Sunday, February 2, 2014

ጥር መጣ ሙሽራ ቀንጥሱ

በጥር ወር ገበሬው ሰብሉን ሰብስቦ የሚጨርስበትና ሠርግ የመደገስ አቅሙ የሚጎለብትበት ወቅት ነው። በዚሁ ተለምዶ ከተሜውም ለሠርግ ጥርን የሚመርጠው ይላሉ የአገራችን የልምድ አንትሮፖሊጅስቶች።

እንደሠርግ እጅ፣ እጅ የሚለኝ ነገር እየጠፋ ነው። ወይ ባሕላዊ አይሆን፣ ወይ ዘመናዊ እንዲሁ የጨረባ ተስካር ብቻ ሰው ሰብስቦ እዩኝ ማለት - ማለት የኛ አገር ሠርግ ትርጉም ሆኗል። ደግሞ የወገኝነቱ አበዛዝ!

ባለፈው ሒልተን ሆቴል ፊት ለፊት አፍሪካ ፓርክ አጠገብ ሙሽሮች የፎቶ ስርዓት እያደረጉ ነበር። ይህ እንግዲህ ከሠርጉ ዕለት ውጪ ለማስታወሻ የሚነሱት ፎቶ ላይ መሆኑ ነው፤ አጃቢ የለም።  አስፋልቱ ላይ ሙሽሪት ተዘርፍጣ፣ ሙሽራም እሷን እየተንከባከበ የሚያስመስለውን ድርጊት እያደረገ ፎቶ ሲነሱ አይቼ ሳበቃ በማየቴ እኔ አፈርኩ። ሚስቴ እንዲህ ዓይነት ነገር እናድርግ ከምትለኝ ጋብቻው ይሰረዝ ብትለኝ ውለታ እንደዋለችልኝ እቆጥረዋለሁ።

የከተሜ ሠርጎች ከሠርጉ በፊት የስቱዲዮ ፎቶ መነሳትን ባሕል አድርገውታል። ስቱዲዮ ውስጥ፣ የተለመዱ የፎቶ አነሳስ ወጎች አሉ። ጥንዶቹ በፍቅራቸው ዘመን አድርገዋቸው የማያውቋቸውን (ለምሳሌ ሙሽራይቱ የሙሽራውን ከረባት እየጎተተች) ለማስታወሻ ፎቶ ይነሳሉ። እኔ የምለው፤ እነዚህ ጥንዶች ወደፊት ማስታወስ የሚፈልጉት ሆነው የማያውቁትን ነገር ነው እንዴ? ስቱዲዮዎቹ በውሸት ጥርብ ግድግዳዎች፣ እንስሳት፣ የሙዚቃ መሣሪያዎችና ጌጣጌጦች ያሸበረቁ ዓይነት ሲሆኑ ጥንዶቹ በኪራይ ልብስ "የውቡ ቤት" ፈርጥ ሆነው ይነሳሉ። ይህንኑ ፎቶም ለልጆቻቸው ማስታወሻ ብለው ሊያሳዩ ያቆያሉ።

Friday, January 31, 2014

Are Revolutions Meant to be Betrayed?

Revolutions are usually portrayed as the most heroic acts that can be done by a generation. Some say that they are simply shortcuts for evolution which bring immediate changes by shaking the status quo that, otherwise, might take long to; others say they are only good in clearing the way for real changes.: Only a few say revolutions are means in which you throw away the evils you know to put in the evils you don't know.

During revolutions, things happen so fast that one can't actually have control nor even clear understanding of what is going on. Post revolutionary eras are mostly unpredictable. Pre-revolution is the best course of any revolutionary progress; it engages wide range of  popular participation and is determined to a goal of laying tyranny down. That's not the same for post revolution era.

Revolutionaries don't usually talk to each other what kind of change they've to bring. Even if they do, they care less for the differences existed between them. They just work together to topple whom they call an obstacle for their esteemed change.

This working together towards different goal brings a problem when they succeed. It's true that predators agree until they will have to split their prey. After a revolution, come other successive revolutions. This is either because each revolutionary wants to take the key position to bring about their change or because the thrown ones want to come back in different colors.

Revolutions are participatory. Like the man behind the Jan 25/2011 Egypt revolution, Wael Ghonim, said it, they help in realizing “the power of the people is greater than the people in power". However, no one can surely tell not only whether the revolutionary people owns the fruit of the revolution or not; but also whether the change is for good or not. Now - 3 years after the revolution, in Egypt, Wael Ghonim's  name is labeled as “foreign agent" and he is living in Dubai. If he goes back to Egypt, he will join his friends in jail. Friends of Mubarek are now back in power.

Thursday, January 30, 2014

ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግሥትና መገናኛ ብዙኃን (የሲምፖዚየሙ አያዎ)


ከመሐል እንጀምር፤ ዶ/ር ያዕቆብ ጥያቄ እየጠየቁ ነው፡፡ ‹‹እንዳለመታደል ሆኖ ከኢትዮጵያ የማጣቅሰው ፕሬዚደንት ኖሮ አያውቅም›› አሉ፤ ከእርሳቸው በፊት ብዙዎች የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን እያጣቀሱ ስለነበር አባባላቸው ፈገግ ያሰኛል፡፡ ሲቀጥሉ ‹‹የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሩዝቬልት ከነጻ ፕሬስ እና ከነጻ ምርጫ አንዱን ምረጡ ቢባሉ የቱን ይመርጣሉ ሲባሉ ‹I will take my chances with free press› አሉ›› የሚለውን በማስታወስ የነጻ ፕሬስ ወሳኝነትን አሳሰበው አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡

ይህ የሆነው ባለፈው ቅዳሜ (ጥር 17/2006) በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነት ት/ቤት የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ያዘጋጁት ሲምፖዚየም ላይ ነው፡፡ ሲምፖዚየሙ የተዘጋጀው ‹‹የዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግሥት እና መገናኛ ብዙኃን ግንኙነት (Nexus)›› በሚል ርዕስ ሲሆን በመወያያ ጽሑፍ አቅራቢነት እና በታዳሚነት የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ የግል እና የመንግሥት ሚዲያ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡ የጽሑፍ አቅራቢዎቹ የጋዜጠኝነት ት/ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር አብዲሳ ዘርኣይ፣ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ. ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዱ ይመሰል፣ የኢዴፓ የቀድሞ ፕሬዚደንት አቶ ሙሼ ሰሙ፣ የሕዳሴው ግድብ አስተባባሪ ኮሚቴ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛዲቅ ኣብርሃ እና የፎርቹን ጋዜጣ የጋራ ባለቤት እና ዋና አዘጋጅ ታምራት ገ/ጊዮርጊስ ነበሩ፡፡

የፕሮግራሙ ታዳሚ ከነበሩት ውስጥ ደግሞ እነ ዶ/ር ዳኛቸው፣ አቦይ ስብሓት፣ ሽመልስ ከማል፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የአንድነት ፓርቲው ሀብታሙ አያሌው እና ሚሚ ስብሓቱን የመሳሰሉ ሰዎች ይጠቀሳሉ፡፡

የሲምፖዚየሙ ፋይዳ

ዶ/ር አብዲሳ ዘርኣይ በመግቢያ ንግግራቸው ላይ ‹‹የዝሆኑን እና የሦስቱን ዓይነስውራን ታሪክ›› አጣቅሰዋል፡፡ አንዱ እግሩን ዳብሶ ዝሆን አጭር ቀጭን ነው ሲል፣ ሁለተኛው ኩምቢውን ዳብሶ ዝሆን ረዥም ቀጭን ነው ሲል፣ ሦስተኛው ደግሞ ሆዱን ዳብሶ ወፍራም ድብልብል ነው ሲል ሁሉም ትክክለኛውን ዝሆን ሳይረዱ ቀሩ ካሉ በኋላ የሌላ ሰው አባባል ተውሰው ‹‹ስንተባበር ሙሉውን ዝሆን እናያለን›› ብለው የሲምፖዚየሙን ፋይዳ ለማስረዳት ሞክረዋል፡፡

ብዙ የሲምፖዚየሙ ታዳሚዎች በዝግጅቱ እና ስብጥሩ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ዳኛቸውም ይህንኑ ሙከራ አወድሰው ነገር ግን የስብጥሩን ንፅፅር ሲመለከቱ የአለቃ ደስታ አባት ነገዎ የተናገሩት ትዝ እንዳላቸው በቀልድ አውስተዋል፡፡ አቶ ነገዎ የመጀመሪያዎውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ምክር ቤት አባላት ከተመለከቱ በኋላ ‹‹እነዚህ ሰዎች የሚመክሩ ናቸው የሚመከርባቸው?›› ብለው ጠይቀው ነበር በማለት፡፡

ልማታዊ መንግሥት እና ዴሞክራሲ፤ ምንና ምን ናቸው?

Wednesday, January 29, 2014

ዓይኔ ነው ላይኔ?



ባለፈው ሰሞን ‹ታምራት ላይኔ ታስሮ ከርቸሌ ሲገባ ያየው የደርጉ ለገሠ አስፋው “ዓይኔ ነው ላይኔ" አለ› የሚል የፌስቡክ ቀልድ ሰምቼ በሳቅ ፍርስ ብዬ ነበር። ዛሬ አመሻሽ ላይ ቤቴ እየገባሁ ሳለ የሰማሁት ነገር ደግሞ ለገሠን በቀልዱ ላይ እንደገረመው ዓይነት አስገረመኝ።

“ልማቱ በተፋጠነበት፣ አስተዳደሩ ኮሽ በማይልበት" ~ ምን ነካው ቄሱ?

ሰፈሬ “የማርያም ጠበል" የሚባል አለ፤ የማርያም ቤተክርስትያን ታቦት ትላንት ጠበሉጋ መጥቶ ያድርና ዛሬ ይመለሳል። ስለዚህ መንገዴ በሰው ተጥለቅልቋል። ዘማሪዎችና ከነሱ በጎላ ድምፅ ሰባኪው ሲያስተምር በቅርብ ርቀት ከታቦት ማደሪያው አካባቢ ይሰማኛል። በመሐል የሆነ ቃል የሰማሁ መሰለኝ። ጆሮ ሰጠሁት፣ አዎ ደገመው። ስለልማት እያወራ ነው። ስለየቱ ልማት?

“ልማቱ እንዲህ እየተፋጠነ እንዴት አልናገርም?" ብሎ ጠየቀ። የሚመልስለት አልነበረም፤ ሰባኪ ለነገሩ ይናገራል እንጂ አያዳምጥም። ከዚያ፣ “ልማቱ በተፋጠነበት፣ አስተዳደሩ ኮሽ በማይልበት፣ አምልኮ በማይከለከልበት…" እያለ ቀጠለ፤ ንግግሩ እሱን ግምት ውስጥ ከመጣል በላይ ፋይዳ ያለው ግን አይመስልም። ‹ተመልሼ የዚህን ሰው ድምፅ ልቅረፅ ይሆን ወይስ ይለፈኝ› እያልኩ ወደፊት ማዝገሜን ቀጠልኩ። በተዳጋጋሚ “ልማት" የሚለው ቃል የሚጠቀስበት እና ተገንብቶ ያላለቀው “ባቡር" ሳይቀር ስሙ የተነሳበት “ስብከት" እየራቀኝ እየራቀኝ መጣ። ኋላ ላይ ያሳሰበኝ ደግሞ ‘ሰባኪው ካድሬ ሆኖ ነው ወይስ ካድሬው ሰባኪ ሆኖ’ የሚለው ነው። ዛሬ ጠዋት ደግሞ በድምፁ ሌላ ሰባኪ እንደሆነ የለየሁት ሰው ሃይማኖታዊ ብቻ የሆነ ነገር ሲናገር እየሰማሁ አለፍኩ። ሆኖም የማታው አልወጣልኝም።

በዚህ ዓይነት ኢሕአዴጉም፣ ካድሬ–ቄሶቹም ከቀጠሉበት ከዛሬ 10 ዓመት በኋላ የሚኖረው ስብከት እንዲህ ሊሆን ይችላል፡-
“እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረ በኋላ ‘አዳም ብቻውን መሆኑ ልማታዊ አይደለም፤ ስለዚህ ልማታዊት አጋር እንፍጠርለት’ ብሎ ሔዋንን ፈጠራት።

“ከዚያም ልማታዊ ዴሞክራሲ* ይተገበርባት በነበረችው በኤደን ገነት በተድላ እና ደስታ እንዲኖሩ ተፈቀደላቸው። ሆኖም አዳም እና ሔዋን የኒዮ–ሊበራሊዝም አስተሳሰብ ተፀናውቷቸው አትብሉ የተባሉትን እፀ–በለስ እንደ ሳጥናኤል ባሉ የውጭ ኃይሎች ግፊት በመብላታቸው እና ቀዩዋን መሥመር በማለፋቸው ምድር ወደተባለ እስር ቤት ተጣሉ።

“ይህ በሆነ በአምስተኛው ሺሕ አምስት መቶ ዓመቱ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደምድር በመላክ ልቡ በኒዮ-ሊበራሊዝም አስተሳሰብ የሸፈተውን አዳምን ሞቶ ወደገነት እንዲገባ መስዋዕትነት ከፈለለት፡፡ አዳምም ሰይጣን ከዚህ ጭንቅ ያወጣኛል፣ በፈጣሪ ላይ ጫና አድርጎ ያስፈታኛል ብዬ አምኜ በድፍረት ለፈፀምኩት ስህተት እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝ ብሎ ለመነ፡፡

“ሆኖም፣ አዳም መልሶ፣ መላልሶ ወደኒዮ-ሊበራሊዝም ፊቱን ማዞሩን አላቆመም ነበር፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር ሌላኛው ልጁን መሲሕ መለስ ዜናዊን ወደምድር ላከ፤ ቅዱስ መለስ ዜናዊም ስለዝቡ ደኅንነት በረሃ ለበረሃ እየተንከራተቱ ታንክ ተደግፈው መጽሐፍ አነበቡ፡፡ ከዚያም ለሕዝባቸው አብዮታዊ ዴሞክራሲን ሲያስተምሩ ኖረው ተሰዉ፡፡”

---
*
ልማታዊ ዴሞክራሲ ድኅረ መለስ ዜናዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው። ኢሕአዴግ ‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›ን በ‹ልማታዊ ዴሞክራሲ› መተካቱን ተከትሎ ኢሕአዴግ የሚለውም ኢሕለዴግ በሚል ቢተካ ጥሩ  እንደሆነ በጥምቀት በዓል ላይ የተገኙ አንዳንድ ምዕመናን ተናግረዋል። (በነገራችን ላይ፣ ‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ› በዚህ ወር ሕትመቱ ተቋርጧል፤ ‹ልማታዊ ዴሞክራሲ› ሆኖ ይመለስ ይሆን?)

Sunday, January 26, 2014

What about the right to be heard?

Following the 2010 national election, I have crunched the numbers of votes in Addis Ababa to find out that '11 out of 23 seats should've be taken by oppositions had it been proportionally that our voices are counted or represented.' Knowing that almost half of Addis Ababa's election participants in 2010 voted to oppositions, it is sad to also know that their voices are represented by only a single man in the house of representatives.

In addition, no one has the confidence to say the dissidents in Ethiopia either have other means to express their alternatives as to how they want their country should be built or even how they want to live their life. The public school of discourse, which is the media, and civil societies are incapacitated.

Nevertheless, the question is not limited to have a means of expressing oneself. People manage their ways of doing it anyway. That's how and why social media are now playing pivotal role in breaking news and creating hot discussions especially in authoritarian countries including Ethiopia. So, the question remains to be: 'is the government listening?'

The constitution grants the freedom to expression and when it is violated, people shout out referring to the article. If democracy is about popular participation and if Ethiopia didn't shut its doors for democracy then how is it possible to ensure that the people's voices are heard?

Freedom of speech is crucial. However, what is most crucial is to be heard. Where is this 'right of people to be heard' by the government they appointed? Or, where is the obligation of the government to hear its people? Because, last time I checked, people speak to be heard.

Saturday, January 25, 2014

የዶጋሊ ድል

    የውጭ ጸሐፊዎች ስለአድዋ ሲጽፉ የአድዋ ጦርነት እያሉ ነው የሚጽፉት፤ እኛ ግን የአድዋ ድል ነው የምንለው፡፡ ማስታወስ የምንፈልገው ድሉን እንጂ ጦርነቱን አይደለም፡፡ የዶጋሊ ድልንም በብዛት የጻፉት የውጭ ጸሐፍት ባብዛኛው ‹የዶጋሊ ጦርነት› እያሉ ነው የሚተርኩት፤ ልዩነቱ እኛም እነሱኑ ተቀብለን ታሪኩን የዱጋሊ ጦርነት እያልን ማስታወሳችን ነው፡፡ ነገር ግን ጦርነቱ በእኛ ድል አድራጊነት እስከተጠናቀቀ ድረስ ልክ እንደአድዋው ሁሉ ‹የዶጋሊ ድል› ብለን መተረክ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥም የዱጋሊ ድል ታሪካዊ ፋይዳ ከአድዋ ድል የሚተናነስ አይደለም፡፡  

ልክ የዛሬ 127 ዓመት ወደኋላ፣ ጥር 18/1879 በራስ አሉላ የሚመራው የኢትዮጵያ ጦር፣ አውሮጳውያን ብዙም ያልተዘጋጀ እያሉ የሚጽፉለትን ነገር ግን በ23 የጦር አመራሮችና በ477 ወታደሮች የተገነባውን ሠራዊት በ10,000 ጦርና ጋሻ እና ጥቂት ቆመህ ጠብቀኝ የታጠቁ አርበኞች ድል ነሳቸው፡፡ ይህ ጦርነት ነበር የአድዋውም፣ የማይጨዉም ጦርነት የቂም መንስኤ እና የድል ዕድል፡፡  

ዶጋሊ፣ በዛሬዋ የኤርትራ ምድር ላይ የምትገኝ መሬት ናት፡፡ ደርግ የዶጋሊ ድል በዓልን ሕዝባዊ በዓል ሆኖ እንዲከበርማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ በዶጋሊ የመታሰቢያ ኀውልት እንዲቆም አድርጎ ነበር፡፡ ጣሊያኖችም በጦርነቱ ለተሰዉ ወታደሮቻቸው ሮም ላይ የመታሰቢያ ኀውልት አቁመውላቸዋል፡፡ የዶጋሊው የድል ኀውልት ግን የሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሕግሓኤ) ደርግን አሸንፎ ኤርትራን ሲቆጣጠር ኀውልቱን አፍርሶታል፡፡  

Friday, January 24, 2014

አመክሮና በቀለ ገርባ

 በዘላለም ክብረት

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ምክትል ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ስራ አስፈፃሚ የነበሩት “ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ  የአሸባሪ ቡድን የሆነው ኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል ክስ ተመስርቶባቸው የ8 ዓመት እሥር የተበየነባቸው ሲሆን፤ ይግባኝ ጠይቀው እስሩ ወደ 5 ዓመት ዝቅ ተደርጎላቸዋል፡፡

ከ5 ዓመቱ የእስር ጊዜ ውስጥም 3ቱን ዓመት በመጨረሳቸው በአመክሮ ይፈቱ ዘንድ ለማረሚያ ቤቱ ያመለከቱ ሲሆን ማረሚያ ቤቱም ‹አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው›  በማለት እስከአሁን ሊፈታቸው አልቻለም፡፡ ይህም ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡

አንዳንድ ህጋዊ ሁኔታዎች ስለጉዳዩ፡

አመክሮ ምንድር ነው?


ሌላውን ትርጉም ትተን የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ‹በተወሰነ ጊዜ በአመክሮ መፈታት› በሚለው ክፍል በተለይም በአንቀፅ 202 እንደደነገገው፡

"ተቀጭው ከተወሰነበት የእስራት ጊዜ ከሶስት እጅ ሁለቱን እጅ ወይም ፍርዱ የእድሜ ልክ እስራት ሲሆን ሀያ ዓመት በፈፀመ ጊዜ አግባብ ባለው አካል ወይም በጥፋተኛው አሳሳቢነት ጥፋተኛውን ከቅጣቱ ነፃ ያወጣዋል፡፡"
ይህም ማለት አመክሮ 2/3ኛውን የቅጣት ጊዜውን የጨረሰ ታራሚ ከእስር የሚፈታበት አሰራር ነው፡፡

አመክሮ ለማግኝት ምን መስፈርት ማሟላት ያስፈልጋል?


የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ከላይ በጠቀስነው አንቀፅ 202 ላይ አመክሮ ለማግኝት አንድ እስረኛ ማሟላት የሚያስፈልገውን መስፈርቶች ይዘረዝራል፡፡ ይህም፡

Irreechaa 2016

(Befekadu Z. Hailu) [Today marks the 10th Anniversary of Irreechaa 2016 ,  a turning point for the then -Oromo protests . In my book, "...