Pages

Monday, September 30, 2013

Ethiopia’s UDJ Public Demonstration Got Its Route Blocked By Police; Protest Held Anyway!



ON SEPTEMBER 29, 2013 major opposition party of Ethiopia, UDJ (Unity for Democracy and Justice), in collaboration with the coalition of 33 political parties held a brief public demonstration in protest against the controversial Anti-Terrorism Proclamation No. 652/2009 and other human and democratic rights violations. The demonstration was called as a closure to the party’s three months long campaign titled “Millions of Voices for Freedom”.

The demonstration got its route blocked by police in the very beginning however thousands of demonstrators could chant their oppositions in the spot where it was started. Many applauded these demonstrators for they took risk to face the infamous brutality of police in Ethiopia and kept themselves peaceful until the dispersion of the gathering.  

Police blocked the demonstration route to Mesqel square reasoning out that Mesqel square is under construction of the city railroad. This, however, didn’t satisfy the organizers of the demonstration because the square hosted a demonstration called by Union of Religious Institution and Ministry of Federal Affairs a month ago as well as another religious event called Mesqel where hundreds of thousands people attended just three days before this demonstration was called.

The government officials instead suggested the demonstration to be held in a compound known as ‘Janmeda’ which is a few kilometers away from the head office of UDJ. The organizers refused to accept that proposal mentioning the fact that the compound is 100 meters away from a military camp and that according to Demonstration Proclamation No. 003/1991 Article 7/2 – which enforces demonstrations to be held at least 500 meters away from any military camp.

Tuesday, September 24, 2013

የ‘ያ ትውልድ’ መጽሐፍ ማሳተም ለ‘ይህ ትውልድ’ ምኑ ነው?

ከክፍሉ ታደሰ መጽሐፍ በመዋስ በተለምዶ ‘ያ ትውልድ’ እያልን የምንጠራው ትውልድ በ1966ቱ አብዮት ወቅት ወጣት የነበረውን ትውልድ ነው። አሁን በቅርቡ ከተጻፉት ውስጥ፣ (1) ዻንዲ — የነጋሶ መንገድ፤ (2) ሕይወት ተፈራ —   ‘Tower in The Sky’፤ (3) ዶ/ር መረራ ጉዺና — ‘የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች’፤ (4) ኢ/ር ኃይሉ ሻወል — ‘ሕይወቴና የፖለቲካ እርምጀዬ’ (?)፤ (5) ቡልቻ ዸመቅሳ—  My Life and My Vision ይገኙበታል። እዚህ ውስጥ ያልጠቃቀስኳቸውም ሌሎችም ብዙ አሉ። ሆኖም ማውራት ለምፈልገው የጠቀስኳቸው ይበቁኛል።

ከጠቀስኳቸው የ‘ያ ትውልድ’ ጸሐፍት ውስጥ የአሁኑ ፖለቲካ ውስጥ የሌለችው ሕይወት ተፈራ ብቻ ነች። ሆኖም ሁሉም የሚጋሩት አንድ ነገር ያለ ይመስለኛል፤ የ‘ያ ትውልድ’ ፀሐይ እየጠለቀች መሆኑን በማመናቸው። ይህን ማመናቸውን በግምት ነው የምናገረው። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ የሕይወት ልምድን ማጋራቶች አንድም ከእርምጃዎቻቸውና ስህተቶቻቸው እንድንማር፣ አሊያም ደግሞ ሕልሞቻቸውን ከግብ እንድናደርስ ነው። የተጻፉት መጽሐፍት በቂ ባይሆኑም ‘ይህ ትውልድ’ ግን ያለበቂ ትምህርትም ቢሆን አገሪቱ እጁ ላይ መውደቋ አይቀርም። ትውልዱ ይህን አውቆ ተዘጋጅቷል?

“እናቸንፋለን” ወይስ “እናሸንፋለን”?

መጽሐፍ እየጻፈ ያለው ‘ያ ትውልድ’ ብቻ ሳይሆን ‘ይህ ትውልድ’ም ጭምር ነው። (ይህ ትውልድ የምለው ከሀያዎቹ አጋማሽ እስከአርባዎቹ አጋማሽ ያለውን ነው።) ለምሳሌ የልደቱ አያሌው ‘ሦስተኛው አማራጭ’፣ የግርማ ሰይፉ ‘የነፃነት ዋጋው ስንት ነው?’፣ የአንዱዓለም አራጌ ‘ያልተኬደበት መንገድ’ እና ሌሎችም እየወጡ ነው። የነዚህኞቹ ከነዛኞቹ የሚለየው አማራጭ መንገዶች ማመላከት ላይ ወይም ያልተኬደበትን መንገድ ማፈላለግ/ማመላከት ላይ ያተኩራል። የተሄደበትን ከያኛው፣ ያልተሄደበትን በይህኛው ማለት ነው።

‘ይህ ትውልድ’ ከ‘ያ ትውልድ’ ስህተት መውሰድ የሚገባው የመጀመሪያው ትምህርት በጥቂት ልዩነት ጎራ ለይቶ አለመቀጣቀጥን ነው ባይ ነኝ። ‘ያ ትውልድ’ በአንድ ርዕዮተ ዓለም፣ በአንድ ዓይነት ሕልም በቃላት አጠቃቀም ውስጥ ለውስጥ በአንጃነትና በሌላም በሌላም ሲከፋፈልና ሲቆራቆዝ እዚህ ደርሷል —  ቢያንስ እስከ ምርጫ 97። ልዩነትን አቻችሎና ተወያይቶ የመፍታት፣ ከነልዩነትም ቢሆን  (ከ“እናቸንፋለን”፣ “እናሸንፋለን” ዓይነት ትናንሽ የቃላትና አተረጓጎም ልዩነት ይልቅ) በዋነኛ አገራዊ ጉዳዮች (ዴሞክራሲ ማምጣት፣ ድህነትን ማጥፋት… የመሳሰሉት) ላይ ማተኮር ያስፈልጋል።
“እኔ ያልኩት ካልሆነ” የሚለው የቃል ሐረግ ካልሞተ የ‘ያ ትውልድ’ ፀሐይ ብትጠልቅም የ‘ይህ ትውልድ’ ፀሐይ አትወጣም።

እናሸንፋለንም፣ እናቸንፋለንም

አንተ ወይም እኔ (እኔ ወይም ሞት) ሞቷል። አሁን ያለው አማራጭ እኔንም አንተንም አካታች የሆነ አማራጭ ብቻ ነው፤ አንዱ ሲያሸንፍ/ሲያቸንፍ ሌላው የማያጎድልበት፣ ሁሉም የሚያሸንፍበት/የሚያቸንፍበት ነው።

ይሄ ትውልድ በኔ እምነት ከያ ትውልድ ይሻላል። በቀኖና የሚነገሩት የ‘ያ ትውልድ’ ድርሳናት ‘ይህን ትውልድ’ የሚያጣጥሉት በያ ትውልድ መለኪያ እየመዘኑት ነው። ይህ ትውልድ የራሱ መንገድ አለው ብዬ አምናለሁ።  ስለአንባቢነት የሚወራውም ቢሆን ተጨባጩን እውነታ ያላገናዘበ ብዥታ ነው ብዬ የምረዳው። ብዙኃኑ ያኔም ሆነ አሁን ኖሮ አላፊ ነው። ልሒቁ ነው ለውጥ የሚያመጣው። ማንም ማንንም የማያጠፋበት የለውጥ መንገድ ደግሞ በዚህ ትውልድ እጅ አለ ብዬ አምናለሁ።
መልካም የለውጥ መንገድ!

Monday, September 16, 2013

#Ethiopia has a prison-in-a-prison for its journalists



Ethiopian government is the only government of our planet that has prosecuted 12 journalists in relation to ‘terrorism’ and yet says ‘there is no journalist jailed for what it has written’. A teacher and Journalist Reeyot Alemu, is one of these convicted journalists in “supporting terrorism”. She was accused for taking pictures of graffiti (the word ‘beqa’ (enough) written in a street wall - that is said by the government ‘were written to incite terrorism’) and sending them to Ethiopian Review, a website where she worked as a reporter and owned by an Ethiopian diaspora, Elias Kifle (who himself is convicted in absentia).

I had gone to Kality to visit Reeyot Alemu on August 26, 2013 and I joined her sister, Eskedar Alemu, right at the door of Kality prison. One of the door guards told us that only relatives are allowed to visit Reeyot. We argued a little and she let us pass. We have explained the incident to Reeyot. She then told us that she was also under pressure from the prison officials enforcing her to list names of her visitors. Her eyes were shading tears when she said:

“No, I can’t. I can’t because my visitors are not only family and relatives. I have many friends who visit me every time and it is my constitutional right to be visited by every one of them. I told them I won’t be visited by anyone if everyone is not allowed to…”

15 days later, on the eve of Ethiopian New year – Sep. 10, 2013, the news that Reeyot Alemu went on hunger strike came out. Her strike was a reaction to the restrictions of visitors. “She was told that either of her father, mother or her ‘God father’ would be the only people who are allowed to visit her”, says Eskedar; even her fiancé, Sileshi Hagos, and other family members are not allowed to.

The same had happened to journalist Eskinder Nega. For more than two years, he was given only a ‘piece’ of his right to be visited by his wife and child but no one else. Now, he once again is granted back his rights of being visited by anyone since a few months ago. However, there is no reason uncovered about either the prior restriction or recent permission of visitors to him.

Tuesday, September 10, 2013

2005 ቢደገም አልጠላም!


ዓመት በመጣ ቁጥር የግል ስኬቴን የምመዘግብበትና ዓመቱ ሲያልቅ የምለካበት አጭር ጽሑፍ አዘጋጃለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ከመቶ 40 እንኳን አይሳካልኝም፡፡ በሌላ ጽሑፍ በተረክኩት የመታሰር ገጠመኜ (…የቀይ ለባሾቹ ውሎና አዳር…) ፖሊሶች ወስደው ካስቀሩብኝ ብጭቅጫቂ ወረቀቶች መካከል የ2005 ዕቅዴ ይገኝበታል፡፡ በዚህ መሠረት ዓመቱ ቢደገም የማልጠላው አንድም የተሳካ ስለመሰለኝ፣ አሊያም አለመሳካቱን መለኪያ ስለሌለኝ ይሆናል ማለት ነው፡፡

2005 ብዙ የማኅበራዊ አውታር ወዳጆቼ እንደተስማሙበት አስተማሪ ነበር፡፡ እንዲያውም አንድ ወዳጄ እንዳለው ‹‹የዘንድሮው ማንነትህ፣ የአምናውን ቢያገኘው ተበሳጭቶበት በጥፊ ይመታዋል፡፡›› ማኅበራዊ አውታሮች (በተለይም ፌስቡክ) በኢትዮጵያ ወቅታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሞቀ ሙግት በማስነሳት የአስተሳሰብ እና የውይይት ልምዳችንን ይሞግቱታል፡፡ ፌስቡክ ሰዎች በሙሉ ዕኩል ቢሆኑ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ማሳያ መሣሪያ እየሆነ ነው፡፡ ስንቶች በጥንቃቄና በስንት ልፋት የገነቡት በአንዲት ቃል የሚፈርስበት፣ ስንቶች ሊያፈርሱት የደከሙለት በሌላ አንድ ቃል የሚገነባበት መድረክ ነው፡፡ የሕዝባችን ጥንካሬም ድክመትም የሚስተዋልበት ገጽ ነው፡፡ ፌስቡክ ብስጭታችንን ማደቢያ (anger management) ትምህርት ቤት ነው፡፡ እውነቱም፣ ሐሰቱም ገዝፎ የሚታይበት ዓለም ነው፡፡ ፌስቡክ ከነድክመቱም ቢሆን መደበኛውን መገናኛ ብዙኃን (mainstream media) አጀንዳ እየሰጠ ይመግበው ጀምሯል፡፡