Ethiopian journalists are prosecuted in “relation to terrorism”. On the other hand, one of the famous “journalists association” – Ethiopian National Journalists Union (ENJU – IFJ member) president, Anteneh Abrham told Ethiopian Radio and Television Agency that he feels proud that Ethiopia hasn’t jailed any journalist for what s/he has written.

The Press Release (Amharic)
It is in this time of despair a committee of eight independent journalists initiated a formation of a new “Ethiopian Journalists Forum (EJF)”. The committee called for ‘founding meeting’ today, Dec 12/2013 at Ethiopian Hotel where more than 20 journalists attended. 

The committee, in its presser, mentioned that ‘the Forum under-formation will independently work to support and upgrade the professionalism of journalists in particular and the media in general’.  It also added that its goals include working:

The Return to Rule by Law: The Case of Draft CSO Law in Ethiopia

(Befekadu Hailu) [The original version of this piece is written in Amharic; please read the Amharic version for accuracy.] The Ministry...