ፎቶዎች ከቃላት በላይ ይናገራሉ እንዲሉ ባለፈው ዓመት ወዲያ ወዲህ ስል መንገዴ ላይ አጋጥመውኝ ካነሳኋቸው ፎቶዎች ላካፍላችሁ ወደድኩ:: እነሆ:-
![]() |
| አራት ኪሎ የፈረሱት ሰፈር አካባቢ ነው:: ጽሑፉ "ስለቀኑብን አፈረሱብን" ይላል:: ይህን ፎቶ ያነሳሁት አምና ነው:: አሁን በቀይ ቀለም ተሰርዟል:: |
![]() |
| ድርጅቱ በመስተንግዷቸው ከምናደንቃቸው አንዱ ቡና ሻጭ ካፌ ነው:: |
![]() |
| ከኢምፔሪያል ሆቴል ወደቦሌ ለመሄድ አንዳንዴ ከመኪና ይልቅ በጀልባ ይቀላል:: |
![]() |
| ፒያሳ - ራስ መኮንን ግርጌ |
![]() |
የቴኒክ ብልሽት:- መጽሔቱ በአንድ እትሙ ሽፋን ገጹ
ላይ ኢትዮጵያ ከስንዴ ኢምፖርት አድራጊነት አልተላቀቀችም ይላል፡፡ የውስጥ ገጹን ጽሑፍ ደግሞ በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፡፡
|
![]() |
| የቴኒክ ብልሽት (ቀጣይ):- መጽሔቱ በውስጥ ገጹ ላይ ኢትዮጵያ ከስንዴ ኤክስፖርት አድራጊነት አልተላቀቀችም ይላል፡፡ (የሽፋን ገጹን ጽሑፍ ከላይ ይመልከቱ፡፡) |
![]() |
| Not Yet Arrived in 2014. In front of Bole Friendship Building |
![]() |
| ሁሉም ሰዎች አንድ ጋዜጣ (ልዕልና ከመታገዱ በፊት) - አሁን እነዚህ ካፌዎች በረንዳቸው ላይ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል:: |
![]() |
| ይህ ማስታውቂያ ተዘቅዝቆ ነው ወይስ ተልጦ ወይስ ግራ ቀኝ ተዛውሮ ወይስ ሁሉም? (ራስ መኮንን አለፍ ብሎ) |
![]() |
| የቤተልሔም ሕንፃ /መገናኛ/ (ጀርባ - ፊቱን ከታች ይመልከቱ) |
![]() |
| ቤተልሔም ሕንፃ ከፊቱ (በነገራችን ላይ ይህ ሕንፃ መስታወቱ አንፀባራቂ በመሆኑ እንዲቀየር ማስጠንቀቂያ ከተጻፈበት ወራት አልፈዋል::) |
![]() |
| Guess Where? You got it right; it is in front of Bole Medhanialem - የጄኔራሎቹ ሰፈር |
![]() |
| ለልማቱ ነው - ምናለበት? |
![]() |
ቃሊቲ (የጠጠር ማምረቻውን ስም ሳየው ያስቀኛል:: አንድ ሰሞን
ሲቪል
ሰርቪስ ኮሌጅን ድንጋይ ማምረቻ ይሉት የነበረው ይመጣብኛል፡፡) |
![]() |
| Got it Wrong: የኮሌጁ የመጽሔት ማስታወቂያ ኮሌጅ የሚለውን ጠንቅቆ አልጻፈውም! |
![]() |
| "ኢ-ልማታዊ መጽሐፎች" (ግልጽ በሆነ ምክንያት የትምህርት ቤቱን ስም ከመጥቀስ እታቀባለሁ) |
![]() |
| "የልማት መስዋዕት" - ለገሃር ከለታት አንድ ቀን |
![]() |
| Legend making: ቦሌ ቴሌ |
![]() |
| ሶኒክ ስክሪን - ፒያሣ |
![]() |
| Legend Making: ቦሌ - ሰን በርድ ካፌ (አሁን ጀግና አይሞትም የሚለው ቅርጽ ተነስቷል) |
![]() |
| ሐዋሳ አውቶቡስ ተራ - "ከኤድስ ለማምለጥ በየሱስ ማመን ነው" Really?! |
![]() |
| ሻሸመኔ - "የረዳኝ እግዚአብሔር ነው መኝታ ቤት" (ይህን ሳየው "እህቴ የላክሽልኝን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ አዋልኩት ሬስቶራንት" ብሎ አብርሃም አስመላሽ የቀለደው ቀልድ ይታወሰኛል::) |






















No comments:
Post a Comment