Tuesday, December 10, 2013

የፎቶሾፕ ፖለቲካ



በፎቶሾፕ የተሠራው ከቨር
ባለፈው ሰሞን  tigraionline.com የባሕር ማዶ ዜጎቻችን የሳዑዲ አረቢያውን መጥፎ አጋጣሚ ተቃውመው በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የወጡትን ሠላማዊ ሰልፍ ፎቶ ለፖለቲካ ግብዓቱ በማሰብ ለኢሳያስ አፈወርቂ ቱፈዛ የተወጣ ሰልፍ አስመስሎ በፎቶሾፕ በመቀየር ዜና ሠራበት፡፡ አሁን ደግሞ ትላንት ያየሁት በፌስቡክና በትዊተር ላይ የተለቀቀ ‹‹የዕንቁ›› መጽሔትን ከቨር የቀየረ ፎቶ ተመሳሳይ ማጭበርበር ሞክሯል፤ ይህንን ማን እንደሠራው ባይታወቅም ችግሩ ስር እየሰደደ መሆኑን ማሳበቁ ነው እንግዲህ፡፡

በፌስቡክና ትዊተር ላይ የታየው ፎቶ ላይ ቴዲ አፍሮ ‹‹ምኒልክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ያደረጉት ጦርነት ለእኔ ቅዱስ ጦርነት ነው›› ብሎ እንደተናገረ ተደርጎ ቀርቧል፡፡ እውነተኛው ላይ ደግሞ ‹‹አመጣጡን ያየ አካሔዱን ያውቃል›› ይላል፡፡ ገርሞኝ የውስጠኛውን ቃለምልልሱን አገላበጥኩ፡፡ ከውስጥ ያለው ስለጦርነቱ የቀረበለት ጥያቄ ላይም ‹‹ቅዱስ ጦርነት›› የሚል ፈልጌ አጣሁ፡፡


እውነተኛው የመጽሔቱ ከቨር
 

የቃለ ምልልሱ ቅንጫቢ

Follow the comments of this story here. 

No comments:

Post a Comment

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንገድ ጠራጊ ማናቸው?

(በፍቃዱ ኃይሉ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዐቢይ አሕመድ እርካብና መንበር በአባዱላ ገመዳ የተቀየሰ ይመስለኝ ጀምሯል። ምክንያት አለኝ። አባዱላ በተቀናቃኞቹ ጃዋር መሐመድም፣ ዐቢይ አሕመድም አድናቆት የተቸራቸው ሰው ናቸው።  ጃ...