በዓመት አንዴ፣ ቃላት ሳንመርጥ እንዳሻን የምንናገርበት ዕድል ቢኖረን አሪፍ ነው በሚል 'በገና ጫወታ፥ አይቆጡም ጌታ' የሚለውን ተረት ከሞት አስነስቼ ልጠቀምበት ነው፤ እነሆ:–
(ከ18 ዓመታ በታች ለሆኑ ማንበብ አይፈቀድም)
– ፩ —
(ሰሞኑን ከተለቀቀው የይሳቃል ቀልድ የተቀነጨበ፤ በደምሴ)
አንድ ሰው የጋና ኤምባሲን አድራሻ ካድሬውን ጠይቆ የተሰጠው ምላሽ፤ በዚያ ኮብል ስቶን በተነጠፈበት መንገድ ትሄድና በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁት ወጣቶች የሚሠሩበትጋ ስትደርስ ወደኮንዲሚኒዬሙ ሂድ፣ እዚያ ራዕይህ ይሳካል። ምናልባት ካልተሳካ ግን ችግሩ ከኔ ሳይሆን ከአፈፃፀምህ ነው።
– ፪ —
አንዷ ኮረዳ ጉች ጉች ያሉት ጡቶቿ መሐል የብር መስቀል አድርጋለች። አንዱ ጎረምሳ ዝም ብሎ ወደዚያ አካባቢ ያማትራል።
ልጅት — ምነው፣ እየሱስ የተሰቀለበትን መስቀል እንዲህ የምታየው?
ጎረምሳ — አይ፣ ግራና ቀኙ የተሰቀሉትን ወንበዴዎች ነው ያየኋቸው።
— ፫ —
(ግጥም)
ባሳለፍነው ዓመት፥ ያ ሁሉ ሸፋዳ
አንዷ ካሜራ ፊት፥ እርሟን ብት*ዳ
ፊልሙን እስኪጠግብ፥ ኮምኩሞ ሲያበቃ
"ለአገሪቷ ክብር"፥ ቆምኩ አለ ጥበቃ!
ድንቄም የአገር ክብር፣ ድንቄም ውክልና
ቂጥ ገልቦ ክንብንብ፣ የቤትሽ ገመና
ሕዝቤ በያገሩ፥ ገብታ ሽር*ጥና
"ክብር…" ተባለልኝ፥ በቲቪ ታዬና።
ክብር ሲሉ…
ዜጋ በችግር ሰደድ ተነድፎ፥
ካገር እንደከብት ሲነዳ፣
እያየ ዝም ብሎ፥ በዚያ ስሜቱ የሚጎዳ፣
ሊቅም በሉት ደቂቅ፥ በዘነዘና ይ*ዳ።
Comments
Post a Comment