Skip to main content

የታክሲዎች የጨረባ ተስካር እና የኔ ብስጭቶች

ጉዳዩ ‘ሲሪዬስ’ ነው፤ በተለይ በአዲስ አበባ። ግን ማንም ደንታ የሰጠው አይመስልም። ዘርፈ ብዙ የትራንስፖርት አገልግሎት ችግሮች በምሬታችን ላይ ምሬት እየጨመሩ ነው። ኪሳራውን ግን እስካሁን አላሰላነውም። ለምን ይህን ጽሑፍ ከአንዲት ወዳጄጋ ሰሞኑን በሰራነው ግምታዊ (ወይም ግብታዊ) ስሌት አንጀምረውም።

አዲስ አበባ ውስጥ ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ሠራተኞች አሉ። ከዚያ ውስጥ በቃ 50ሺሕዎቹ ብቻ በትራንስፖርት ችግር አንድ ሰዓት አረፈዱ እንበል፤ 50ሺሕ የሥራ ሰዓት ባከነ ማለት አይደለም? በቀኑ የሥራ ሰዓት 8 ስናካፍለው  በድምሩ በየቀኑ 6,250 ሰው ከሥራው እንደቀረ (ወይም 6,250 የሥራ ቀናት እንደባከኑ) መቁጠር ይቻላል። በዓመት አስሉትማ!

ዛሬን እየኖሩ ስለነገ ስርዓት መያዝ መጨነቅ ይቻላል?

እኛ ሰፈር ጠዋት፣ ጠዋት ከወትሮው የከፋ የታክሲ እጥረትና ትርምስ ካለ፥ ትራፊክ ፖሊስ በአካባቢው አለ ማለት ነው። ታክሲዎቹ ትርፍ ሰው የሚጭኑት ትራፊክ ፖሊስ ሳይኖር ብቻ በመሆኑ የሥራ ሰዓት እና ቀጠሮ የረፈደበት ሰው ትራፊክ  ፖሊሶቹን ሲያይ እንደስርዓት አስከባሪ ሳይሆን እንደ ችግር ፈጣሪ ባይመለከታቸው ይገርማል።

ጠዋትና ማታ (የሥራ መውጫና መግቢያ ሰዓቶች ላይ) የትራንስፖርት አማራጮቹ አቅም ከትራንስፖርት ፈላጊዎቹ ቁጥርጋ አይጣጣምም። ስለዚህ ምንም እንኳን ለትራንስፖርት ዘርፉ ስርዓት መያዝ ሲባል የትራፊክ ሕግጋቱን ማክበር አስፈላጊ ቢሆንም ዛሬን ለመኖር ሲባል አገልግሎት  ጪዎቹም ሆኑ ተገልጋዮቹ ተባብረው ስርዓቱን ይጥሳሉ። ስርዓቱን የመጣሱ ነገር ወደባሕልነት ሊያድግ የሚችል  መሆኑ አሁን የሚያስጨንቀው ሰው የለም።

“200 ሺሕ ብር ያለው ሰው የሚያሾረው ኢንደስትሪ"

አንድ እሁድ ከምሽቱ 2:30 ላይ ቦሌ ቆሜ የአራት ኪሎ ታክሲ እየጠበቅኩ ነበር። ያለወትሮው አካባቢው በጊዜ ጭር አለብኝ። ታክሲ ያገኘሁት ከአንድ ሰዓት ጥበቃ በኋላ ነበር — ያውም አቆራርጬ! አራት ኪሎን ስሄድ ያው ሆነብኝ። ከዚያ እንደኔው ታክሲ የቸገረው መንገደኛ ምስጢሩን ነገረኝ —  “ዛሬ እኮ ማንቼ ደርቢ ስላለበት ነው” በማለት። ለካስ የታክሲ ሾፌሮችና ረዳቶች ኳስ ለማየት ሥራ በጊዜ እየጨረሱ ገብተው ነው። ይሄኔ ነበር አንድ ወዳጄ ሁሌም የሚናገራት ነገር ትዝ ያለችኝ፤ “ሁለት መቶ ሺሕ ብር ያለው ሰው የሚቆጣጠረው የትራንስፖርት ኢንደስትሪ”።

ግለሰቦች የየራሳቸውን ታክሲ እየገዙ እንደፈለጉ ይሠሩበታል ካልፈለጉ ሥራ ያስፈቱታል። የገዛ ንብረታቸው ስለሆነ መብታቸው ነው።  ችግሩ በዘርፉ ስርዓት ያላቸው ማኅበራት እንዲኖሩ መንግሥታዊ ማበረታቻም ሆነ ግልጽ አቅጣጫ አለመኖሩ ነው። አሊያንስ ባስ ሥራ ሲጀምር ደስ ያለኝ በዚያ ተስፋ ነው። ቢያንስ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሳቢያ አገልግሎቱ አይቋረጥም።

ስርዓቱን በየቀኑ እየተደባደቡ/እየተደበደቡ ማስከበር ይቻላል?

የአዲስ አበባ ትራፊክ ጽ/ቤት ሁሉም ታክሲዎች የሚንቀሳቀሱበትን አካባቢ ታሪፍ በይፋ እንዲለጥፉ የሚያዝ መመሪያ አለው። ባለታክሲዎቹ ግን አይተገብሩትም።

ለምሳሌ ከአራት ኪሎ አምባሳደር እና መልስ ዋጋው በመመሪያው መሰረት ዕኩል 1·35 ቢሆንም ስንመለስ ዳገት ነው በሚል ባለታክሲዎቹ 2·70 ይጠይቃሉ። አንድ ተሳፋሪ ‘የለም ዋጋው ይሄ አይደለም፣ አልከፍልም’ ካለ ያለው ዕድል ሁለት ነው፤ ወይ ወርዶ በእግር መሄድ አሊያም መደባደብ። መደባደብ ውስጥ መደብደብም አለ። ለአንድ ቀን አይደለም፣ በየቀኑ።

አንዳንዶች የተሳፋሪውን ተባብሮ አለማደም ተጠያቂ ያደርጋሉ። ስንት ዓይነት ተሳፋሪ አለ? ስንት አንገብጋቢ ጉዳይ ያለበት አለ? ዛሬ ብቻ የመጣ አለ? በየሄደበት በታክሲዎች ለማደም እየተባበረ ዕድሜና ግዜውን ሊያባክን አይችልም። ሁሉም ሰው ብዙ ኑሮ አለበት። ይህንን ስርዓት ለማስከበር ደሞዝ የሚከፈላቸው የምር፣ ለሕዝቡ በሚበጅ መልኩ ማስከበር አለባቸው።

ስርዓቱን ለማስከበር ስርዓቱ የሚፈልገውን ሟሟላትም ያስፈልጋል። በርካታ የሕዝብ ማመላለሻ አማራጮች፣ የባቡርም ይሁን አውራ ጎዳና ግንባታ/እድሳት ገድሎ የማይገድለው አማራጭ መንገድ፣… ከልብ  መታሰብ አለበት። ምክንያቱም በመሐል ቤት ዜጎች እየተጨፈለቁ ነው።

Comments

Popular posts from this blog

The "Corridor Development" is a Façade of the Prosperity Party

Befekadu Hailu I have seen a news report claiming that 40% of central Addis Ababa will be demolished for the corridor development; I am not able to confirm the validity of the news but it sounds real to me given the size of massive operations in the demolition of old neighborhoods and construction of bike lanes, green areas, and glittering street lights. I like to see some beauty added to my city but cannot help mourning the slow death of it too. Addis Ababa was already in a huge crisis of housing and the demolition of houses is exacerbating it. Apparently, Prime Minister Abiy Ahmed is eager to showcase his vision of prosperity by demonstrating how fast his administration can do magic by beautifying the front sides of the streets with lights, new pavements, and painted fences ("to fake it until he makes it" in my friend's words). Therefore, he and his party do not care about the miserable human stories behind the scenes and they will harass you if you tell it (Azeb Woku...

መጽሐፍ የሚወጣው፣ የተዋነይ ዘ ጎንጅ 5 መሥመር ቅኔ

ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል። “የአምን ወይገኒ ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ።” (ተዋነይ ዘ ጎንጅ። ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ) ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን ...

የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ

በፍቃዱ ዘ . ኃይሉ “የአዲስ አበባ ብሔርተኝነት” ቢኖር ኖሮ መሪው ልጅ ሚካኤል ይሆን ነበር። አሁን አሁን እሱ ስለ አዲስ አበባ የዘፈናቸውን ዘፈኖች ቁጥር ራሱ በትክክል መቁጠር ይቸግረኛል። ለአዲስ አበባ ከተዘፈኑ ዘፈኖቹ ውጪም በየዘፈኑ ውስጥ የሚጨማምራቸው መልዕክቶች በራሳቸው መወድሰ አዲስ አበባ ናቸው። ለምሳሌ፣ በቅርቡ በለቀቀው ‘አዲስ አራዳ’ በተሰኘው አልበሙ ውስጥ ‘የድሬ ልጅ’ የሚል ዘፈን አለው። ዘፈኑ የተዘጋጀው ያው የአዲስ አበባ እህት ተደርጋ የምትቆጠረውን ድሬ ዳዋን ለማወደስ ነበር። ልጅ ሚካኤል ግን የአዲስ አበባ ፍቅሩ ያመልጠውና የሚከተለውን ያቀነቅናል፦ “መጣልሽ በሏት፣ ድሬ ድረስ፣  ከአዱ ገነት፣ ከሸገር፣ ከአዲስ ደረሰ፣... የሸገር ልጅ አራዳ ነው፣ ሰው አክባሪ፣ ሰው ወዳዱ፣ ቀላጅና ተረበኛ፣ ፍቅር ይዞ የሚተኛ፣ ‘አለው’ የለ፣ ‘የለው’ የለ፣ ከሁሉ ጋ፣ ግባ ጀባ...፤” ፤ ልጅ ሚካኤል በዚህ አልበሙ ብቻ አዲስ አበባን የሚያውድሰባቸው ሌሎችም ዘፈኖች አሉ፤ ‘ አዲስ አራዳ ’ የሚለው የአልበሙ መጠሪያ እና ‘ሸገር’ የሚሉት ዘፈኖቹ ዋነኞቹ ናቸው። ታዲያ እንዲህ በአዲስ አበባ ፍቅር የሚቃጠለው ልጅ ሚካኤል "ሊነግረን የሚፈልገው ምንድን ነው?" የሚለው ጥያቄ ደጋግሞ ይመጣብኛል። ይህ የልጅ ሚካኤል አዲስ አበባ ምንነትን ለመረዳት የሚጥር ፖለቲካዊ መጣጥፍ ነው። ‘አዲሱ አራዳ’ ማነው? በዚህ ዘፈኑ በብዙዎቻችን ዕድሜ የትዝታ ማኅደር ውስጥ የሚገኙ ነገር ግን በአዲስ አበባ ልማት ሥም የፈረሱ እና እየተረሱ ያሉ ሰፈሮችን ሥም ያነሳሳል። ዘፈኑ በግጥሙም በዜማውም፣ የሐዘን እንጉርጉሮ ያለበት ነው። ምሳሌ እንውሰድ፦ “ጨርሰሽ ስትወጪ ከቡፌ ዳ’ላጋ፣ ጠብቂኝ እንዳልል፣ ቆመሽ መሐሙድ’ጋ፣ አገር ...